tgoop.com/Enatachn_mareyam/18072
Create:
Last Update:
Last Update:
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ክብርት ሰንበት ] 🕊
❝ አሁን ማንኛውም ቁርባኑ [ ሥጋውና ደሙ ] በተሠራበት ቤተ ክርስቲያኑ ጌታችን ስለማይለይ ፣ ሰንበትን እያከበርን መሆናችንን መናገር እንችላለን።
ይህች ሰንበት [ ቁርባን የተሠራባት ማንኛውም ዕለት ] እያከበርናት ያለነው ለምትመጣው ሰንበት ምሳሌ አድርገን አይደለም ፤ በመንግሥቱ ውስጥ ሆነን ሰንበታችንን [ ዕረፍታችን ክርስቶስን ] ፊት ለፊት የምናይባትን የምትመጣዋ ሰንበት መያዣ አድርገን እንጂ። ❞
[ ሊቅ ቀሲስ ታድሮስ ]
🕊
❝ በነቢዩ በዳዊት መዝሙር በታወቀች በበዐላችን ቀን በእውነት ሃሌ ሉያ እንበል ፣ [ ይህች ቀን ያልታወቀች ያይደለች ] እግዚአብሔር ሥራውን ይሠራ ዘንድ የጀመረባት በእውነት የታወቀች ናት።
ወዮ ይህቺ ዕለት ቀዳሚት ናት ደኃራዊት አይደለችም ፣ ወዮ ይህቺ ዕለት ለዘላለሙ የምትሠለጥን [ ሰፋኒት ወይም ለዘላለም ጸንታ የምትኖር ] ደኃራዊት ናት ፤ ወዮ ይህቺ ዕለት ለአብርሃም ተገለጸች ፣ እርሱንም አስመኘች ፣ ትንቢትም አናገረች እርሱንም ደስ አሰኘች። ❞
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/18072