tgoop.com/Enatachn_mareyam/17991
Last Update:
†
🕊 [ በዓለ ዸራቅሊጦስ ] 🕊
🕊 የቤተክርስቲያን የልደት ቀን 🕊
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። ❞ [ ዮሐ.፲፬፥፳፮ ፤ ፲፭፥፲፮ ]
ቅዱሳን ሐዋርያት ፦
❝ ከአብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው የሚሆን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስም አንድ ነው። ...
በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን ፤ ❞ [ ዲድስቅልያ ]
🕊 🕊
❝ ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡ ❞ [ መጽሐፈ ምሥጢር ]
❝ ሃሌ ሉያ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው። ❞ [ ቅዱስ ባስልዮስ ]
[ 🕊 እንኩዋን አደረሳችሁ 🕊 ]
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/17991