tgoop.com/Enatachn_mareyam/17962
Last Update:
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ አምስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ አንድ ሰው ኑዛዜ ለማድረግ ከወሰነ ፣ በዚህ ምክንያት ነፍስ ኃጢአትን ከመፈጸም በልጓም እንደ ተያዘ ትያዛለች፡፡ በድፍረት እያደረግነው ሳንናዘዝ የምንተወው ከሆነ በጨለማ እንዳለ እንሆናለንና፡፡
የበላዩ በማይኖርበት ጊዜ ፊቱን በዓይነ ሕሊና መሳልና ዘወትር በፊታችን እንደ ቆመ በማሰብ ፣ መሰባሰብንም ሁሉ ፣ ወይም ንግግር ወይም ምግብ ፣ ወይም መኝታ ፣ ወይም እርሱ ይጠላዋል ብለን የምናስበውን ማንኛውንም ሌላ ነገር ሁሉ ካስወገድን ፣ እንኪያስ በእውነት እውነተኛ መታዘዝን ተምረናል፡፡ ዲቃላ ልጆች የመምህራቸውን መቅረት [ አለመኖር ] እንደ ደስታ ይቆጥሩታል ፣ በሕግ የተወለዱት ግን እንደ ጉዳት ይቆጥሩታል፡፡
አንድ ጊዜ እጅግ ልምዱ ካላቸው አባቶች አንዱን ትሕትና እንዴት በመታዘዝ እንደሚገኝ ይነግረኝ ዘንድ አጥብቄ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ፦ ለይቶ ለይቶ የማወቅ ጸጋ ያለው ታዛዥ ሰው ፣ ሙት የሚያስነሣና የአንብዕ ጸጋ የተሰጠው ፣ እንዲሁም ከፀብእ [ ከፀብአ አጋንንት ] ነጻ ቢሆን እንኳ ፣ ያን ያደረገው የመንፈሳዊ አባቱ ጸሎት እንደ ሆነ አድርጎ የሚያስብ ነው ፣ ከከንቱና ባዕድ አሳብም የተለየ ሆኖ ይኖራል፡፡ እርሱም ራሱ እንዳመነው ስለ ተደረገው ነገር በአባቱ እርዳታ እንጂ በራሱ ጥረት እንደ ሆነ አድርጎ እንዴት ራሱን ሊያስታብይ ይችላል? አለኝ፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/17962