tgoop.com/Enatachn_mareyam/16624
Last Update:
†
[ 🕊 የዐቢይ ጾም ሳምንታት 🕊 ]
💖
ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል ፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ ፣ ቅድስት ፣ ምኩራብ ፣ ደብረዘይት ፣ ገብረ ኄር ፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡
🕊 💖 🕊
[ ፩ ኛ. ዘወረደ ፦ ]
በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን ፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን ፤ አሜን !
† † †
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16624