tgoop.com/Enatachn_mareyam/16481
Last Update:
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ 💖 መንፈሳዊው መሰላል 💖 ]
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ]
🕊
❝ የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር እንደ መሆኑ ፣ ከእርሱ ውጭ በራሱ ሕይወት ያለው ነገር የለም፡፡
ስለሆነም መንፈሳዊ ሕይወት ስንል ሰዎችና መላእክት ከእግዚአብሔር ሕይወትነት ያላቸው ሱታፌ ሲሆን ይህ ሱታፌም አንድ ቦታ ላይ የሚያቆምና የተገደበ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ነው፡፡
እግዚአብሔር ፍጻሜ የሌለውና “እስከዚህ ድረስ” ተብሎ የማይወሰን አምላክ እንደመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ኅብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ በእርሱ ሕይወት የሚሳተፉ ሁሉ ጉዟቸው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም፡፡ የመንፈሳዊ ጉዞ አስደሳችነቱም ይህ ነው ፤ ወደማይደረስበት ፣ ግን ደግሞ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብሮ ወዳለ አምላክ የሚደረግ የማያቋርጥ ጉዞ !
ይህ ጉዞ ፣ ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ባየው መሰላል አንጻር ሥዕላዊ በሆነ ሁኔታ ተገልጦልናል፡፡ በመሰላሉ ላይ [ ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ሳይሆን ከመሰላሉ በላይ ] እግዚአብሔር “ተቀምጦ” ነበር፡፡ መሰላሉ በመሬት ላይ የተዘረጋ መሆኑ እግዚአብሔር ወደ እርሱ የምንወጣበትን የቅድስና መሰላል ልንደርስበት በምንችለው በመሬት ላይ የዘረጋልን መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ፣ እግዚአብሔር ከመሰላሉ በላይ ቆሞ መታየቱ ደግሞ ከላይ ሆኖ “አይዟችሁ ፣ ወደ እኔ ኑ" እያለ በፍቅሩ የሚጠራንና የሚስበን እርሱው ራሱ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከታች ከመሬቱ ጀምሮ የሚጠራንና የሚስበን ፣ በመሰላሉ ላይ የትኛውም ደረጃ ላይ ብንደርስም አሁንም ከዚያ በላይ ወዳለው እንድንቀጥል የሚያደርገን ከመሰላሉ በላይ ያለው እርሱ ነው፡፡
እንደዚያ ሆኖም ግን እርሱ ከመሰላሉ በላይ [ ማለትም በባሕርዩ ሊደረስበት የማይችል ] ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት ይህ ነውና ፤ ከራሳችን በላይ ለራሳችን የቀረበ የውስጥና የቅርብ መጋቢና ተንከባካቢ አባት ፣ ሆኖም ግን በባሕርዩ የማይታወቅና የማይደረስበት ረቂቅ አምላክ ! ❞
[ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ትርጓሜ ላይ የሰጡት አስተያየት ]
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16481