tgoop.com/Enatachn_mareyam/16452
Last Update:
#አማኑኤል__ሆይ
#አቤቱ_ተወዳጅ_አማኑኤል_ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
#አማኑኤል_ሆይ ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን፤ ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
#ክብርና_ምስጋና_ላንተ_ይሁን🙏
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16452