tgoop.com/Enatachn_mareyam/16385
Last Update:
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ መታዘዝ ! ]
🕊
❝ ሁለት በሥጋ ወንድማማቾች የሆኑ አኃው በገዳም ለመኖር ሄዱ፡፡ አንደኛው ባሕታዊ ነበር ፣ ሌላው ደግሞ ፍጹም ታዛዥ ነበር።
መንፈሳዊ አባቱ የሚያዘውን ማንኛውንም ነገረ ሁሉ ያደርጋል ፤ በጧት ብላ ቢለውም ይበላል፡፡ ከታዛዥነቱ የተነሣ በገዳሙ የሚታየው በልዩ ሁኔታ ነበር፡፡
ባሕታዊው ወንድም ግን በዚህ ሁኔታው ተቆጣና ለራሱ "በእርግጥ ታዛዥ መሆኑን ለማየት እፈትነዋለሁ" አለ፡፡ ስለዚህም ወደ አባቱ [ የገዳሙ አበምኔት ] ሄደና " ወደ ሆነ ቦታ አብረን እንሄድ ዘንድ ወንድሜን ላክልኝ " አለው:: አባቱም እንዲሄድ ነገረው ፣ ባሕታዊው ግን ይህን ያደረገው ሊፈትነው ነበር፡፡
ከዚያም ወደ ወንዝ ሄዱ፡፡ በዚያ ብዙ አዞዎች ነበሩ ፤ " ወደ ወንዙ ግባና ተሻገር " አለው፡፡ እርሱም ወደ ወንዙ ወረደ ፣ አዞዎቹም ሰውነቱን ሊልሱ መጡ ፣ ግን ምንም ምንም ዓይነት ዓይነት ጉዳት አላደረሱበትም፡፡
ይህንን ሲያይ ባሕታዊው "ና ከወንዙ ውጣ" አለው፡፡ ሲሄዱ በመንገዳቸው ላይ የሞተ ሰው አስከሬን በመንገዱ ዳር ተጥሎ አገኙ፡፡ ባሕታዊው "ያረጀ እራፊ ቢኖረን ኖሮ በላዩ ላይ ጣል እናደርግበት ነበር" አለ፡፡ ተኣዛዚ የሆነው ወንደሙ ግን "ከሞት ይነሣ ዘንድ እንጸልይ" አለው፡፡ መጸለይ ጀመሩ ፣ በጸሎታቸው ጊዜም ምውቱ ምውቱ ተነሣ፡፡
ባሕታዊው "የሞተው ሰው የተነሣው ስለ እኔ ብሕትውና ነው" ብሎ በውስጡ ራሱን ከፍ አደረገ፡፡ ሆኖም ባሕታዊው ታዛዢ የሆነውን ወንድሙን እንዴት በአዞዎች እንደ ፈተነውና የሞተው ሰው እንዴት እንደ ተነሣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለገዳሙ አባት ገልጦለት ነበር፡፡ ወደ ገዳሙ ሲመለሱ የገዳሙ አባት ለባሕታዊው "ወንድምህን ያደረግኸው ምንድን ነው? የሞተው ሰው ተነሥቶ እንደ ገና ወደ ሕይወት የመጣው በእርሱ ተኣዛዚነት ነው" አለው። ❞
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16385