tgoop.com/Enatachn_mareyam/16383
Last Update:
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ ስምንት ]
🕊
[ አባ ሲሶይ የተናገረውን ቃል ሲያብራራ ! ]
🕊
❝ አንድ እኁ አባ መቃርዮስን ፦ “አባ ሲሶይ አንድ ሲሰጥ አሥር የሚቀበል አለ ሲል የተናገረው ነገር ምን ማለት ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡
አባ መቃርዮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት ፦ “ዲያብሎስ በቀንም ሆነ በማታ በሚጋደለውና ትኅርምትን ገንዘብ ለማድረግ እየተለማመደ ባለ ሰው ላይ ማነጣጠሩንና ማሸመቁን መቼም ቢሆን አያቆምም ፣ እንዲህ ያለውን ሰው ከመተናኮልም ሥራ አይፈታም፡፡
ነገር ግን ይኸ ሰው ዲያብሎስን በአንድ ምት ብቻ ቢቋቋመው [ ማለትም በጌታችን ደግነትና ምሕረት ሥር ወድቆ በዕንባ ቢማጸን ] ደግና ቅን የሆኑትን የሚያፈቅር አምላካችን በዛ ሰው በአንዱ ምት ደስ በመሰኘት የዲያብሎስን አሥር ምቶች ከንቱና ባዶ ያደርጋቸዋል፡፡
ምክንያቱም ሰው ሥጋና ደም ብቻ ነውና፡፡ በአንድ ምት [ በትሕትና ] ብቻ ብዙና ረቂቃን የሆኑትን የዲያብሎስን ተንኰሎችና ሥራዎች ከንቱ ያደርጋቸዋል ፤ ከትሕትና ፊት ድል መነሣትና መውደቅ የዲያብሎስ ጠባይ ነውና፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16383