tgoop.com/Enatachn_mareyam/16360
Last Update:
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ ሰባት ]
🕊
[ አባ ወቅሪስን ስለ ክፉ ሃሳቦች አስተማረው ! ]
🕊
❝ አባ ወቅሪስ ከሌሎች አኃው ጋር አብሮ ከአባ መቃርዮስ ጋር ተቀምጦ ሳለ አባ መቃርዮስን ፦ “ ሰይጣን በወንድሞች ላይ ይወረውራቸውና ይፈትንባቸው ዘንድ እነዚህን ሁሉ ክፉ ሃሳቦች እንዴት ሊያገኝ ቻለ? ” ብሎ ጠየቀው፡፡
አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “በምድጃ እሳት የሚያነድ ሰው በእጁ ብዙ ማቀጣጠያ እንጨት ይይዛል ፣ ያንንም ወደ ምድጃው ከመጣል አያመነታም ፣ ወደ ኋላም አይልም፡፡ ዲያብሎስም እንደዚህ ነው፡፡ እሳቶችን ይለኩሳል ፣ ያቀጣጥላል ፣ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ ሰው ልቡና ማንኛውንም ዓይነት የክፉ አቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን ማለትም ርኩሰቶችን ከመጣልና የተለኮሰውን እሳት አብዝቶ እንዲነድ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡
ውኃ የእሳትን ኃይል እንደሚያጠፋውና አሸናፊው እንደ ሆነ እናያለን፡፡ እኛን የሚረዳንና የሚጠብቀን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና ድል የማይነሣው የመስቀሉ ኃይልም እንዲሁ ነው፡፡
ድካማችንን ከእርሱ እግር ሥር ብንጥል የዲያብሎስ ክፉ ሃሳቦች ከነ ቅርንጫፎቻቸው ከእኛ ውስጥ ይጠፋሉ ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልባችን በሰማያዊ እሳት በመንፈስ እንዲቃጠልና በሐሤት እንዲሞላ ያደርገዋል፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16360