Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/Enatachn_mareyam/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም@Enatachn_mareyam P.16352
ENATACHN_MAREYAM Telegram 16352
- በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል::
- በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
- ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል::
- እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች ፲፩ [11] ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር ፲፩ [11] ብቻ ነበር::
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል::
- ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን [በ፫፻፹፩ [381] ዓ/ም] መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::

ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ፴፫ [33] ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::

🕊 †  ቅድስት ኢላርያ   †  🕊

† "ኢላርያ" ማለት "ፍሥሕት [ደስ የተሰኘች]" እንደ ማለት ነው:: ከተባረኩ ቅዱሳት አንስት ትልቁን ሥፍራ ትይዛለች:: ማን እንደ እርሷ !

ቅድስት ኢላርያ ማለት :-

- የታላቁ ንጉሠ ነገሠት: የደጉ ዘይኑን [Emperor Zenon] የበክር ልጅ
- በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደች
- ትምሕርተ ሃይማኖትን: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተማረች
- ምድራዊ ንግሥናን ንቃ ፍቅረ ክርስቶስን የመረጠች
- የአባቷን ቤተ መንግስት ትታ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ [ገዳመ አስቄጥስ] የወረደች:
- ስሟን ከኢላርያ ወደ ኢላርዮን ቀይራ በወንዶች ገዳም የመነኮሰች
- ራሷን በፍጹም ገድል ቀጥቅጣ ከወንዶቹ በላይ በሞገስ ከፍ ከፍ ያለች
- ትንሽ እህቷን ጨምሮ በርካቶችን የፈወሰች
- በእርሷ ምክንያት ለግብጽና በመላው ዓለም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ ቸርነት በዘይኑን የተደረገላት ታላቅ እናት ናት::

ቅድስት ኢላርያ ማንም ሴት መሆኗን ሳያውቅባት: አባ ኢላርዮን እንደ ተባለች በዚህች ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያንም እነሆ ላለፉት ፩ ሺህ ፬ መቶ [1,400] ዓመታት: ቅድስቲቱንና የተባረከ አባቷን ዘይኑንን: ስለ በጐነታቸውና ውለታቸው ታስባቸዋለች::

† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: †

[  † ጥር ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት  ]

፩. በዓለ አስተርዕዮ ማርያም [እመቤታችን ከእረፍቱዋ በሁዋላ ለደቀ መዛሙርት በዚሁ ቀን ተገልጣ ነበር]
፪. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ [ታላቅ ሊቅና ጻድቅ]
፫. ቅድስት ኢላርያ እናታችን [የዘይኑን ንጉሥ ልጅ]
፬. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፮. ቅዱስ ኒቆላዎስ ሰማዕት
፯. አባ ፊቅጦር

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. አባ ምዕመነ ድንግል
፪. አባ አምደ ሥላሴ
፫. አባ አሮን ሶርያዊ
፬. አባ መርትያኖስ
፭. አበው ጎርጎርዮሳት

" ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን:: እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን:: አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ:: አንተና የመቅደስህ ታቦት:: ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ:: ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው:: ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት. . ." [መዝ.፻፴፩፥፯]

" ወዳጄ ሆይ ! ተነሺ:: ውበቴ ሆይ ! ነዪ:: በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና: መልክሽን አሳዪኝ:: ድምጽሽንም አሰሚኝ:: " [መኃ.፪፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏2👍1

tgoop.com/Enatachn_mareyam/16352
Create:
Last Update:

BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16352

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

bank east asia october 20 kowloon The channel also called on people to turn out for illegal assemblies and listed the things that participants should bring along with them, showing prior planning was in the works for riots. The messages also incited people to hurl toxic gas bombs at police and MTR stations, he added. Telegram users themselves will be able to flag and report potentially false content. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. Just as the Bitcoin turmoil continues, crypto traders have taken to Telegram to voice their feelings. Crypto investors can reduce their anxiety about losses by joining the “Bear Market Screaming Therapy Group” on Telegram.
from us

Telegram አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
FROM American