tgoop.com/Enatachn_mareyam/16340
Last Update:
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ ስድስት ]
🕊
[ ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ትርጉም ተናገረ ! ]
🕊
❝ ጥቂት አኃው በአባ መቃርዮስ ዙሪያ ተቀምጠው ፦ ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ትርጉም ንገረን ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ ነገራቸው ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት ከመንፈሳችን ጋር ልትነጻጸር ትችላለች ፣ አንድ ሰው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውቀት ገንዘብ ካደረገ መንፈሱ ብሩህና የተመጠነ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት የተመጠነና የተቀመመ እንደ ሆነ ሁሉ እንደዚሁም መምህሩም ነገሩ የተቀመመና መረዳቱም ብልህ ነው ይባላል” አለ፡፡
አኃውም ፦ “ማደግ ምንድን ነው ? የእኛ ቅጠሎችስ ምንድን ናቸው?” አሉት፡፡
አባ መቃርዮስም እንዲህ አላቸው ፦ “ዕድገት መንፈሳዊ የመልካም ተጋድሎ ሕይወቶች ናቸው ፤ ቅጠሎች ደግሞ የዋሃንና ንጹሐን የሆኑት ሰዎች ናቸው፡፡ ዛፍ ሲኖር የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቹ ጎጇቸውን ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡ እኛም ሰማያውያን ሰማያውያን ዛፎች ለመገኘት እንድንችል እንሁን !
ዛፉ የሚያስተምረው መምህር ነው ፤ ለተማሪዎቹ የሚሰጣቸው ትምህርቶችና ማበረታቻዎች ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት ውስጧ [ልቧ] አንድ ነው ፤ ወንድሞቼ ሆይ ፦ በሦስት መሥፈሪያ የሰወርነውን እርሾ ማለትም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ እንቀበል ዘንድ እኛም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ልባችን አንድ ይሁን፡፡
ሦስት መሥፈሪያ የተባሉም ሥጋ ፣ ነፍስና መንፈስ ናቸው፡፡ሦስቱ መሥሪያዎች አንድን ሙሉና ፍጹም ሰው የሚያስገኙ ፣ የክርስቶስ ሙላት ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ ለመድረስ መለኪያዎች ናቸው፡፡
አኃውም እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በአእምሮው ርቀትና አስተዋይነት ተገረሙ ፣ ልቡናቸውም ታደሰ ፣ “ከማሰቤ የተነሣ እሳት ነደደ” [መዝ.፴፰፥፫] የተባለውም ተፈጸመ፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16340