tgoop.com/Enatachn_mareyam/16232
Last Update:
🕊 💖 🕊
[ ❝ ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት ❞ ]
🕊 💖 🕊
❝ የሐዲስ ኪዳኑ ታላቅ ሰርግ የተፈጸመባት ሰርግ ቤት በቃና ዘገሊላ የታደመችው እመቤታችን ናት፡፡ ይህቺን የሰርግ ቤት ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ፦ ❝ ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት። ❞ በማለት ሲያመሰግናት አባ ሕርያቆስ ደግሞ በቅዳሴው ፦ ❝ የሚልክያስ ንጹሕ አዳራሽ ❞ በማለት በ ታላቅ አዳራሽ መስሎ ይገልጻታል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ስለ ጌታችን ፦ ❝ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል። ❞ በማለት እልፍኝ ከተባለችው እናቱ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ [ ውዳ.ማር ፤ ቅዳ.ማር. ፤ መዝ.፲፰፥፭ ]
❝ ሰርግ ቤት ❞ በተሰኘችው እመቤታችን በሰርግ ቤት ውስጥ የሚከናወኑ አራት ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡
❝ በሰርግ ቤት ውስጥ ሙሽራውና ሙሽሪቱ አንድ ሆነው እንደሚዋሐዱ በእመቤታችን ውስጥም መለኮትና ሥጋ አንድ ሆነዋል፡፡ በሰርግ ቤት የሙሽራውና የሙሽሪት ዘመዶች አንድ ቤተሰብ እንደሚሆኑ በእመቤታችን ማኅጸን በተፈጸመው የአምላክና ሰው ተዋሕዶ ምክንያት ሰውና መላእክት ፤ ነፍስና ስጋ ፤ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ሆነዋል፡፡
በሰርግ ቤት መብልና መጠጥ እንደሚቀርብ በእርስዋ በተደረገው ተዋህዶ ምክንያት ሥጋወደሙ ለሁላችን ማዕድ ሆኖ ተሰጥቷል፡፡
በሰርግ ቤት ዘፈንና ጨዋታ እንዳለ ደግሞ ሁሉን የሚያስደስቱ ታላላቅ ተአምራት በአምላክ ሰው መሆን ምክንያት ታይተዋል፡፡ ❞ [ ውዳ.ማር.ትር.ገጽ ፶፪ ]
[ ቃና ዘገሊላ ]
† † †
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16232