tgoop.com/Enatachn_mareyam/16192
Last Update:
🕊
[ 🕊 ዕ ለ ተ ከ ተ ራ ! 🕊 ]
💖
እንኳን ለከተራ ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
🕊 💖 🕊
[ ከተራ ምን ማለት ነው ? ]
“ ከተራ” ከተረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “ከተረ” ፣ ወሃ ገደበ፣ ውሃ አገደ፣ ውሃ ዘጋ በማለት ወደ አማርኛ ተርጉመውታል ።
ታዲያ በየአመቱ ጥር ፲ [ 10 ] የጥምቀት ዋዜማ ዕለት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት ቀደም ብለው የቤት ክህነት አገልጋዮች ተሰባስበው ጊዜዊ ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ በመቆፈር ወይም በአቅራቢያቸው ያለውን ጅረት በመገደብ ለሚቀጥለው ጥር ፲፩ [ 11 ] የጥምቀትን ክብረ በዓል ለማክበር የሚሰበሰቡት ምዕመናን እንዲጠመቁ የመጠመቂያ ስፋራ የሚያዘጋጁበት ዕለት ነው።
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ዳስ ወይም ድንኳን ጥለው ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ።
ቅዱሳን አባቶቻችንም በየአመቱ በከተራ ዕለት በዚሁ በአዘጋጁት የመጠመቂያ ስፍራ አጠገብ በጣሉት ጊዚያዊ ዳስ ወይም ድንኳን ውስጥ አንድ ላይ ተሰባስበው እየጸለዩ በማደር እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ “የታቦት መኖር የእኔ ከአናንተ ጋር የመኖሬ ምልክት ነው” ብሎ የገለጸለትን ቃል ይፈጽማሉ።
የተባረከ ዕለተ ከተራ [ የጥምቀት ዋዜማ ] ይሁንላችሁ።
† † †
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16192