tgoop.com/Enatachn_mareyam/16188
Last Update:
#ጥር 10 #የከተራ_በአል
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አመታዊ የከተራ በአል እንኳን አደረሰን
👉ከተራ ምንድን ነው? ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ ሲሆን ፍችው ውኃ መከተር መገደብ ማለት ነው፡፡
👉በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ
👉ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ ይገድባሉ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ ለጥር 11ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
👉በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
👉በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው
👉ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከጥምቀት ከተራ በአል ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን"
#_መልካም__በዓል🙏
ለመቀላቀል👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16188