tgoop.com/ETHYWCA/1040
Create:
Last Update:
Last Update:
የበጎ ፈቃደኝነት ጽንሰ ሀሳብ አዲስ በነበረብት እንዲሁም የሴቶችን ነባራዊ ችግር ወደ ፊት ማውጣት ከባድ በነበረበት ወቅት በ1953 ተመስርቶ የነበረውን ወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያን እንቅስቂሴ እ.ኤ.አ በ2000ዓ.ም ተረክበው ካስቀጠሉ ጥቂት ልበ ሙሉ ጠንካራ ሴቶች እንዷ የነበሩት ወ/ሮ እሌኒ መኩሪያ፤ ወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በሰፊው እንቅስቃሴ ያደርግ በነበረብት ወቅት የድርጅቱ ሰራተኛ በመሆን ያላቸውን እውቀት በማበርከት እንዲሁም የቦርድ አባል በመሆን ድርጅቱን የደገፉ አንጋፋና ድንቅ የወ.ሴ.ክ.ማ ቤተሰብ ነበሩ፡፡ ወ/ሮ እሌኔ መኩሪያ በኖሩበት የትውልድ ቅብብሎሽ ሁሉ ያላቸውን እውቀት በማስተላለፍ እና ጊዜያቸውን በመስጠት ወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር ዛሬ የደረሰበት ቦታ እንዲደርስ ጉልህ ሚና አበርክተዋል፤ በዚህም ማህበራችን ሁሌም ሲያስባቸው ይኖራል፡፡ የወ.ሴ.ክ.ማ አባላት፣ ቦርድ፣ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም መላው የወ.ሴ.ክ.ማ ሰራተኞች በወ/ሮ እሌኒ መኩሪያ ዜና እረፍት የተስማንን ከፍተኛ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡
BY YWCA in Ethiopia

Share with your friend now:
tgoop.com/ETHYWCA/1040