tgoop.com/Dreyob/6831
Last Update:
ሰዎችን አስደሳች የመሆንን ዝንባሌ መገንዘብ (የመፍትሄ ሃሳቦች)
በትናንትናው ፖስቴ ላቀረብኩት ሰውን ለማስደሰት የመታገል ችግር መፍትሄ የሚሆኑ የተወሰኑ መመሪያዎችን አቀርለሁ፡፡
ለምንድን ነው ሰዎችን ለማስደሰት የምንታገለው?
1. ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እኛ ሃላፊነት የመውሰድ ዝንባሌ
• ይህ ዝንባሌ እያየንና እየሰማን ካደግነው ባህላዊ ሁኔታ ወይም ከእምነት አስተምህሮ ሊመጣ ይችላል፡፡
• ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት መንስኤው እኛ ሆንም አልሆንም ለራሳቸው ስሜት ሃላፊነት መውሰድ ያለባቸው እነሱ ናቸው፡፡
• የእኛ ሃላፊነት ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ሚዛናዊ መሆንና ስህተት ሲከሰት የእርማት እርምጃዎችን መውሰድ ነው፡፡
2. ከአንድ ከራሳችን ሁኔታ አንጻርና ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚመጣ የዝቅተኝነት ስሜት
• ይህ ዝንባሌ የእኛን አመጣጥም ሆነ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ሰዎች ያስባሉ ብለን ከምንገምተውና ከምናስበው ሊመጣ ይችላል፡፡
• ሰዎች ምንም አሰቡ ምንም፣ ዋናውና ወሳኙ ነገር እኛ በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት የማስተካከካላችን ጉዳይ ነው፡፡
• መለወጥ የምንፈልገውንና የምንችለውን መለወጥ፣ የማንችለውን ነገር ደግሞ ተቀብሎ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡
3. ማንም ሰው በእኔ ሊከፋ አይገባውም የሚል ምልከታና ፍርሃት
• ይህ ዝንባሌ “ባለስልጣኑ” ብዙ በሆነበት ቤት ውስጥ ከማደግና ሁሉም ለሚያሳየን ኃይለኛነትና ትእዛዝ ትክክለኛውን ምላሽ ለመስጠት ሲታገሉ ከማደግ ሊመጣ ይችላል፡፡
• ለህልውናችን በሌሎ ሰዎች ላይ የተደገፍንባቸው አመታት እያለፉ ሲመጡ ራሳችንን በመቻል ያመንንበትን ነገር ማድረግ እንደምንችል ራሳችን ወደማሳመን ማደግ አስፈላጊ ነው፡፡
• ሰዎች በእኛ ሲከፉ ሊያደርጉብን ወይም ሊከለክሉን ከሚችሏቸው ነገሮች ይልቅ እኛ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የምናደርገው ጥረት የበለጠ ጎጂ እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
4. ከዚህ በፊት ከደረብን የመገፋት ህመም ለመውጣት አለመፈለግ ወይም አለመቻል
• ይህ ዝንባሌ ለደረሰብን የመገፋት ስብራት ትክክለኛው መፍትሄ ምን እንደሆነ ካለማወቅ ሊመጣ ይችላል፡፡
• ሰዎች ከሚያደርሱበትን ማንኛውም አይነት ከአቅማችን በላይ የሆነ ጉዳትና ችግር ለመውጣት ሊያግዘን የሚችል ሌላ ሰው ማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡
• ካለፈው መማር፣ ሰዎችን ይቅር ማለትና መለወጥ እንደምንችል አምኖ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡
5. የግል የቀይ መስመር (personal boundary) በማስመር ደረጃ በእውቀት አለመኖር
• ይህ ዝንባሌ የሚመጣው በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት ካለመብሰል ነው፡፡
• ከሰዎች ጋር የምናደርጋቸው የግንኙነት ልውውጦች አንድ ወጥ ስሌት እንደሌላቸውና ሁኔታዊ እንደሆኑ ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡
• ይህንን ሁኔታ መስመር ለማስያዝ የራስን ስሜት መገንዘብና አያያዙን ማወቅ፣ እንዲሁም የሌላውን ሰው ስሜት መገንዘብና አያያዙን ማወቅን ይጠይቃል፡፡
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
BY Dr. Eyob Mamo

Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/6831