tgoop.com/Dreyob/6803
Last Update:
የጊዜ አጠቃቀም ችግር መነሻዎች
የጊዜ አጠቃቀማችሁ ለዘመኑ የሚመጥን መሆኑን እርግጠኞ ሁኑ፡፡ ያንን ካላደረጋችሁ ቀስ በቀስ ኋላ ቀር ወደመሆን ትንሸራተታላቸሁ፡፡ ገንዘብን መክሰር፣ ስራን በጊዜው አለመጨረስ፣ በሰዎችና በድርጅቶች ተፈላጊ አለመሆንና የመሳሰሉትን አጉል ውጤቶች መከተሉ ስለማይቀር ማለት ነው፡፡
⏱️ለውጥን ለማግኘት ከፈለጋችሁ በቅድሚያ ያንን ተጽእኖ ያመጣባችሁ ምን እንደሆነ ለመለየት ሞክሩ፡፡
⏱️አንዳንዶቻችን ያደግንበት ቤት ምንም አይነት ወጥ የሆነ የጊዜ ሂደት መሳሌነት ያላየንበት ቤት ነው፡፡
⏱️አንዳንዶቻችን የትኩረት ችግር ይኖርብን ይሆናል፡፡
⏱️አንዳንዶቻችን ካለብን የስሜት ቀውስ የተነሳ ይሆናል ጊዜያችንን የማናደራጀው፡፡
ችግራችሁን ለመለየትና መፍትሄውን ለማግኘት የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷልና ተጠቀሙበት፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!
BY Dr. Eyob Mamo

Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/6803