Telegram Web
“ፌሚኒዝም እና ክርስትና ሊቃረን ይችላል.. ከተቃረነም ያው ወይ ክርስትናን አልያም ፌሚኒዝምን እንመርጣለን የሚጠቅመንን..”

ይሄንን ንግግር አንዲት ፌሚኒስት ስትናገረው ሰማሁ እና እንዴት ታዩታላችሁ ንግግሩን😁😁 ወይ ፌሚኒዝምን ወይ ክርስትናን ምረጪ መባል ሊጀምር ነው በግልጽ.. አይ ቀልድ😁😁
413🤣127😢95😁20😱11👏8🔥7
“ወንዶች አትግደሉን..??”

ፌሚኒስቶች እባካችሁን እህቶችን በዘላለም ሞት አትግደሏቸው..
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
586👍68🤔23👏17🤣8
ሐዋ 3 (ሙሉዋን)

- ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ወደ ወቅደስ ሲወጡ ምጽዋት እየለመነ የሚቀመጥን አንድ አንካሳ ያገኛሉ.. እርሱም ከእነርሱ ምጽዋትን ሲጠብቅ እነርሱ ግን በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈወሱት

- ጴጥሮስ ይህ ተአምር በኢየሱስ ስም እንደሆነና እርሱ በግፍ ቢገደልም ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁም በነቢያት የተመሠከረለትም እርሱ እንደሆነ.. ስለዚህም ንስሐ ገብተው ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ይሰብካቸዋል።

@Apostolic_Answers
769🙏70🥰22👍10😱1
ጌታ ይመስገን ደስ የሚል ጊዜ ነበረን
ላይቭ ላይ..

እና ብዙ ጊዜ ከክርስቲያኖች ጋር እንዲ ስማማር ውስጤ በማልገልጸው ዓይነት ደስ በሚል ስሜት ነው ሚሞላብኝ የምር
941👍52🥰44🙏25🔥10👏10😱5🙈3
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን:

ሐዋ ሥራ - 4:1-22

- እነ ጴጥሮስ በጌታ ኢየሱስ በኩል ስላልለው ስለ ትንሣኤ ሙታን እና እንደ አጠቃላይ ጌታችን ኢየሱስን ስለሰበኩ የአይሁድ የካህናት አለቆችና ሰዱቃውያኑ ተባብረው ወኅኒ ቤት አሰደሯቸው.. ብዙዎች ግን አመኑ

- በነገታውም በሸንጎ መሃል አቁመዋቸው ያንን አንካሳ ሰው በምን ኃይል ወይም በማን ስም እንደፈወሱት ጠየቋቸው..

- እነ ጴጥሮስም መሰከሩ ከጌታ ኢየሱስ በቀር ሌላ በማንም መዳን እንደሌለ..

- በግልጥ ሲሰብኩ የሚታዩ ምልክቶችን እንደሚያደርጉ ባስተዋሉ ጊዜ ስለ ኢየሱስ እንዳይሰብኩ አዘዟቸው..

- ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ግን: “እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” እያሉ ይመልሱላቸው ነበር..

- እነ ጴጥሮስን ለጊዜው ከእሥር ፈቷቸው

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
737🙏76🥰33👍13🔥8👏2😱2
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንበብ

ሐዋ 4: 23-ፍጻሜ

- እነ ጴጥሮስ ከእሥር ከወጡ በኋላ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሌሎች ነገሯቸው..

- ሌሎችም በአንድ ልብ ሆነው ጸለዩ.. ሲጸልዩም ቤቱ ተናወጠ ሁሉምም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ..

- አማኞች ገንዘቦቻቸውን ሁሉ በአንድነት እየሰበሰቡ በጋራ ይጠቀሙት ነበር.. የኔ የአንተ የሚባል ነገር አልነበረም.. ሐዋርያቱም የኢየሱስን ትንሳኤ ከታላቅ ጸጋ ጋር በግልጥ ይሰብኩ ነበር..

- ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ በሐዋርያቱ በርናባስ(የመጽናናት ልጅ) ተባለ.. እርሻ ነበረው ሸጦ ከሐዋርያት እግር ሥር አስቀመጠው..

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
647🙏90👍14👏11
ዝማሬዎችን አብረን እየሰማን አብረን ሪያክት እንድናደርግ አስቤ የከፈትኩት ዩትዩብ ቻናል ነው.. እስቲ ሊንኳን ተጭነው subscribe የምትለዋን ተጭነው ይውጡ😁😁

መጀመሪያ ሪያክት የማደርገው “ነገር ግን ሁሉም ይሰድበኛል” በሚለው ይመስለኛል ሎል
👇👇

https://www.youtube.com/@ሐዋርያዊ_መልሶች_Reaction
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
424😁108🤣44🥰13👍9🤔3
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ ሥራ 5 (ሙሉዋን)

ጠቅለል ያለው አሳቡ ይሄ ነው.. መሃል ላይ “ሐዋርያትን ከወኅኒ ቤት አስመጧቸው” የሚለውን ከመቅደስ አስመጧቸው በሚለው ይስተካከል😁😁

@Apostolic_Answers
673🙏79👍25🥰14🔥12😱3👏2😁2
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ ሥራ 6 (ሙሉዋን)

@Apostolic_Answers
598🙏49👍19🥰15👏14🔥4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድቅድቅ ጨለማ😆😆

ይቅርታ ወዳጆቹ ሎል

መዘመሩን ተወውና ከዛሬ በኋላ እንዳትሰማ ራሱ😁😁
🤣88973😁57🙈20🤔17😢6
"በዓለም ውስጥ ብዙዎች ተሰቅለው አልፈዋል ሰይጣን ግን በአንዳቸውም የደነገጠ አይደለም። ታድያ ግን ስለ እኛ የተሰቀለውን የክርስቶስን የመስቀሉን ምልክት እንኳ ገና ሲያይ ይንቀጠቀጣል።"

[ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፡ Catechetical Lecture 13፡ 3]

@Apostolic_Answers
1.22K🙏81🔥32🥰28👍26🤣5
ዛሬ በጌታ ቀን..

ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

መልካም የጌታ ቀን
824🙏102🥰28👍18🤣4
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ - 7(ሙሉውን)

@Apostolic_Answers
470🙏47🥰21👍18👏1
ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ:-

"... አቤቱ ጌታ ሆይ ይህ የሚያረጅ የሚጠፋ የተስፋ አለም ለኛ ለክርስቲያን ህዝቦችህ አይደለም ፤ ነገር ግን የሚመጣውን አለም ተስፋ እናደርጋለን እንጠብቃለንም..."
____________________

የቤተ ክርስቲያንን አምልኮ ለማወቅና ለመውደድ ከዛም በፍቅርና በእውቀት ለመሳተፍ ከታች የማስቀምጠውን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇👇

@Amlake_Birhan

👆👆👆👆
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
480🥰30🔥11👍10👏4😢1
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ ሥራ - 8:1-25

- እስጢፋኖስን በታላቅ ለቅሶ ቀበሩት.. በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ላይም በዛ ሰዓት ትልቅ ስደት ሆነ..

- ከሐዋርያት በቀር ብዙዎችም ወደ ሰማርያ እና ይሁዳ አገሮች ተበተኑ.. ጳውሎስ(ሳውል) ግን ክርስቲያኖችን ያሳድድ ነበር ከቤትም ድረስ እየጎተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባ ነበር..

- ወደ ሰማርያ ከተበተኑት ውስጥ ፊልጶስ በዛው ክርስቶስን ለሕዝቡ ይሰብክ ነበር ብዙ ምልክትና ተአምር ይታይ ነበርና ብዙዎች እያመኑ ተጠመቁ.. ሲሞን የሚሉት በሃገሪቱ የታወቀ ጠንቋይም አመነ..

- ሐዋርያት ከኢየሩሳሌም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ሰማርያ ላኩላቸው እና ለተጠመቁት ሰዎችም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይቀበሉ ዘንድ በአንብሮተ እድ ጸለዩላቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ..

- ጠንቋይ የነበረው ሲሞን ግን በሐዋርያት እጅ በመጫን የሚሰጠውን ጸጋ ባየ ጊዜ ገንዘብን ሰብስቦ አመጣና ለእኔም እንደ እናንተ ሥልጣን ይሰጠኝ አለ.. ጴጥሮስ ግን የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት ስለመፈለጉ ገሰጸው በንስሐም እንዲመለስ መከረው..

- ሐዋርያቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ.. ለሳምራውያን(በሰማርያ ላሉ) ግን ወንጌል በሰፊው ተሰበከ

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
684🙏79🥰28👍20🔥4👏2😱1
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ 8:26-ፍጻሜ

- የጌታ መልአክ ፊልጶስን ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያስወስደው ምድረ በደ ሂድ አለው..

- በዛም አንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጠንና ጃንደረባ የሆነ ሰው በሰረገላ ተቀምጦ ያይና መንፈስም ሄዶ እንዲያናግረው ያዘዋል

- ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰረገላው ላይ ሆኖ የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር.. እናም ፊልጶስ ቀርቦ “ምታነበውን ታስተውለዋለህን?” ብሎ ጠየቀው.. ጃንደረባውም የሚመራው ሳይኖር ሊረዳው እንደማይችል በመመስከር እንዲያብራራለት ፊልጶስን ለመነው..

- ያነበው የነበረው የኢሳይያስ መጽሐፍ ክፍል እንዲህ ይል ነበር: “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።”

- ፊልጶስም ከዚህ መጽሐፍ ጀምሮ ወንጌልን ሰበከለት.. ወኃ ጋርም በደረሱ ጊዜ ኢትዮጵያዊው ጀንደረባ “እነሆ ወኃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?” በማለት በፊልጶስ ኢየሱስ የ እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ ተጠመቀ..

- ከዚያም ፊልጶስ ተነጠቀ ወደ ቂሣርያም እስኪደርስ ድረስ እየዞረ ወንጌልን ሰበከ

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
731🙏92🥰16👍13🤣3
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን:

ሐዋ 9:1-19

አሳዳጁ ሳውል(ጳውሎስ) ክርስትናን ተቀበለ

@Apostolic_Answers
518🙏63🥰22👍17
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን:

ሐዋ 9:20-ፍጻሜ

- ሳውል ወዲያው ገና እዛው በደማስቆ ሳለ በምኩራቦች ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መልስ እስኪያጡ ድረስ ይሰብክ ጀመረ.. ሕዝቡም ደግሞ ይህ አሳዳጁ አይደለምን እያሉ ተገረሙ

- ሳውልን አይሁድ ሊገድሉት ፈልገው በከተማዋ በሮች ላይ ሁሉ ጥበቃ ቆሙ ክርስቲያኖች ግን ሳውልን በሌሊት በአጥር ላይ በቅርጫት አድርገው አወረዱት

- ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ክርስቲያኖች ከእርኡ ጋር ይተባበሩ ዘንድ ፈሩ.. በርናባስ ግን ወደ ሐዋርያት አስገባውና ስለ ሳውል የተፈጠረውን ሁሉ ጌታ እንዳገኘውም ተረከላቸው..

- ሳውል በዛ በኢየሩሳሌም በኢየሱስ ስም ያስተምር ነበር.. እዚህም ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ሳውን ወደ ቂሣሪያ ወሰዱት ከዛም ደግሞ ወደ ትውልድ ሃገሩ ወደ ጠርሴስ ይሰዱታል..

- ጴጥሮስ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሲጓዝ ወደ ልዳ ሄደ.. በዛም ኤንያ የሚሉትም ለ8 ዓመት ሽባ ሆኖ አልጋ ላይ የተኘውን ሰውን ፈወሰው..

- ለልዳ ቅርብ በሆነችው በኢዮጴም ደግ የሆነች ጣቢታ የሚሏት ዶርቃ የተባለች ሴት ሞተች.. በዛም የሚኖሩት ከልዳ ጴጥሮስን አስጠሩት እርሱም ገብቶ ጸለየላት ተነሣችም

- በኢዮጴ በርካታ ሰዎች በጌታ ያምኑ ጀመር.. ጴጥሮስም በዛው ስምዖን ከሚሉት ቁርበት ፋቂ ሰው ቤት ብዙ ቀን ተቀመጠ..

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
567🙏82🥰13🔥3😱2
“የሚመካ ግን በጌታ ይመካ”

[2ኛ ቆሮንቶስ 10: 17]
777🙏99👍25🔥19🥰13
2025/10/09 06:44:20
Back to Top
HTML Embed Code: