Telegram Web
ከተማ አቀፉ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፤ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ በገላን ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ፈተናውን በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል።

ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ሂደቱን የሚከታተል የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ከማዋቀር አንስቶ በቂ የፈተና አስፈጻሚዎች ተመልምለው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ተናግረዋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 6,828 ተማሪዎች በ24 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከተማ አቀፉን የ2017ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 71,972 ተማሪዎች በ194 የፈተና ጣቢያዎች የ2017ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው እና በቂ ፈታኞች፣ጣቢያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋር፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ እና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት በላይነሽ ዋቅጅራ እና የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ ዶክተር አያሌው ጥላሁን በጋራ በመሆን በቶፕ ቴን ሆቴል መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፦ አትሌት መሠረት ደፋር

ለሀገሯ ይህን ያክል ዋጋ የከፈለችው አትሌት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የገጠማትን ችግር ለመፍታት በፍርድ ቤት ስለመንከራተቷ በቅርበት አውቃለሁ ያለችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር፤ ሕግ ለዚህች የሀገር ባለውለታ ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ ብላለች።

መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ መሠረት ደፋር አሳስባለች።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፦ አትሌት መሠረት ደፋር ለሀገሯ ይህን ያክል ዋጋ የከፈለችው አትሌት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የገጠማትን ችግር ለመፍታት በፍርድ ቤት ስለመንከራተቷ በቅርበት አውቃለሁ ያለችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር፤ ሕግ ለዚህች የሀገር ባለውለታ ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ ብላለች።…
"ብዙ ገለቴዎች አሉን!"
- አትሌት ስለሺ ስህን
" ...ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ"
- አትሌት መሠረት ደፋር


#Ethiopia | የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ስለሺ ስህን "ገለቴ ቡርቃ አደባባይ ወጥታ ጉዳቷን ተናገረች እንጂ ሌሎች ተመሳሳይ በደል እየደረሰባቸው ያሉ አደጋ የደረሰባቸው ብዙ አትሌቶች አሉ" ሲል ተናግሯል።

ፕሬዝዳንቱ አክሎም "ፌደሬሽኑ ላለፉት 3 ወራት ይሄንን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን ስንሰራ ነበር። አሁን ላይ አትሌቶችን ከአደጋ የሚከላከል ኢንስቲቲዩት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን አቋቁመናል ሲል ፕሬዝዳንቱ ተናግሯል።

ብዙ የተጎዱ አትሌቶች አሉ። ብዙ ገለቴዎች አሉን። በወንዶች አትሌቶች ላይም ጭምር ነው አደጋው ያለው። ይሄንን ለማስቀረት እየሰራን ነው ብሏል።

እኛ እንደ ፌደሬሽን ከገለቴ ጎን መቆማችንን ለማሳወቅ እንወዳለን። ለሌሎች አትሌቶችም ከጎናቸው እንዳለን የኢትዮጲያ ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን" ብለዋል።

አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፦ አትሌት መሠረት ደፋር

ለሀገሯ ይህን ያክል ዋጋ የከፈለችው አትሌት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የገጠማትን ችግር ለመፍታት በፍርድ ቤት ስለመንከራተቷ በቅርበት አውቃለሁ ያለችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር፤ ሕግ ለዚህች የሀገር ባለውለታ ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ ብላለች።

መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ መሠረት ደፋር አሳስባለች።

@Yenetube @Fikerassefa
የፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀረበ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዳቀረቡት ከ2018 ረቂቅ በጀት 1.2 ትሪሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 415 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊዮን ብር ለክልል መንግስታት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ የሚውል ነው።

ከረቂቅ በጀቱ 1 ትሪሊዮን ብር ወይም 73 በመቶውን ከታክስ ገቢ 236 ቢሊዮን ብር ከልማት አጋሮች ቀሪውን ደግሞ ከፕሮጀክቶች ድጋፍ እና ልዩ ልዩ ገቢዎች ለማግኘት መታቀዱን ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰላም

የቻናላችን ቤተሰቦች የጋርመንት( Men Boxer ) በማምረት ዘርፍ የተሰማራቹ እንዲሁም Boxer ጨርቅ አቅራቢዎች በውስጥ መስመር አውሩን።

@Fikerassefa
ህወሓትን በመቃወም የትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ፤ በ #አፋር እና በ #ትግራይ ክልሎች ውስጥ “አራት ክፍለ ጦር” ያለው የራሳቸውን ሠራዊት ማደራጀታቸውን ተናገሩ።

#ከትግራይ ኃይሎች በመለየት የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር፤ "አዲስ ነገር ለመፍጠር" ወደ በረሃ መውደረዳቸውን እና "ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣... ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር" እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።

ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የሠራዊቱ አመራሮች ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነን እና ሌሎች የሠራዊቱን ውሳኔ የተቃወሙትን ማገዳቸው ይታወሳል።

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር "ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም" ብለዋል።

ለተቃውሟቸው ጠመንጃ ማንሳትን መምረጣቸው በጦርነት ውስጥ የቆየውን የትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግጭት አዙሪት አይከተውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ጄነራሉ "እኔ ኢንተርናሽናል ጄነራል ነኝ። ይህንን ሆኜ የህወሓት ሚሊሻ መሆን አልፈልግም። ህወሓት ፓርቲያችን ነው የሚሉ የእርሱን ሚሊሻ እንደሆኑ ነው የሚቆጥረው። ሚሊሻነትን ደግሞ አልቀበልም" ብለዋል።

@Yenetube
በዲላ ከተማ የፖራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መዉጫ ፈተና አለመዉሰዳቸዉን ተናገሩ

ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸዉን የገለፁ በዲላ ከተማ የፖራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ተፈታኝ ተማሪዎች እንደተናገሩት ከሆነ ፈተናዉን ለመዉሰድ አምና ጥር ወር ላይ 500 ብር ከፍለዉ እንደነበር ገልፀዋል ።

ባልታወቀ ምክንያት ፈተናዉ መቅረቱንና በቀጣይ ትፈተናላችሁ ተብለዉ በዚህ አመት ለፈተናዉ 200 ብር እንዲጨምሩ ብሎም ባሳለፍነዉ እሁድ የመፈተኛ ሚስጥራዊ እና መለያ ቁጥር እንዲወስዱ እንደተነገራቸው ተናግረዋል፡፡ ተፈታኞቹ ትምህርቱን ሲከታተሉ የነበረዉ በቅዳሜና እሁድ መርሃግብር ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ መሆናቸዉንም ገልጸዋል ።

ከያሉበት አከባቢ ፈተናዉን ለመዉሰድ ከፍተኛ ወጪ አዉጥተዉ መምጣታቸዉንና በተባሉት መሠረት እሁድ ሚስጥራዊ እና መለያ ቁጥር ለመዉሰድ ወደ ተቋሙ ሲያመሩ የሚያናግራቸዉ አንድም አካል አለማግኘታቸዉን ተናግረዋል ።ብስራት ሬዲዮ ጉዳዩን ለማጣራት የተቋሙን አመራሮች የናገረ ሲሆን ፈተናዉን ለመዉሰድ ከትምህርት ሚኒስቴር የፋይዳ መታወቂያ አስፈላጊ መሆኑ በተላለፈዉ መመሪያ መሠረት በጊዜዉ ያላቀረቡ ተማሪዎች በመኖራቸዉ ፈተናዉ ለቀጣይ አመት መተላለፉን ተናግረዋል ።

አክለዉም ተማሪዎቹን ለፈተና በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀታቸውን አብዛኞቹ ተማሪዎችም የተባሉትን የፋይዳ ቁጥር በጊዜዉ መላካቸዉን ገልፀው እንዲፈተኑም ጥሪ ማቅረባቸዉን ክፍያዉንም እንዲከፍሉ ማድረጋቸዉንና ባለቀ ሰዓት ይህ ክስተት መፈጠሩን አስረድተዋል ። ተፈታኞቹም ይህ መልዕክት የተነገራቸዉ ፈተናዉን ለመዉሰድ ከያሉበት አከባቢ ወደ ከተማዋ ገብተዉ ፈተናዉ አንድ ቀን ሲቀረዉ መሆኑን ገልፀዋል ። የፋይዳ መታወቂያ በተባልነዉ ጊዜ ያቀረብን ተማሪዎች ያለ በቂ ምክንያት በዚህ ዓመት አለመፈተናችን ቅሬታ ፈጥሮብናል ሲሉ ተናግረዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ኢሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል።

በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተገንዝቧል።

ተስፋለም የመጀመሪያውን ሌሊት ካሳለፈበት እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ትላንት ሰኞ ሰኔ 2 ቀን፤ 2017 ቄራ አካባቢ ወደሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ተዘዋውሯል።

ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርቦ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወስኖ ነበር። ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተስፋለም የጠየቀውን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ተስፋለም “ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” እንደተጠረጠረ ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ በሰጠበት ደብዳቤ ላይ ሠፍሯል። የተስፋለም የዋስትና መብት እንዲከበር ከተሰጠው ትዕዛዝ በኋላ መርማሪ ፖሊስ በቃል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። ይሁንና እስካሁን በይፋ ፍርድ ቤት ይግባኝ አልጠየቀም።

የተስፋለም ዋስትና እንዲከበር ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አስፈላጊውን ክፍያ ፈጽሞ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተጻፈው ደብዳቤ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረምበት ቀርቷል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
የኢትዮጵያ ኢሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል። በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ…
የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መታሰርን በተመለከተ ከሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ

በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል። በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተገንዝቧል።

ተስፋለም የመጀመሪያውን ሌሊት ካሳለፈበት እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ትላንት ሰኞ ሰኔ 2 ቀን፤ 2017 ቄራ አካባቢ ወደሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ተዘዋውሯል። ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርቦ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወስኖ ነበር። ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተስፋለም የጠየቀውን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ተስፋለም “ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” እንደተጠረጠረ ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ በሰጠበት ደብዳቤ ላይ ሠፍሯል። የተስፋለም የዋስትና መብት እንዲከበር ከተሰጠው ትዕዛዝ በኋላ መርማሪ ፖሊስ በቃል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። ይሁንና እስካሁን በይፋ ፍርድ ቤት ይግባኝ አልጠየቀም።

የተስፋለም ዋስትና እንዲከበር ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አስፈላጊውን ክፍያ ፈጽሞ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተጻፈው ደብዳቤ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረምበት ቀርቷል። በዚህም ምክንያት ይህ መግለጫ ይፋ እስከሆነበት ሰዓት ድረስ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በፍርድ ቤት የተረጋገጠለት የዋስትና መብት አልተከበረም።

ለጋዜጠኝነት ባለው ፅኑዕ ክብር እና ለሙያው ባለው ቁርጠኝነት የሚታወቀው ተስፋለም ዳግም በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መዋሉ የሥራ ባልደረቦቹን፣ ወዳጆቹን እና ቤተሰቦቹን በእጅጉ አሳስቧል። ተደጋጋሚ ችግሮች ቢገጥሙትም “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ባለፉት ዓመታት ነጻ እና ገለልተኛ የሆኑ፣ ከፍተኛ ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውን የጠበቁ ዘገባዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም ተዓማኒነት እና ተቀባይነትን እያፈራ የመጣ የበይነመረብ ሚዲያ ተቋም ነው።

ተቋማችን የዋና አዘጋጁ ተስፋለም ወልደየስ እስር በሚዲያው ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑን እየገለፀ፣ በአስቸኳይ ወደ ሥራው እንዲመለስ ጥሪውን ያቀርባል። በተጨማሪም፣ ጉዳዩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ተቋማችን ከፖሊስ እና ከፍርድ ቤት የሚያገኛቸውን መረጃዎች ለሚዲያው ቤተሰቦች ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጥንቃቄ ባሕር ዳር!

ባሕር ዳር የመጀመሪያው በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተጠቃ አንድ ሕፃን ልጅ ተገኝቷል። የምርመራ ናሙና ወደ አዲስ አበባ ተልኮ በተደረገው ምርመራ ውጤቱ የዝንጀሮ በፈንጣጣ መሆኑ ተረጋግጧል።

ስለሆነም ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርግ። በመንግሥት በኩል አሁንም መረጃዎች እንዳይወጡ ነው ጥረት እየተደረገ ያለው።
በጠቅላላ ሪፖርት ከተገለጸው ውጭ ቫይረሱ በአዲስ አበባ እና በባሕር ዳር ከተሞች መገኘቱን ይፋ ማድረግ አልተፈለገም ተብሏል!

@Yenetube @Fikerassefa
አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ

በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል።" ሲል አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
አቶ ታደለ ገብረመድህን በቁጥጥር ስር ዋለ !

አትሌት ገለቴ ቡርቃ "ዘርፎኛል "በሚል በሚዲያ የከሰሰችው  እና ብዙዎችን  ያሳዘነው የአትሌቷ ህይወት  በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ  የቀድሞው ባለቤቷ ታደለ ገብረመድህን  በቁጥጥር ስር ታውቋል

@Yenetube @Fikerassefa
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tgoop.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Forwarded from YeneTube
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
አዲሱ የትራንስፖርት ግብር አከፋፈል የዘርፉን አሰራር ያላገናዘበ በመሆኑ ወደነበረበት እንዲመለስ ተጠየቀ!

የትራንስፖርት ዘርፉ የግብር አከፋፈል ቀድሞ ከነበረበት የቁርጥ ክፍያ ተቀይሮ ገቢን መሠረት ባደረገ ተመን እንዲቀየር መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም አከፋፈል የዘርፉን አሰራር ያላገናዘበ በመሆኑ ወደነበረበት እንዲመለስ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ጠይቋል፡፡

አዲሱ አካሔድ የትራንስፖርት ዘርፉን አሰራር ያላገዘበ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ "ግብር ሰብሳቢው ተቋም ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳያገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ወደነበረበት የቁርጥ ክፍያ ሊመለስ ይገባል" ሲልም ነው ፌዴሬሽኑ የጠየቀው፡፡

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወርቅዓለማው ንጋቱ ለአሐዱ እንደገለጹት አዲሱ የትራንስፖርት ግብር አከፋፈል በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ደረሰኝ የማይቀርብባቸው በርካታ ክፍያዎች ስላሉ የአሰራር ክፍተት ይፈጥራል፡፡

"አሰራሩ ግብር ከፋዮች ተገቢውን ግብር እንዳይከፍሉ ያደርጋል" ያሉት ኃላፊው፤ "በየቦታው ከሚገኙ ኬላዎች ክፍያ ጀምሮ፣ የማደሪያ ቦታዎችና በገቢዎች ተቀባይነት የማይኖራቸው ጥቃቅን ክፍያዎች፣ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ካለው አለመረጋጋት እና ግጭት ጋር ሲደመር ደረሰኝ ለመስጠት የማይመቹ ናቸው" ብለዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ዘርፉ በሀገራዊ ሎጅስቲክስና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው እንደመሆኑ ያልተገባ የገንዘብና አስተዳደራዊ ሸክሞች ሳይኖሩበት፣ ተገቢውን የመንግሥት ግብር በአግባቡ እየከፈለ እንዲቀጥል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብቱ ተጠብቆ ከእሥር እንዲለቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አፀና።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን 2017 በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ወስኖ ነበር።ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ጋዜጠኛው ሳይፈታ ጉዳዩ ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ. ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ታይታል።

ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በዛሬ የችሎት ውሎ የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማጽናቱንና ጋዜጠኛው ከእሥር እንዲለቀቅ ወስኗል ሲሉ የተጠርጣሪው ጠበቃ ቤተማርያም ኃይሉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።ጠበቃው "ፖሊስ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ የተጠርጣሪውን በእሥር መቆየት የግድ የሚል ባለመሆኑ" በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው የዋስትና መብት እንዲፀና ወስኗል ሲሉም አክለው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ኢንሳይደር የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መሥራችና ዋና አዘጋጅ ተስፋለም ወልደየስ "ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት" ተጠርጥሮ እሑድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ኢትዮጵያ ኢንሳይደርን የሚያስተዳድረው ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ትናንት አስታውቋል።

አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ተስፋለም ዋልድየስን በአስቸኳይ ይፈቱ" ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው ገቡ!

ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱ ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው ገቡ። ዛሬ ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ሰያካሄዱት በትግራዩ ጦርነት ከምዕራብ ትግራይ እና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው።ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ መንግስት ወደቀዬአችን እንዲመልስን ብንጠይቅም ምላሽ አጥተናል ሲሉ በምሬት ገልፀዋል።ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት በፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት በራፍ ቆመው ምላሽ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ የቆዩ ተፈናቃዮቹ፥ ረፋዱ ላይ ነበር የክልሉን ፕሬዝዳንት ፅሕፈትቤት ግቢ ጥሰው የገቡት። ተፈናቃዮቹ "ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፥ ከዚህ አንወጣም" ሲሉም ተደምጠዋል ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
2025/06/16 02:37:07
Back to Top
HTML Embed Code: