Telegram Web
ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ

ኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

በ34ኛ ሳምንት የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባእንደርታ ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ መድን ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በተመለሰ በ2ኛ አመቱ ሊጉ ሊጠናቀቅ 3 ጨዋታ እየቀረው በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሳክቷል፡፡

ከአሁን በፊት ከጅማ አባጅፋር እና መቐለ ሰባእንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የመድን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ሻምፒዮን በመሆንም ታሪክ ሰርቷል፡፡

ኢትዮጵያ መድን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳ 10ኛው ክለብም ሆኗል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ

ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ፈተናው እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት እየተሰጠ ባለው የመውጫ ፈተና 190 ሺህ 787 ቅድመ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 102 ሺህ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የቤት ውስጥ ሰራተኞችን የሚመለከተው ኮንቬንሺን 189 እንዲፀደቅ ጥረት እያደረግን ነው ሲል አንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር አስታወቀ።

የአንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር የህብረቱ ፕረዝደንት ሒሩት አበራ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከፈረመች አመታት ቢቆጠሩም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ የቤት ሰራተቾች በማህበረ ተደራጅተው ስለመብቶቻቸው ያለመጠየቅ፣እንደ ማኒኛውም ሰራተኛ የሰራተኞችን መብት በሚያስጠብቀው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156 ውስጥ እንዲሁም በሌልች የህግ ማእቀፍ ውስጥ ያለመካተታቸውና ያለመጠየቃቸው እስካሁን አዋጁ ሳይፀድቅ ቆይቷል  ብለዋል።

ስለቤት ውስጥ  ሰራተኞች የሚያወሳውን አለም አቀፍ ስምምነት 189 ኮንቬንሺን ለምን አልተፈረመም ብለን ስንጠይቅም ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ነው ይባላል በህግ አውጪው በኩል ሲሉም አስረድተዋል። መመሪያው ፀድቆ በስራ ላይ ቢውል፣ የቤት ሰራተኞችን መሰረታዊ መብቶች የሚያስጠብቅ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚያስተካክልና የስራ ከባቢያቸውንም ምቹ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን፣ መመሪያውና የስራ ቅጥር ውሉ፣ የቤት ሰራተኞች ጉልበታቸው ሲደክም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡በአሁን ወቅት የቤት ሰራተኞች በስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚዋዋሉት ውል ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ሐላፊነትን የማይሰጥና መብትና ግዴታን የማይለይ ነው፡፡

ሆኖም ይህን ችግር ለመፍታት ነው ማህበሩ የተቋቋመው ያሉ ወ/ሮ ህሩት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከአራት አመታት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት፣ በሀገሪቱ ወደ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰራተኞች እንዳሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቷ፣ እነዚህ ዜጎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርሱባቸውም በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ 

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት ያስፈልጋል ተባለ

#ኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ገለጹ።

የገንዝብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

የምክር ቤት አባላቱ በሀገሪቱ ለተጀመሩት የመንገድ ፕሮጀክቶች ትልቅ ማነቆ የሆነውን በጀት መፍታት የሚያስችል የብድር ስምምነቶችን ገንዘብ ሚኒስቴር ሊያመጣ እንደሚገባ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ከአጋር የልማት ድርጅቶች ሀብት የማሰባሰብ ስራ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ በምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ከተለያዩ የብድር አቅራቢ ተቋማት በተገኘ ብድርና ከልማት አጋሮች በተገኘ ድጋፍ በርካታ መንገዶች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ሆኖም በምክር ቤቱ በቂ አይደለም የተባለውን በመውሰድ የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ እና ከልማት አጋሮች ሀብት ማሰባሰቡን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

አጠቃላይ እንደሀገር የተጀመሩትን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከአንድ ነጥብ ሶስት ትሪሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

ችግሩን ለመፍታት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን አንስተው፤ ዘርፉን ለማሳደግ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያስፈልጋል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ፤ ሌሎች አበዳሪ ተቋማት ከዚህ ቀደም ሲሰጡት የነበረውን ብድር ለማስቀጠል ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በማደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የግብርና መዋለ ንዋይ ምርትና ግብይት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ አበበ እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉም ምጣኔ ሀብቱ ላይ የራሱን ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡

"ይህንን በመቅረፍ የግብርና ሙዓለ ንዋዩን ለማሳደግ ደግሞ፤ አበዳሪ ባንኮች የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ብድር ከልክለዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ አሐዱ ዘገባ እንደ ሀገር ባጋጠመ የገንዘብ እጥረት፣ በጸጥታ ችግርና በመሠረተ ልማት አለመሟላት ዘርፋን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ላይ ተግዳሮት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶችም ከገቡበት ሥራ በመውጣት በተለያዩ ሕገ-ወጥ ሥራዎች ላይ በመሰማራቸው በምክንያት፤ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ እንዳያመጡ እንቅፋት እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Hamrin A
🗝️ እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዕጩዎችና መራጮች በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መራጮችና ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ማበልፀጉን አስታወቀ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ያለፉት ሥድስት የኢትዮጵያ የምርጫ ሂደቶች ማንዋል እንደነበሩ ጠቅሰው፤ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መራጮችም ሆኑ ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበትን ሶፍትዌር ማበልፀግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ሰብሳቢዋ ይህን ያሉት፤  በዛሬው ዕለት በቴክኖሎጂው አሥተዳደር ሥርዓት ላይ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ነው።

ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሂደቱ ኢትዮጵያ በምርጫ ሥርዓቷ “አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ የሚያስችላት” ከመሆኑ ባለፈ፤ በምርጫው ሂደት ላይ “ግልፅነትና ተጠያቂነትን” ለማስፈን ያስችላል ብለዋል።


የውይይቱ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው ሶፍትዌሩ ጊዜ ቆጣቢና እንግልት የሚቀንስ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለግልፅነትና ለተጠያቂነት ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

ባሳለፍነው ወር ቦርዱ ለ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ፤ ሁለተኛ ዙር የምርጫ ጣቢያዎችን በዲጂታል ሲስተም የመመዝገብ ሥራ ማከናወኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

ቦርዱ ለ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጾ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች በአፈጻጸም ቀልጣፋና ጊዜው የሚጠይቀውን ዘመናዊነት የተከተለ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኦነግ አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና ቢሮው ከአራት ዓመታት በኋላ እንደተመለሰለት አስታወቀ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከነሃሴ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግቶ የነበረውን እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ዋና ቢሮው በይፋ እንደተመለሰለት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

"በይበልጥ የአዲስአበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቻለውን ያህል ጫና ሲያደርግ ነበረ" ያሉት አቶ ለሚ የምክር ቤቱ እንዲሁም ሌሎች ተወካዮች በተገኙበት ቢሯችን ለማስመለስ ችለናል ብለዋል።

አክለውም "ወደ ቢሯችን እንድንመለስ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል" ሲሉ አስታውቀዋል።አያይዘውም ፓርቲያቸው ከ200 በላይ ጽህፈት ቤቶች እንዳሉት ጠቅሰው በቀጣይ በተዋረድ የተዘጉ ጽሕፈት ቤቶቻችን እንዲከፈቱልን ውትወታችን ይቀጥላል ብለዋል። ወደፊትም አደረጃጀቶቻችንን ለማጠናከር ተስፋ አድርገን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
ቲክቶከሯ ጃኒ ተጨማሪ 7 ቀን በእስር ቤት ታሳልፋለች

ቲክቶከሯ ጃኒ ገብሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተይዛ ወደ ድሬደዋ ከተወሰደች በኋላ ከዚራ ፖሊስ ጣቢያ ትገኛለች።

ወጣቷ ለእስር ያበቃት በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ተናግራለች በተባለ ንግግር ሲሆን ዛሬ በድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርባ ነበር።

ፖሊስ ከተከሳሿ ስልክ ጋር ያልሰራናቸው ምርመራዎች ስላሉኝ ተጨማሪ ቀናት ይሰጡኝ በማለቱ 7 ቀን በፍርድ ቤት ተፈቅዶለት ለሰኔ 9/2017 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከኢትዮጲካሊንክ ሰምቷል።

ቲክቶከሯ ይፋዊ መጠሪያ ስሟ በሶሻል ሚዲያ እንደሚገለጸው "ስመኝ ገብሩ" ሳይሆን በፍርድ ቤት ወደ "ጃኒ ገብሩ" በመቀየሩ በዛሬው ችሎት በይፋዊ መጠሪያ በማድረግ ጃኒ ገብሩን ማስመዝገቧን ከኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassef
ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ

በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሲዳማ ቡናና ወላይታ ዲቻ መካከል  የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ የእግር ኳስ ውድድር መካሄዱ ይታወሳል፡፡

ሁለቱን ክለቦች ለመደገፍ ከሀዋሳ፣ ከወላይታ ሶዶ እና ከአካባቢው የመጡ በርካታ ደጋፊዎች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ጨዋታው በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ ተደርጎ ፖሊስ በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር የነበረውን ግጭት በማስቀረት አስፈላጊውን ወቅታዊና ሕጋዊ ተግባር በመፈፀም ሕግና ሥርዓት አስከብሯል፡፡

ነገር ግን የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት የሚመራቸው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ያሉ አካላት ተናበው የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ አስመስለው በመዘገብ ግጭት ለማባባስ እየሞከሩ እንደሆነ ታዝበናል፡፡

ፖሊስ ግጭቱን ለማባባስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ውስን ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ ሲሆን ውጤቱንም በየጊዜው ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል። ከዚህ ውጭ በአንድም ሆነ በሌላው መልኩ የእርስ በርስ ግጭት የሚፈልጉ አካላት ሰው ሞቷል እያሉ የሚያሰራጩት ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን እና በአንድም ሰው ላይ የሞትም ይሁን የአካል መጉደል ጉዳት ያልደረሰ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ስፖርት በባህሪው የተጣላን የሚያቀራርብ ሆኖ ሳለ በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ሌላ እንዳይሰፋ ፖሊስ በወሰደው ህጋዊ እርምጃ ግጭቱን ተቆጣጥሯል፡፡

ይሁን እንጂ በሀሰተኛ ወሬ ሕብረተሰቡን ወደ ግጭት እንዲያመራ እና የሕዝብ አለኝታና ጠባቂ የሆነውን ፖሊስ ስም ለማጉደፍ በሚንቀሳቀሱት ላይ ፖሊስ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድና በቀጣይም ስፖርቱ ለእንዲህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነት ተገዢ እንዳይሆን ፖሊስ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ያስታውቃል፡፡  
    
@YeneTube @FikerAssefa
ለመገናኛ ብዙሃን !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት "ገለቴ ቡርቃ" ጉዳይ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

ስለሆነም ነገ ሰኔ 03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በፌዴሬሽኑ በመገኘት መረጃውን ለስፖርት ቤተሰብ እንድታደርሱ በአክብሮት እንጠይቃለን ።

@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚኒኬሽን
አፕል የአለም ትልቁ ኩባንያ ነው። እአአ ከ2011 ጀምሮ የኩባንያው ዋጋ በቀን ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ይጨምራል። ይህ ስኬት ግን ያለ ቻይና የሚታሰብ አልነበረም። አፕል እና ቻይና ያለፉትን ሃያ ምናምን አመታት ቸበርቸስ ብለውበታል። ይሁን እንጂ ይህ የአሜሪካ ኩባንያ ሳያስበው ይሁን እያወቀ ካለቻይና መኖር የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በዚህ ዙሪያ የሰራነው አጠር ያለ ልዩ ዝግጅት ነው ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉት፤ መሰል ዝግጅቶችን በየጊዜው ለመከታተል ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

https://youtu.be/GEAHr2Xqf5Q
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tgoop.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
ከተማ አቀፉ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፤ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ በገላን ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ፈተናውን በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል።

ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ሂደቱን የሚከታተል የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ከማዋቀር አንስቶ በቂ የፈተና አስፈጻሚዎች ተመልምለው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ተናግረዋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 6,828 ተማሪዎች በ24 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከተማ አቀፉን የ2017ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 71,972 ተማሪዎች በ194 የፈተና ጣቢያዎች የ2017ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው እና በቂ ፈታኞች፣ጣቢያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋር፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ እና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት በላይነሽ ዋቅጅራ እና የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ ዶክተር አያሌው ጥላሁን በጋራ በመሆን በቶፕ ቴን ሆቴል መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፦ አትሌት መሠረት ደፋር

ለሀገሯ ይህን ያክል ዋጋ የከፈለችው አትሌት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የገጠማትን ችግር ለመፍታት በፍርድ ቤት ስለመንከራተቷ በቅርበት አውቃለሁ ያለችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሠረት ደፋር፤ ሕግ ለዚህች የሀገር ባለውለታ ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ ብላለች።

መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ መሠረት ደፋር አሳስባለች።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
2025/06/18 10:38:15
Back to Top
HTML Embed Code: