የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ለማላቅ የተዘጋጀውን የማላቅ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀመጠ።
(ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም) በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ሁሉም የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና የ2ኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን የማላቅ ስትራቴጂው በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው የተለያዩ ተግባራትን የያዘ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል::
አያይዘውም ስትራቴጂውን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና የሚመለከታቸው አካላት የክላስተር ማዕከላትን በማደራጀት ፣ ተማሪዎችን በማስተባበርና ወላጆችን በማወያየት ለእቅዱ ውጤታማነት በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። እንዲሁም ከሰኞ ጀምሮም ወደ ስራ እንዲገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በውይይቱ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጥላዬ ዘውዴ አማካኝነት በየክፍለ ከተማው የሚቋቋሙ ክላስተር ማዕከላት አደረጃጀትን ጨምሮ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሌሎች የአፈፃፀም ተግባራትን በአግባቡ መተግበር የሚያስችል የማላቅ ስትራቴጂው ለተሳታፊዎች ቀርቧል::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

❤63👎5👍3🥰1
❤52👍15👎10👏2
የ2018 ትምህርት ዘመን ጥናትና ምርምር ስራ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ::
(ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ትምህርት ዘመን የጥናትና ምርምር ስራዎች 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ::
የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ በውይይቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ለትምህርት ሴክተሩ አስፈላጊ የሆኑና በተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ ለውጥ የሚያመጡ ጥናትና ምርምር ስራዎች ለመስራት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረው ጥናትና ምርምሩ የትምህርት ጥራትን ለማምጣትና በስነምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል ::
አቶ ተስፋዬ አያይዘውም የዚህ የሩብ ዓመት የስራ ግምገማ ቀጣይ መምህራን ለሚሰሩት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ስራ ቅርብ የሆነ ድጋፍና ክትትል ለማድረግና በትስስር የሚሰሩ ሥራዎች የሚፈልጉትን አቅም በማወቅ ረገድ መነሻ የሚሆን ሀሳብ የሚገኝበትና በምን መልኩ መደገፍ እንዳለብን ግንዛቤ የምንወስድበት ይሆናል ብለዋል ::
በውይይቱ የክፍለ ከተማ ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች እና የሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የጥናትና ምርምር ስራው 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በአቶ ዮሐንስ ተስፋዬ አማካኝነት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል::

❤39👏4