Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎ ካልደረሰዎ ወይም ከጠፋብዎ *9779# ላይ ይደውሉ📞

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከ608 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ!

በ2017 የትምህርት ዘመን ከ608 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ መልቀቂያ ፈተና የፈተና ስርቆትና ኩረጃ በሚቀንስ መልኩ በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

በወረቀት የሚፈተኑት መሰረተ ልማት ያልተሟላባቸው፤ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት ኮኔክሽን በበቂ ባላገኙ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ፤ በበየነ መረብ የሚሰጠው ፈተና እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ወደፊት ሙሉ በሙሉ ፈተናውን በበየነ መረብ ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የፈተና ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በመግለጽ፤ ፈታኞችን የመመልመል፤ የተመለመሉት ወደዬመፈተኛ ጣቢያው እንዲሰማሩ የማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡በአማራ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ በርካታ ት/ቤቶች የዘንደሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደማያስፈትኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግሥቱ በቅርቡ ገልጸዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ 685 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የዘንድሮውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች 470 ብቻ ናቸው ብለዋል።

ክልሉ ቀደም ባሉት ዓመታት በየዓመቱ ከ150 ሺህ እስከ 180ሺህ ተማሪዎችን የማስፈተን አቅም እንደነበረው የገለጹት ኃላፊዋ ሰላም ባለባቸው አከባቢዎች በሚገኙ ት/ቤቶች የሚገኙ 99ሺህ 880 ተማሪዎች የዘንድሮን ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ፈተናን በወረቀት ለሚፈተኑ ተፈታኞች

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀድሞው የተሻሻለ የመልስ መስጫ ወረቀት ለተፈታኞች ምቹ በሆነ ዲዛይን በአዲስ መልክ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ተፈታኞች ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ማስገንዘብ በማስፈለጉ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡


ተፈታኞች ማድረግ ያለባቸው ነገሮች

👉ክረምት ከመሆኑ አኳያ በሚፈጠር እርጥበት፣ የምትፈተኑበት ጠረጴዛ ላይ ባለ ፈሳሽ ነረርም ይሁን በሙቀት በሚፈጠር የእጅ ላብ ወረቀቱ እንዳይረጥብ እና እንዳይቀደድ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

👉ሙሉ ስማቸውን የሚፈተኑትን የት/ት ዓይነት እና የተማሩበትን ት/ቤት በcapital letter ሊነበብ በሚችል መልኩ በተቀመጠው ጠቋሚ መሰረት ነጭ ቦታው ላይ ብቻ ይፃፉ፡፡ የሚጽፉትን ከአድሚሽን ካርዳቸው ጋ ማግኘት ይችላሉ።

👉የመፈተኛ መለያ ቁጥራቸውን(ከአድሚሽን ካርዳቸው) የት/ቤት መለያ ቁጥራቸውን(ከአድሚሽን ካርዳቸው) የሚፈተኑትን የጥያቄ ወረቀት መለያ ቁጥር(hጥያቄ ወረቀቱ )እና የት/ት ዓይነቱን መለያ ቁጥር ከአድሚሽን ካርዳቸው ወይም ከጥያቄ ወረቀቱ) በመውስድ በትክክል በቦታው ላይ መፃፍ እና በተፃፈው ትይዩ ወደታች የፃፉትን ቁጥርበተሰጠው የአጠቋቆር መግለጫ መሰረት በትክክል ሙሉ ክቡን ማጥቆር ግዴታ ነው።

👉ፈታኙ የፃፈውን እና ተፈታኙ ፅፈው ያጠቆሩትን የጥያቄ ወረቀት መለያ ቁጥር ተመሳሳይመሆኑን ማረጋገጥ።

👉በሚፈተኑት የት/ት ዓይነት የጥያቄ ቁጥር ብዛት መሰረት እና በተሰጠው የአጠቋቆርመግለጫ መሰረት ከአራቱ አማራጮች ውስጥ መልስ ነው ብለው ያመኑበትን አንድ ፊደል

👉መልሱን ሲያጠቁሩ ተሳስተውም ይሁን መልስ ቀይረው ለማስተካከል ከፈለጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን መልስ እርሳሱ እስኪለቅ ድረስ በደንብ ማጥፋት ግዴታ ነው።

🙅‍♂️ተፈታኞች ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች

👉ፈሳሽ ያለበት ነገር ላይም ይሁን እርጥበት ያለበት ቦታ ላይ የመልስ ወረቀቱን ማስነካት ወይም ማስቀመት በፍጡም የተከለከለ ነው።

👉መፃፍም ይሁን ማጥቆር ከሚገባቸው ቦታ ውጪ የመልስ ወረቀቱ detect mark guide (5ቱ ክቦች)፣ ከመስሪያ ቦታው ውጪ ባሉ አራቱም ህዳጎች እንዲሁም ከመልስ ወረቀቱ ጀርባ ላይ በምንም አይነት መልኩ የእርሳስም ይሁን የሌላ ነገር ምልክት መተው በፍፁም የተከለከለ ነው።

👉ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር

👉ምንም መልስ ሳያጠቁሩ ማለፍ


📌ማጠቃለያ

👉መኮረጅም ይሁን ማስኮረጅ ሙሉ ውጤትን እስከመሰረዝ ድረስ ያስቀጣል።

👉ከአንድ በላይ መልስ ማጥቆር ውጤት አያሰጥም።

👉ምንም መልስ አለማጥቆር ውጤት አያሰጥም።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይመዝገቡ!

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ምዝገባ ነገ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል፡፡

እስካሁን ያልተመዘገባችሁ የድጋሚ ተፈታኞች (Re-sitters) በመመዝገቢያ ፕላትፎርሙ (https://exam.ethernet.edu.et) ገብታችሁ ምዝገባችሁን በቀሩት ሰዓታት አድርጉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የምትቀመጡ ተፈታኞች በተቋሞቻችሁ በኩል መመዝገባችሁን እንድታረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴሩ ማሳሰቡ ይታወቃል።

የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 02-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ለፈተናው የምታመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የፋይዳ መታወቂያ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#RemedialExam

የሪሚዲያል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

በዚህም ተማሪዎቹ ለኦንላይን ፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና በበይነመረብ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በኮምቦልቻ እና በደሴ ግቢ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ከ2000 በላይ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና በበይነመረብ መስጠት ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል - የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
********

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ተናገሩ።

አብዛኛውን ጊዜ ፈተና ሲነሳ የፈተና ስርቆትና ኩረጃ አብሮ የሚነሳ ሲሆን፤ ይህን ለማስቀረት መንግስት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ሀገረ አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች ከተማሩበት ት/ቤት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንዲፈተኑ አድርጓል።

ለፈተና ስረቆትና ኩረጃ የሚያግዙ ድምፅን ምስልን የሚወስዱ ማንኛውንም መሳሪያዎችን ተማሪዎች እንዳይጠቀሙና ይዘውም እንዳይገኙ በመከልከል፤ ጥብቅ ፈተሻ እንደሚደረገ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ተይዘው ሲገኙም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ፈተናን ለመስረቅና ለመኮረጅ የሚያባክኑትን ጊዜ ትምህርቱን በሚገባ ቢያጠኑበት መልካም ነው፤ ውጤታማም ብለዋል።

በብይነ-መረብና በወረቀት የሚሰጠው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ መንገድ ለመስጠት፤ የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስና የተለያዩ ዝግጅቶችን አጠናቀው ተማሪዎችን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ፈተናውን በብይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎች በየትምህርተ ቤታቸው ልምምድ በማድረግ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ዶ/ር እሸቱ፤ ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎችም ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ እየተደረገም ይገኛል ነው ያሉት።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶች ዝግጁ መሆናቸውን መፈተሸና ለሰው ሀይል ስልጠናዎችን መስጠት፤ እንዲሁም ከክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

#EBC

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡

በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡

ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?

ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተፈታኞች የቴክኒካል ድጋፍ የሚሰጥ ቡድን ተቋቁሟል።

በበይነ መረብ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ማንኛውንም ድጋፍ በመጀመሪያ በትምህርት ቤታቸው ቀጥሎም በመፈተኛ ማዕከላት ካሉ የትምህርት አመራር እና ቴክኒክ ድጋፍ ሰጪዎች ማግኘት እንደሚችሉ ይታወቃል።

ተጨማሪ ድጋፍ ለተፈታኝ ተማሪዎቹ የሚሰጥ ቴክኒካል ቡድን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።

ዘጠኝ አባላት በውስጡ የያዘው ቴክኒካል ቡድኑ፤ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍሎ የተደራጀ ነው።

(የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድኑን ድጋፍ ለማግኘት ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MockExam

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተማሪዎች #ሞዴል ፈተና በተለያዩ ተቋማት ተሰጥቷል። 

#ሞዴል ፈተናው ለሁለት ቀናት እንዲሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባዘጋጀው መርሐግብር መሠረት፤ በርካታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞቹ የኦንላይን ልምምድ እንዲያገኙ አድርገዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ዘንድሮ 150 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በብይነ መረብ ይወስዳሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Wise Box
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🚀ሁሉን በአንድ መተግበሪያ ማለት #Wise #Box ነው፡፡
አስደሳች ዜና ለተማሪዎች በሙሉ #Wise Box በመጠቀም የሚከተሉትን መግኘት ትችላለችሁ👌

🔸 ኢንትራንስ ኤግዛም እና ሞዴሎች
🔸 Practice ኢንትራንስ ኤግዛም
🔸 Normal ኢንትራንስ ኤግዛም
🔸 ኤግዚት ኤግዛም እና ሞዴሎች
🔸 ዩኒቬርሲት ኤግዛሞች
🔸 የክላስ ፈተና 9ኛ-12ኛ ክላስ
🔸 ቤተ መጽሐፍት
🔸 ልብ ወለዶች(English, አማርኛ, Afaan Oromoo)
🔸 ሚኒስትሪ ኤግዛም እና ሞዴሎች
🔸 የመመረቂያ ጹሑፍ(Ideas and Samples)
🔸 መስተወሻ መያዣ
🔸 መርሐግብር/ስኬጁል መያዣ

አፕልኬሽኑን ለማውረድና ቤተሰብ ለመሆን ይህን መስፈንጠሪያ ይንኩ፣ 👌
እኛ ቤት ሁሉም ነፃ ነው አናስከፍልም፤ ክፍያችን የእርሶ እርካታ ነው ይጎብኙን፡፡👇
May 30 revised-Sene2017-EXIT EXAM Schedule - 1 -(1).xls
235.5 KB
#ExitExam #Revised

ከአንድ ሳምንት በሗላ የሚሰጠው የ 2017 ሰኔ ወር ብሔራዊ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተና (university national exit exam) መርሐ ግብር(schedule)
➡️ሰኔ 2 management
➡️ሰኔ 3 Accounting
➡️ሰኔ 4 ህግ computer science, biology, sociology, social work.... እያለ ይቀጥላል
➡️ሰኔ 5 Midwifery, Pharmacy, Medical Radiology እያለ ይቀጥላል.........

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/05/31 19:29:08
Back to Top
HTML Embed Code: