Telegram Web
መኖርያ ቤታቸውን ሸጠው የአርባምንጭ ዝጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ታምር አድራጊ ጸበል ለዓለም ያስተዋወቁ የጻድቁ ባርያ የሆኑ ምስጉን እናት
~~~~~~~

ጠርያ ስማቸው ወ/ሮ ካሠች ባላሉ። ቅድስ ቤተክርስትያን ወለተ ማርያም ብላቸው ትጠራችዋለች። በመምህርነት የሞያ መስክ ዕድሚያቸውን ሙሉ አገልግለዋል።

ዕድገት እና ነዋሪነታቸው አርባምንጭ ከተማ ላይ ነው።

ወዳጅ ልጆቻቸው "እናታችን" ብለው ይጣሯችዋል። ፍጹም መረጋጋት ግርማ ካለው የእናትነት ጸጋ ጋር ፊታቸው ላይ ይነበባል።

የዛሬውን እንኳን አደረገው እና ያቺ ጥንታዊቷ ከ120 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረችው ከአርባምንጭ ከተማ በ17 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ፣ ካህናት እና ዲያቆናት ከከተማ በወር አንዴ እየመጡ የሚቀድሱበት ልትወድቅ ደርሳ በየእለቱ ጭቃ እየተመረገባት በግድ የቆመችው የዝጊቲ አቡነገብረመንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን እንደዛሬ ብዙዎች አያውቋትም ነበር።

የጻድቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸበልም በአከባቢው ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ የሚጠቀሙት ቢሆንም በሣር በጥሻ እና በጎርጅ ውስጥ የተደበቀ ነበር።

"በስሜ ገንዘብ ሳትለምኝ በእራስሽ ገንዘብ ጸበሉን ገንቢልኝ ፤ገንዘብ ከሌለሽም በኮባ ቅጠል አጠራቅመሽ የሰው ልጆች ይድኑ ዘንድ አሳውቂው" ሲሉ በህልም ከጻድቁ እንደተረዱ የሚገልጹት እኝህ እናት ስፍራው ላይ ከ44 በላይ የጸበል ምንጮችን በጻድቁ ረዳትነት አመላክተዋል።

እነዚህ የጸበል ምንጮችም ዛሬ ላይ ለጸበልተኛው የፈውስ እና የድህነት ምክንያት ሆነው በጻድቁ ምልጃ በክርስቶስ ኢየሱስ ምህረት እና ቸርነት ኃይል እያደረጉ ይገኛሉ።

የገዛ መኖርያ ቤታቸውን ሸጠው የጻድቁን የጸበል ስፍራ አስገንብተው ደውያን እንዲፈወሱ፣ደካሞች እንዲያርፉ ምክንያት ሆነዋል።

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ለእዚህች ምስጉን እናት ለአገልግሎታቸው እውቅና ሰጥታቸዋለች።

ዛሬ ላይ ይህ ስፍራ ከግማሽ ቢሊዬን ብር በላይ በሆነ ሐብት በአንዲት እህታችን አማካኝነት ግንባታው እየተከናወነበት ሲሆን ዛሬም ድረስ ህገ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ የሱባኤ እና የእረፍት በዓት ሆኗል።

የእናታችንን የአገልግሎት ዘመን ያርዝምልን!
ኑ በፈረሰው በኩል እንቁም

ማህበረ ቅዱሳን ያዘጋጀው መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ጌምቤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ከዚህ በፊት በዚሁ ገፄ ለይ በቪዲዮም ጭምር እንዳሰፈርኩት ያለፈው ወር ለይ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሻማ ሳያጠፉ ሂደው ቤተክስቲያኑ ሙሉ በሙሉ መውደሙን እና በአከባቢው ያሉት ምዕመናን ጥቂት መሆናቸውን ነግሬያችሁ ነበር አሁን እግዚአብሔር ፈቅዶ ማህበረ ቅዱሳን ጅማ ማዕከል የፊታችን ነሃሴ 22 በዛ ቦታ ያሉ ያዘኑትን ጥቂት ምዕመናንን ለማፅናናት እንዲሁም ምዕመኑ ለቤተክርስቲያኑ የራሱን አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በማሰብ ልዩ ጉዞ አዘጋጅቷል በጅማ እና አከባቢዋ ያላችሁ የተዋህዶ ልጆች የዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በሰማዕቱ ስም ተጋብዛችዋል ትኬቱን ከላይ ባሉ ስልክ ቁጥሮች ወይም በጅማ አድባራት ሰንበት ት/ት ቤት ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ያገኙታል ሼርርር ይደረግ
የጌምቤ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት ገብተው ይከታተሉ https://youtu.be/qRzxIOB-eec
Forwarded from Qualitymovbot
ይሄንን ተዓምር ስሙ የኔ የዩቱብ ቻናል ነው ሰብስክራይብ አድርጉ https://youtu.be/bU0ttxRGI0g
እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ ሼርርር አድርጉ https://youtu.be/9ej7VR6K7eA
#ቁርሴን_ለነዳያን_ቻሌንጅ

ሰላም በመላው ዓለም የምትገኙ የተዋህዶ እንኳን ለታላቁ ዐቢይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ

ለችግረኛ እና ለምስኪን የሚያስብ እርሱ ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀዋል
መዝ 41÷1

እንደሚታወቀው የ2015 ታላቁን ዐቢይ ፆም ጀምረነዋል ሁሉም የተዋህዶ ልጅ ይፆማል እግዚአብሔር ፈቅዶ ስንጨርስ እንኳን አደረሳችሁ ስንባባል እቤት ያፈራውን ዘመድ አዝማድ ጋር ተጠራርተን ስንቋደስ አንድ አንዶች ምስኪን ችግረኞች እቤታቸው ምንም የሌላቸው ጠዋሪ ያጡ እንኳን ስጋ መግዛት ቀርቶ ጨው መግዣ አጥተው እቤታቸውን ዘግተው የሚቀመጡ በርካታ የተዋህዶ እናት አባት ቤተሰቦች አሉ

ታዲያ እነዚህን ምስኪን እናት አባቶቻችንን ፆም ለማስፈታት ይረዳን ዘንድ ከመጀመርያዋ ቀን እስከ 55ኛው ቀን ድረስ የምንበላ የነበረውን ቁርሳችንን ገንዘቡን በማጠራቀም እንድናግዛቸው #ቁርሴን_ለነዳያን_ቻሌንጅ ጀምረናል

ይሄንን ቻሌንጅ ለመቀላቀል

1ኛ የተዋህዶ ልጆች ቢያንስ ለ10 ሰዎች ሼር ማድረግ

2ኛ በዚህ ቻሌንጅ ተሳታፊ መሆን እፈልጋለሁ በማለት በስልክ ቁጥር
0967791717
0917394585 በቴሌግራም በዋትሳፕ በኢሞ መልዕክት ማስቀመጥ ወይም መደወል

3ኛ በየዕለቱ ለቁርስ የምናወጣውን በማጠራቀም ወይም ደግሞ እግዚአብሔር ከሰጠን ለይ ለነዳያን መስጠት

በተረፈ የተለያዩ ዝርዝር ነገሮች ስላሉ በቴሌግራም ያናግሩን መልካም ፆም
ታላቅ መንፈሳዊ የበረከት ጉዞ
ወደ ቋራ በርሚል ጊዮርጊስ

በዚህ ሰዓት ብዙ ህሙማን ከህመማቸው ከደዌያቸው እየተፈወሱ በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ እያገኙ ያለበት ተዓምራዊ ቦታ በርሜል ጊዮርጊስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መጋቢት 9 ማህበራችን መባ የጉዞ ማህበር ጉዞ አዘጋጅቷል በዚህ ጉዞ ለይ የጣና ገዳማትን ጨምሮ በርካታ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት ይጎበኛሉ ፈጥነው ይመዝገቡ

👉 መነሻ ቀን መጋቢት 9 ከሌሊቱ 10:00
👉  መመለሻ ቀን መጋቢት 15
👉 መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ እና ፒያሳ ጊዮርጊስ
👉 የደርሶ መልስ ክፍያ 4000
👉 መመዝገቢያ ቦታ ባሉበት ሆነው ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ ገንዘቡን በንግድ ባንክ 1000247966866 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በቴሌግራም ይላኩልን

ስልክ 0967791717
         0917394585
ሼር አድርጉ
ይሄ መልዕክት ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ

"ለችግረኛ እና ለምስኪን የሚያስብ ሰው እርሱ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በመከራ ቀን ያድነዋል " መዝ 41÷1

በመላው ዓለም ያለን የተዋህዶ ልጆች ዓቢይ ፆምን ትንሳኤከ ብለን ጧፋችንን አብርተን  ለመዘመር እንዲሁም ከቤተሰቦቻችን ጋር ከያለንበት ቦታ ተሰብስበን ያለንን እየተቋደስን በደስታ ለማሳለፍ ጥቂት ቀናት ይቀሩናል

እርግጥ እኛ ስንበላ ስንጠጣ እንኳን አደረሳችሁ ስንባባል እቤታቸውን ዘግተው የሚቀመጡ  ለመለመን አፍረው የችግር አለንጋ እየገረፋቸው የውስጣቸውን በውስጣቸው ይዘው የሚቀመጡ ብዙ ሰዎች አሉ

እስቲ ዘንድሮ እነዚህን ሰዎች ለበዓል ልጎብኛቸው ብዬ በብዙ ችግር ውስጥ ይሆናሉ ብዙ ሰዎች ላይመለከቷቸው ይችላሉ ብዬ ወደ አሰብኩበት ትውልድ መንደሬ አቀናለሁ ለእነዚህ ምስኪን ሰዎች በቻልኩት መጠን ለበዓል የሚሆን ስጦታዎችን ይዤ እሄዳለሁ በዚህ መልካም ተግባር መሳተፍ የምትፈልጉ በተለያዩ ክፍለ አለማት ያላችሁ ወዳጆቼ ከስር በማስቀምጥላችሁ ስልክ ቁጥር እየደወላችሁ ወይም በቴሌግራም አናግራችሁ እንድንተጋገዝ አሳስባለሁ
በነገራችን ለይ ለበጎ ነገር መሳተፍ ትልቅ ነገር ነው ለመሳተፍ የደግሞ የልቦና ቅንነት ይፈልጋል እና ያላችሁን ጥቂት ነገር ለበጎ ተጠቀሙበት
0967791717
0917394585
ዕለተ ሆሳህናን በሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት እናሳልፍ

እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዚህ ዐቢይ ፆም ወቅት ወደ ተለያዩ ገዳማት መንፈሳዊ ጉዞ እያዘጋጀ ምዕመናን በረከት እንዲያገኙ እያደረገ የነበረው ማህበራችን አሁን ደግሞ የሆሳዕናን በዓል ስዕለት ሰሚ ወደ ሆነቸው ተዓምረኛዋ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ጉዞ አዘጋጅቷል ይሄ ጉዞ ለየት የሚያደርገው በዝማሬ የሚያገለግሉ ዘማርያን እና የሚያስተምሩ መምህራን ተጋብዘዋል

የደርሶ መልስ ጉዞ ምግብ ጨምሮ 500 ብር ብቻ
መነሻ እሁድ ሌሊት 11:00
መመለሻ በዕለቱ
መነሻ ቦታ ፒያሳ ጊዮርጊስ

ስልክ 0967791717 / 0917394585 ይደውሉ እርሶ ባይሄዱ እንኳን በቅንነት ሼር ያድርጉ
Audio
🔔አዲስ_ዝማሬ

🎤አኑርልኝ_ለአፌ_ጠባቂ

🎙ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

JOIN US
🔔
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
https://youtu.be/nMkoV-wIjTw

🤗ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🤗
👳🏽‍♂ በግሩም እና በተወዳጅ ዘማሪያን
ብዙ እውቀትን ታገኙበታላችሁ ከታች ባለው ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ።
👇🏽👇🏽
https://youtu.be/ggPuK3XXHF4
https://
         👆 ይቀላቀሉን   👆

ቴግራም ቻናል
👇👇👇
JOIN US
@kidus_yared_kidus
@kidus_yared_kidus
አንድ ሰው በወር አንድ መቶ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ብቻ ተወልዶ ባደገበት ሰንበት ት/ት ቤት በተማረበት ደብር ልዩ ጉባኤ ያዘጋጅ

ብዙውን ጊዜ እኛ የለመድነው ህንፃ ቤ/ክ መገንባት ብቻ ነው ነገር ግን አብዛኛዎቹ ምዕመናን ት/ት በማጣት ወደ ኢ አማንያን እየሄዱ ይገኛሉ ይሄንን ነገር በጥቂቱም ቢሆን ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ ሁላችንም በመተባበር እና በመተጋገዝ በወር አንድ መቶ ብር ብቻ በመስጠት በአደግንበት ደብር ጉባኤ ማዘጋጀት ይቻላል ለዚህ በጎ ተግባር ፍላጎት ያላችሁ በተከፈተው የቴሌግራም ፔጅ በመቀላቀል በደብራችሁ ጉባኤ በወር መቶ ብር ብቻ በመስጠት ማዘጋጀት ትችላላችሁ

👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/gubae2121

ሊንኩን በመጫን ወደ ግሩፑ ተቀላቀሉ ለዚህ ሀሳብ ደጋፊ የሆኑትን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ
Forwarded from 📚👳‍♂ORThODOX LIFE19👳‍♂📚 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
https://youtu.be/cvHyhvvBHdA
ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች ባለማህተቦች ሰላማችው ይብዛልኝ ።
በአዲስ ነገር ወደናንተ እንድ መጣ የናንተ መልካም ፍቃድና ትብብራችው ያስፈልገናል እናንተ ስብስክራቭ 👍ላይክ ስታደርጉን በይበልጥ ያበሩታናልና ላይክ ሰብስክራቭ አድጉኝ ባለማህተቦች በዚህ ቻናል ለቤተክርሲቲያናችን ድምጻችን የምናሰማበት እና እናንተ ያስተምራል ብለን ያሰብነውን በቅርቡ ወደናንተ እናደርሳለን እስከዚያው በዚህ ጥዑም ዝማሬ ተጽናኑ!
ታዲያ ሰብስክራይቭ ላይክ ታደርጋላችሁ በማርያም በወላዲቱ አትለፉኝ አድርጉኝ🙏
መንፈሳዊ ሚዲያዎችን በመንፈሳዊነት እናብዛ በማርያም❤️
        👇👇👇
https://youtu.be/cvHyhvvBHdA
https://youtu.be/cvHyhvvBHdA
2025/06/13 22:20:45
Back to Top
HTML Embed Code: