Telegram Web
****

ቃና ዘገሊላ

ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ)
የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው:: ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል

ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ
መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ):
ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው

ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን
ቻይ' እያልን የምንጠራው:: እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1ነገሥትን ተመልከት) እንደ ነበር ይታወቃል


እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12) እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)

ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ 2 ላይ
እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው:: "ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: (ዮሐ. 2:11) ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም

ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው
የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: (ማቴ. 4:1) አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ

+ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት 23 ነው:: ጥር 11 ተጠምቆ: የካቲት 21 ቀን ከጾም ተመልሷል:: ከዚያም የካቲት 23 ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል
ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር 12 ቀን አድርገውታል

በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ
ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ

ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ
የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና)
ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ


የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው
ሲቀመጡ: ሌሎች ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ:: ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ:- በጸጋ: አንድም 'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል:: እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ አልቦሙ-ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው

+ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ ቃሉንና ክቡር ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል:- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!) ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ " አላት::
ምክንያቱም ጌታ:-

የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: (አበረከተ ይሉታልና) አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው:: (እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ) አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ:: ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት:: "አባትህንና እናትህን አክብር" (ዘጸ. 20) ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?ልቡና ይስጠን!

ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን "ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ-የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: (ዮሐ. 2:5) ጌታም በ6ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን አደረጋቸው

+እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው) ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ: ተገለጠ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
🌿❤️  ጥር 21  በዓለ  አስተርእዮ  ማለት🌿❤️
《የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን ለዚህች ታላቅ ክብረ በዓሏ አደረሳችሁ አደረሰን!!!

🌿❤️ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡

🌿❤️ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡
🌿❤️ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
... 🌿❤️ የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡
🌿❤️ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡
🌿❤️ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡
🌿❤️ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡
🌿❤️ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
🌿❤️ አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ
#አስተርእዮ__ማርያም ተብሏል፡፡
🌿❤️ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡
🌿❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡
💟ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ 《ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ》ነገረቻቸው፡፡
💟ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡
🌿❤️ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡
🌿❤️ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡
🌿❤️ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
💟እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡
🌿❤️ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡
🌿❤️ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን አሜን ።
❤️💜💚💛💙❤️💙💚💜❤️
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
❤️💜💚💛💙❤️
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
#ይህንን_ያውቃሉ

የሦስቱ ዲያቆናት ምሳሌነት ምንድን ነው ?

ቅዳሴ ላይ እንደሚታወቀው ልዑካኑ  ከሁለት እስከ ሃያ አራት ድርስ ሊደርሱ ይችላሉ

አምስቱ ልዑካን  ማለት ሁለት ካህን ሦስት ዲያቆናት በአጠቃላይ የአምስቱ አማዕደ ምሥጢራት ምሳሌ ናቸው

ሦስቱ ዲያቆናት የየራሳቸው ምሳሌነት አላቸው

1. የዋና ዲያቆን (ሠራዒ )

ይህ ዲያቆን የቅዱስ እስጢፋኖስ ምሳሌ ነው

መጾር ወይም መስቀል ይዟ መቀደሱ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀበለውን ሰማዕትነት ለማሰብ ነው

2. ተጨማሪ (ንፍቅ )

ዲያቆን ይህ ዲያቆን ደግሞ መጥመቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ ነው

ከፊት ከፊት እየቀደመ  ካህናቱን መምራቱ ሊቀ ካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፊት ቀድሞ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጥርጊያውን መንገድን የማዘጋጀቱ

ይህ ዲያቆን መብራት ወይም ጠፋፍ የሚያዙ ከመስዋዕት ከማቅርብ አልፎ በዚህ ይመሰላል

3. ፍሬ ሰሞን (መጽሐፍ ገላጽ )

  ይህ ዲያቆን የሐዋርያት አባቶቻችን ምሳሌ ነው እንዴት ቢሉ መጽሐፍ ይዞ በአራቱም አቅጣጫ ይዞራል ይህም
ሐዋርያት በአራቱ አቅጣጫ ወንጌልን የመስበካቸው ምሳሌ ነው።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡


የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
#ብዙ_እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል።”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
"ወደ ቤተክርስቲያን ወጥተህ እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ስራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሠመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"
  
       
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
D#ነገረ #ክርስቶስ #ክፍል #፵
ጌታ ክርስቶስ በባሕርይው ፍቅር ነው። ይህ ማለት ጥላቻ አይስማማውም ማለት ነው። አይሁድ እርሱን ጌታን ከኃጢአተኞችና ከቀራጮች ጋር ሲበላ አይተውት ነቅፈውት ነበር። "የቀራጮችና የኃጢአተኛዎች ወዳጅ" ብለውታል (ማቴ. ፲፩፣፲፱)። ኢየሱስ ኃጢኣታችን እንደ ምድር አሸዋ የበዛ ቢሆን እንኳ ንስሓ ብንገባ ይቅር የሚል አምላክ ስለሆነ ኃጥአንን ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ምክንያት ለመሆን አብሯቸው ይበላ ይጠጣ ነበር። 

ጌታ ሰዎች ተአምራቱን አይተው፣ ትምህርቱን ሰምተው ከኃጢአታቸው ተመልሰው መልካም ሥራን ይሠሩ ዘንድ በከተማዎችና በመንደሮች እየተመላለሰ ያስተምር ነበር። ነገር ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላቸው ከኃጢአታቸው ያልተመለሱ ሀገሮች ስለነበሩ ወዮልሽ ኮራዚ ወዮልሽ ቤተሳይዳ እያለ ወቅሷቸዋል። በፍርድ ቀን መከራ እንደሚበዛባቸውም ነግሯቸዋል (ማቴ. ፲፩፣፳-፳፭)። ጌታ ኃጥአንን እንጂ ኃጢአታቸውን አይወድም። ኃጥአንን ከኃጢአታቸው ለመለየት ብዙ ተአምራትን አሳይቷል። ነገር ግን በባሕርይው ፍቅር የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይው በትክክል የሚፈርድ (ፈታሒ በርትዕ) ስለሆነ ለሁሉም እንደየሥራው ይከፍለዋል። ፍቅሩና ፍርዱ የተስማማለት ጌታ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው እያልን ኃጥአን እንሁን ማለት ትልቅ በደል ነው። ጌታ ኃጥአንን በባሕርያቸው ይወዳቸዋል በግብራቸው ግን ይጠላቸዋል። ጻድቃንን ደግሞ በባሕርያቸውም በግብራቸውም ይወዳቸዋል። ስለዚህ እንደ ጻድቃን በግብርም ለመወደድ መልካም ሥራን መሥራት ይገባናል።
#የካቲት_16

#ኪዳነ_ምሕረት (#የሰባቱ_ኪዳናት_ማሕተም)

የካቲት ዐሥራ ስድስት በዚችም ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም አማላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓልን ያደርጋሉ። በዚች ዕለት መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጠራ ለድኆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀብላለችና።

ይህችም የከበረች እመቤታችን ልጅዋ ንጹሕ ሥጋዋን ተዋሕዶ ከብቻዋ ኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ፈጽሞ ስለእኛ መዳን ወዶ ያደረገውን መከራ ተቀብሎ ሙቶ ተነሥቶ ከዐረገና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ እርሷን እናቱን ማርያምን በደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ዘንድ ትቷት ነበር እነሆ ልጅሽ እርሱንም እነሆዋት እናትህ ብሎ አደራ እንዳስጠበቀው።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ማርያም ትጸልይ ዘንድ ያለ ማቋረጥ ወደ ልጅዋ መቃብር ሁል ጊዜ ስትሔድ ኖረች ይኸውም ጎልጎታ ነው።

አይሁድም በአዩዋት ጊዜ ቍጣንና ቅናትን ተመልተው በድንጊያ ሊወግሩዋት ወደዱ እግዚአብሔርም ከዓይናቸው ሠወራት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መጥታ በዚያ እንዳትጸልይ ተማክረው ከመቃብሩ ዘንድ ጠባቂዎችን አኖሩ እርሷ ግን በየዕለቱ መሔድን አላቋረጠችም ጠባቆችም አያይዋትም የልጅዋ የጌትነቱ መጋረጃ ሠውርዋታልና መላእክትም መጥተው ያገለግሏታል ጌታችንም ዘወትር ይጐበኛታል የምትሻውንም ይፈጽምላት ነበር።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ ሰማይ አሳረጓትና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳዩዋት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብም ወዳሉበት አደረሱዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያ ዕለት በአካለ ነፍስ ያሉ አባቶች ሁሉ አንቺን ከሥጋችን ሥጋን ከዐፅማችን ዐፅምን ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው በመሆኑ በአንቺ ድህነት አግኝተናል ከጥፋትም የሕይወት ወደብ ሆነሽልናልና እያሉ ሰገዱላት።

ከዚያም ወደ ተወደደ ልጅዋ የእሳት መጋረጃ ወደተተከለበት ወደ ጌትነቱ ዙፉን አደረሷት ጌታችንም እጇን ይዞ ወደ ውስጠኛው መጋረጃ አስገብቶ ከጌትነቱ ዙፋን ላይ አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጣት ያዘጋጀላትንም ዐይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው በሰው ልቡና ያልታሰበ ተድላ ደስታን ሁሉ ነገራት።

ከጌትነቱ ዙፋንም በታች የእስራኤል ንጉሥ አባቷ ዳዊትን የነቢያትና የመላእክት ማኀበር እንደ ግድግዳ ከበውት በመሰንቆ ሲያመሰግን አየችው እንዲህም ይላል ልጄ ስሚ በጆሮሽም አድምጪ ወገንሽን የአባትሽንም ወገን ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና እርሱም ጌታሽ ነውና።

ዳግመኛም የሥቃይን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ መላእክት ከዚያ ውሰዷት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በእርሱ ጐዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደተዘጋጀ ወደጨለማው ዳርቻ አደረሷት እመቤታችን ማርያምም ወዮልኝ ወደዚያ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ማን በነገራቸው አለች መልአኩም አመቤቴ ቡርክት ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኖራልና ለአንቺም ከአንቺ በኋላም በቃል ኪዳንሽ ለሚታመኑ አትፍሪ አላት ከዚህም በኋላ ወደ ቦታዋ መለሷት።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለ ኋጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች እንደ ዛሬይቱም የካቲት ዐሥራ ስድስ ቀን በጎልጎታ ቦታ ቁማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር አባትህ በክርስቶስ ስምህ ከአንተ ጋርም ህልው በሆነ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ አማፅንሃለሁ ዓለም ሁሉ ሊሸከምህ የማይችል ሲሆን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተሸከመችህ ማሕፀኔ አማፅንሃለሁ ልጄ ሆይ ያለ ሕማም ያለ ድካም ከእኔ በመውጣትህ በመወለድህ በአሳደጉህ ጡቶቼ በሳሙህ ከንፈሮቼ በአቀፋህ እጆቼ ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ አማፅንሃለሁ ። በውስጡ በተኛህበት በረት በተጠቀለልክበት ጨርቅ አማፅንሃለሁ የምወድህ ልጄ ሆይ በልቡናዬ ያለውን ሁሉ ትፈጽም ዘንድ የልመናዬን ቃል ሰምተህ ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ወዳንተ ፈጽሜ እማልድሃለሁ።

የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ እነሆ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ከእርሱም ጋር አእላፍት መላእክት አሉ በዙሪያውም ሁነው ያመሰግኑታል እርሱም እናቴ ማርያም ሆይ ምን ላድርግልሽ አላት እመቤታችንም ለተወዳጅ ልጅዋ እንዲህ ብላ መለሰችለት ልጄ ወዳጄ ሆይጌታዬና ፈጣሪዬ አለኝታዬና መጠጊያዬ በእናቴ ማሕፀንም ሳለሁ ባንተ ጸናሁ አንተም ጠበቅኸኝ ሁልጊዜም ስም አጠራሬ አንተ ነህ።

አሁንም ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ እኔም አገልጋይህ የምለምንህ ይህ ነው መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ወይም የተራቆተውን ለሚያለብሱ የተራበውን ለሚያጠግቡ የተጠማውንም ለሚያጠጡ የታመመውን ለሚጐበኙ ያዘነውን ለሚያረጋጉ የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ድንግል ማርያም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(
#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
"#በፈረሰ ልብ የሚገነቡ ከተሞች የቀን ጉዳይ እንጂ ፍርስራሽ መሆናቸው አይቀሬ ነው"
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
'ተንሥእ ወሑር ኅበ ነነዌ ሀገር ዐባይ -
ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ"
ዮና ፩፥፪
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት፤
መንፈሳዊ ተልእኮ ተቀብላችሁ በየተሰጣችሁ ጸጋ በተለያየ ስፍራ ሆናችሁ የምታገለግለ‐ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤
በመንፈስ ቅዱስ ልደት የከበራችሁ ምእመናን ወምእመናት ልጆቻችን በሙሉ፤ ዘመንን በዘመን እየተካ፣ መዓቱን በምሕረት እየመለሰ የሚያኖረን እግዚአብሔር እንኳን ለ2016 ዓ.ም ጾመ ነነዌ አደረሰን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት የሰው ልጆች በኃጢአት በወደቁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ የሁሉ አባት በመሆኑ ተወልዶ ብልጫ የለም" እንዲሉ ከእስራኤል ውጭ ወዳለችው ነነዌ ነቢዩ ዮናስንና ነቢዩ ናሆምን ልኳል። በበደል ውስጥ ሆነው ቢጾሙም ሆነ ቢጸልዩ ጸሎቱ ድል የሚነሣ መሥዋዕቱም የሚያስምር አይሆንምና፡ ንስሐም ለድሀና አቅም ለሌለው የሚሰበክ ሳይሆን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያደፈ ሁሉ የሚጠራበት የሕይወት መስታወት ነውና የሕይወት ትንሣኤ በሆነው ንስሐ ነነዌን ለማንሣት ዮናስ ወደ ንጉሡና ወደ ሠራዊቱ የንስሐ ሰባኪ ሁኖ ተልኳል።

ነነዌ ከተማዋ አድጎ፡ ልማቷ ቢሰለጥንም እግዚአብሔር ግን የተመለከታት ፈርሳና ተበላሽታ ነበር፡፡ በፈረሰ ልብ የሚገነቡ ከተሞች የቀን ጉዳይ እንጂ ፍርስራሽ መሆናቸው አይቀሬ ስለሆነ ዛሬ ነነዌ ከታሪክ መዝገብ ላይ ብትሰፍርም በዓይን ግን የምትታይ አይደለችም። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የነነዌን ጾም ያወጀችው ዓመት ሙሉ የተጣላ በነዚህ ሦስት ቀናት እንዲታረቅ፣ ሲካሰስ የሚኖር ሕዝብም ወደፈጣሪው በንስሐ እንዲመለስ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ነቢዩን ወደ ነነዌ ሲልከው፡- “ተነሥተህ ሂድ" ማለቱ በበደል የሳተን በሩቅ ሆኖ መተቸት መንፈሳዊ ተልእኮ ባለመሆኑ ተነሥተን ብንሄድ፣ መንገድ አጋምሰን ወገኖቻችንን ብንፈልግ ሁሉንም ለንስሐ ማብቃት እንደምንችል ሲያስተምረን ነው፡፡ ለመነሣት ስንፍናንና ፍርሃትን ድል መንሣት ያስፈልጋል። ለይቅርታ ስንነሣ ትዕቢትን እናሸንፋለን። ፉክክርን እናርቃለን። ለጋራ ሀገራችን የጋራ መፍትሔ፡ ለጋራ ቤተ ክርስቲያናችን የጋራ መድኃኒትን እናገኛለን።

በሌላ በኩል አምላካችን እግዚአብሔር በደለኛይቱን ከተማ ታላቂቱ ከተማ በማለት ሲጠራት ሕዝቡንም ግራና ቀኙን የማያውቅ በማለት ራርቷል። እግዚአብሔር አምላክ አክባሪ፤ አዛኝ፡ በደለኛውንም በክብር እንጂ በውርደት የማይጠራ አምላክ ነው። እኛም ይህንን የነነዌን ጾም ስንጾም በአንድ በኩል እንጀራን የተራቡ፣ በሌላ በኩል ሰላም የተራቡ ወገኖች ስለአሉን ወደ እነዚህ ወገኖች የንስሐን ስብከት፣ የማጽናናትን መልእክት ይዘን መሄድ አለብን። በተጨማሪም ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን፡ በረሃብ፣ በመታረዝ፣ በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን የመከራ ማቅ በሕሊናችን ተሸክመን ስለጸሙ የተውነው የዕለት ቊርሳችንን ለእነርሱ ሞትን ማባረሪያ እንዲሆን ልንፈቅድ ያስፈልጋል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

ይህንን የነነዌ ጾም ልንቀበል ዋዜማ ላይ ባለንበት በዚህ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ጥንታዊ ከሆኑት ገዳማት አንዱ በሆነው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኙ፣ ዓለሙን ትተው በፈቃዳቸው ረሀብተኛ እና ጥማተኛ ሆነው ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ መነኮሳት ጫካው መኖሪያችሁ፣ ዳዋው ልብሳችሁ፤ ቅጠሉ ምግባችሁ መሆን አይችልም ተብለው የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎንጭተዋል፡፡ እነርሱ በሥጋ እየሞቱ እኛም በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል፡፡
ይህ ለእነርሱ ክብር ቢሆንም ለቤተክርስቲያን ግን ታላቅ ደወል ያሰማ ክስተት ነውና ውሉደ ክህነት ቤተክርስቲያናችሁን የምትጠብቁበት፣ የመከራውን ማዕበል ለማለፍ በመንፈሳዊ ፍቅር አንድነትን ማጽናት የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም ታላቅ ሀገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጸማችን፣ ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ለሀገር ደኅንነት፡ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን፡

እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልእክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ || ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ
የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም
#የዐብይ_ፆም_የመጀመሪያው_ሳምንት_ዘወረደ ( ሕርቃል) ይባላል፦ ✟ ✟ ✟

   ✟«ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው።

👉🏾ይህም
#ጌታችን_መድሃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን #ከድንግል_ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ #ከቅድስት_ድንግል_ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ( #ዮሐ
፣3÷13-21)

፠ ✟
#እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ #እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”/ ገላ4÷4 / እንዳለ #ሐዋርያዉ_ቅዱስ_ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

፠ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን «ሕርቃል» የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ (
#ዘፍ ፣ 3÷ 14)ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡

፠ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው።

፨እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።

✟ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፫ 


#የጾም_ጊዜያችሁን_ከእኛ_ጋር_የትኛውም_ጊዜ_በላይ_ተጠናክረን_መጥተናል_ለወዳጆቾ_ያካፍሉልን
​​«ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው?»
ክፍል 1

እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ?
የቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሥርዓቱ በልኬት እና በምክንያት የታጀበ ነው። ጾምን ስንመለከት አብዛኞቻችን በተለምዶ ሰዓት ሳንጠብቅ (እስከ 3፣ 6፣ 7፣ 9፣ 11 ሰዓታት እያልን) እንጾማለን እንጂ የአዋጅ አጽዋማት የተወሰነ የተገደበ ሰዓት አላቸው።

ፍትሐ ነገሥታችን “ሕማማት እስከ 12 ሰዓት ይጹሟቸው፥ ሌሎቹን አጽዋማት በዓለ ልደት እና ጥምቀት ረቡዕ እና ዐርብ የሚውሉባቸው ካልሆኑ በቀር እስከ 9 ሰዓት ይጹሙ” (ፍት.ነገ አን 15፥565-566)  ብሏል።

የአጽዋማትን ዝርዝር ካስቀመጠ በኋላም በዚሁ  አንቀጽ ቁጥር 572 ላይ ደግሞ “በእነዚህ በታዘዙት ጾሞች ከቀኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፣ ... ከዚህ አብልጦ  የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል፣ ከጥሉላት ምግቦች መታቀብ ካልሆነ በቀር እሑድና ቅዳሜ ግን አይጹሙ” ብሎ ወስኗል።

ዐቢይ ጾም ሁዳዴ፣ ጾመ ዐርብዓ ግን ይለያል። “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ  ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣  ሌሎቹን ሳምንታት እስከ  11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)።

ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።

ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል 👉 በዐቢይ ጾም የተከለከሉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
#ዐቢይ_ጾምን_ለምን_55_ቀን_እንጾማለን?

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የዐቢይን ጾም የቀናት ቁጥር 55 አድርገው ሲወስኑ ያለ አንዳች ምክንያት ሳይሆን በምስጢር ነው። ይሄውም እንዴት ነው ቢሉ ጾሙ 55 ቀን የሆነበት የመጀመረያው ምክንያት በነዚህ በሚጾሙት በ55ቱ ቀናት መሀከል (8 ቅዳሜና፣ 7 እሁዶች በአጠቃላይ 15 ሰንበታት) አሉና እነዚህ ሰንበታት ደግሞ ስለማይጾሙ እነርሱን ጌታችን ከጾማቸው ከ40ው ቀናት ጋር በመደመር 55 ቀናትን እንድንጾም አድርገውናል ።

ሌላውና የዐቢይ ጾምን 55 ቀን የምንጾምበት ሁለተኛው ምክንያት በጾሙ የመጀመሪያና የመጨረሻውን ሳምንታት በመቁጠር ነው። እነዚህ ሁለት ሳምንታት የመጀሪያው ሳምንት "
#ጾመ_ሕርቃል" ሲሆን የመጨረሻው ሳምንት "#ሰሞነ_ሕማማት" ይባለል።

#ሕርቃል የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺህ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺህ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገ*ደ*ለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

በተመሳሳይ በዐቢይ ጾም ከሆሳዕና በኋላ ያለው የመጨረሻውን ሳምንት የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል የምናስብበት ጊዜ ነውና ሰሞነ ህማማት ተብሎ እንዲታወስና እንዲጾም አድርገዋል።

በእነዚህ ከፊትና ከኋላ በገቡት ሁለት ሳምንታት አማካኝነት የጾሙ ቀናት ቁጥር ከፍ ብሏል ማለት ነው። ልክ እንደ ላይኛው ሁሉ እነዚህንም ሁለት ሳምንታት ብናነሳቸው የምንጾመው 40 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።
በአጠቃላይ የዐቢይ ጾምን 55 ቀን አድርገን የምንጾመው ከላይ ባየናቸው ምክንያቶች ነው።

     
🤑💶 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር ለምትፈልጉ በሙሉ❗️🤑💶💰💰

🎯 40% Discount አዘጋጅተውላችዋል


@City_Forex_Ethiopia


𝘾𝙞𝙩𝙮 𝙁𝙤𝙧𝙚𝙭 𝙀𝙩𝙝𝙞𝙤𝙥𝙞𝙖      📞   𝟬𝟵 𝟳𝟳 𝟯𝟯 𝟴𝟱 𝟴𝟲     🇪🇹
𝘾𝙞𝙩𝙮 𝙁𝙤𝙧𝙚𝙭 𝙀𝙩𝙝𝙞𝙤𝙥𝙞𝙖       📞  𝟬𝟵 𝟳𝟳 𝟯𝟯 𝟴𝟱 𝟴𝟲     🇪🇹

ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት
      
👇👇 ይህን ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ   !👇👇


█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸



👆 ይህን ይጫኑት  ይህን  ይጫኑት  ይህን ይጫኑት 👆



🎯 Add Your Channel

👇 ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከፈረጉ ከስር ያለውን ይጫኑ 👇
2024/05/23 07:06:21
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243