Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዕለቱ ሳሙኤል በለጠ መጽሐፉ ላይ ሒሳዊ ዳሰሳ ያቀርባል።
የመጨረሻው ፎቶግራፍ
(The Last Photograph)

ምንም አላውቅም የቡናና የገላ ቀለም መለየት እንደ ቁልቁለት ዳገት ይሆንብኛል ማወቅ የምፈልግ ይመስለኝ ነበር፥ ሳውቅ አንዳንዶቹ እውቀቶች መረሩኝ ፥ ለምን እኔ(ሰው) እንጂ ደሴት አይደለሁም(No Man is an Island) በእርግጥ ማወቅ የሆኑ ትዝታዎች ለሕይወት መዓዛ ይሰጣል! በልጅነቴ ተፈጥሮ እወድ ነበር አሁን በለስላሳ ብርሃን ፥ 'ሚጠመቁ ቅጠሎች
ሕልም 'ሚያልሙ ፥ የቅጠል ጥላዎች አዕምሮዬ ላይ ይመጣል በሸራ ባልስልም ሠዓሊ ሆንኩ...!

ክፍሌ ተቀምጬ ከመዝሙረ ጋር መጣች አብራ(ማናት ደግሞ) ጠረን የሚባል የዕውቀት ዜማ በአፍንጫዬ ነፍስ በኩል ረቂቅ_ዜማውን አዜመ መዝሙረ ወደ ጓዳ ሲያልፍ እሷ አጠገቤ ቁጭ አለች፥ የመጀመሪያ ጠረን ቅርብ ነገር ነው ልብን ያሳያል።

#ብጽፍም_ብጽፍም_ብጽፍም
ከጠረኗ ካልተገናኘ ታሪኳ አይደለም!

ተጫወቱ አጫውታት 'ንጂ መዝሙረ የርቀት ድምጽ ከፍና ዝቅ ካለው ጀረባዋ ከፊቶቿ ምናምን የሚነበብ ነገር አጣሁ ጸጸትና ጸሎት ያማሰለው ደም በስጋ ከቆመ ነፍሰ ስጋ ቃል አይወጣም ያለ ቃል መጽሐፍ...!

ተጫወቺ? እኔ
እሺ ቤቱ ታፍኗል መሰል? እሷ
አጫውታት #ካሜራ_ማን_ናት! መዝሙረ

ኦ! ፎቶ በጣም ዕወዳለሁ እናቴ ካየኸው ፎቶ አንሳው ትለኝ ነበር ዛሬን ለትዝታ ነገን በእርግጥ አይን መስማት አለበት ከማየትም ብላኛለች የት እንደምትቆምም ታውቃለህ ለምስልህ ብላኛለች ያው ለሕሊና ብርሃንና ጊዜ...!

ቡዙ አወራሁ መሰል?
ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!
(ለአንተ ለአንባቢው አዎ)
ግን እኔ ፎቶ ባነሳት አንዲትን ትወደኝ ይሆን?

ልክ አየህ ፎቶ ሥጋ ብቻ አይደለም ነፍስም ይነሳል ነብሮ ነፍስ አንስተህ ማን ሊጠላህ ሃሃሃ ሳቀች በጥርሷ በኩል ወደ ነፍሷ መግባት አማረኝ መዝሙረ ከጓዳ ወጣ ተያይዘው ሄዱ!

1፣2፣3 ቀን ፍቅር ከድንገተኛ መውደድ ተምታታብኝ ጠንካራ ልብ ለመለመ "መወለድ ሕልም፣ ሞት ድንገት፣ ሕይወት ፍቅርም ድንገት" የሚል ማህሌ ፈጠርኩ 4፣3፣2፣1 ቀን ለመውደድ ይበቃል? አዎ በድንገት(በቅጽበት) መውደድ ቁስል ቢኖረውም ቶሎ ይድናል አገራችንንኮ ለሶስት ሺህ አመታት ወደናት ነው የማናድናት...!

ምንድነው ቶሎ መውደድ?
ምንድነው ቶሎ ስፍስፍ ማለት?
ፍቅር?
ሊሆንም ይችላል!

አንድ ቀን መጣች ብቻዋን መዝሙረ የለም አለችኝ ስንገባ መንፈሷ ገብቷል። ደስ ትላለች ትንሽ አውርታ ትሄዳለች፥ ቶሎ እወዳታለሁ ቀጥ ያለች ልቤ ተቆልምማ ትሞቃለች ሕይወትን ፍለጋ ለሐሴት ትፋጭራለች፥ የአዕምሮ ውበት ቶሎ ይወደዳል እነዚህን ፖለቲከኞችን እዝጌር ይሄን ነገር ለምን ነሳቸው? ምነው የአዕምሮ አድማሳቸው ሐምራዊነት አጣ፥ በዛለይ ሩቅ አይደለም የሷ ሩቅ ነው መሰለኝ ልቧም ንጹህ የፈለገችው ባትፈልግስ ሁሉ ይሆንላታል።

አያችሁ ወደድኳት በአንዴ!
እስከ መቼ? አላቅም

ቶሎ መውደድ እውነት ነው? ድሮ_ድሮ እናቶች እንዲህ ተርተው ነበር ደግ ንጹህ አሉ አገር፣ አለም፣ ተፈጥሮ፣ ይወዱታል ምክንያት? በድንገት(Spontaneous) ፍቅር ስላለው ሁሉ ይገዛለታል።

.
.
.

ወደድኳት!

ሁለመናዬ እሷ ጋር ሆነ!
(ስነሳም፣ ስተኛም፣ ስኖርም)

.
.
.
(ግን አላገኛትም!) ቀን ቀን በምናቤ ስተኛ ጠረኗ በደም ሥሬ ይመላለሳል። ደስ ይለኛል ከደም ስሬ ትቀርባለች ከአካሌ ሩቅ፥ 1፣2፣3 ቀን ይሄ ይረዝማል 2፣3፣4፣5፣6፣7፣8 ቀናቶች በመውደድ፣ ባለማግኘት(በደስታ፣ ተስፋ በመቁረጥ) እየፈለጉ፣ አለማግኘትን፣ ተስፋ እያደረጉ፣ ተስፋ መቁረጥን ይሄን ጸጸት ከመልኬ ጋር ፎቶ የሚያነሳ እሱ የመጨረሻው ፎቶግራፍ ይሆናል።
ስትመጪ!

የእግርሽ ኮቴ ከርቀት ይሰማል
(እንኳን እኔ ቀርቶ)
ዓለም 'ርምጃሽን ያውቃል!
(Samuel belete)

When you are coming
Your foot sound
Heard from all roads
Not only from a far city
But also, it heard from all of the world

Ardalan Sarfaraz
171.pdf
4.4 MB
171.pdf
ቀጣዩ አፀድ

ድርሰት:- 'ፍራንዝ ካፍካ
ርዕስ:-The Next Village
ትርጉም:- ሳሙኤል በለጠ
ምንጭ መጽሐፍ:- the hunger artists
ዘውግ :- የአጭር አጭር ልቦለድ

አያቴ እንዲህ ይል ነበር 'ሕይወት አስገራሚያ አጭር---- ነው!' አሁን ነገሩን በትዝታ ሳስታውሰው ከሽበቶቹ አልፎ--- ባለው የአዕምሮ ነቃኔ ክፍል ደጋግሞ ያሰበው ይመስለኛል!

ይታይህ ይለኛል--- ነገሩን ለእኔ ለማስረዳት በምሳሌ ፈረስ እየጋለብክ ወደ ቀጣዩ መንደር ብትሄድ ስለ ቀጣዩ መንደር ታውቃለህ---? መንደሩ አፀድ ይበዛዋል ወይስ እሾህ? ውህብ ሴቶች ወይስ የነገረኛ ሴቶች ጫጫታ በዜማ መንደሩን ያጠለሸዋል? አይታወቅም! አየህ! ማን ምን ያውቃል ሊፈጠሩ የሚችሉ መልካም እድሎች አይታወቁም---!

ይህንን የሰማሁ "እኔ" ነጭ ፈረሴን ኮልኩዬ ወደ ቀጣዩ መንደር ለመሄድ ተነሳሁ በመንገዴ የሚገጥመኝን አላውቅም መንደሩ አጭር ነው ያኛው መንደር 'ረጅም ይመስላል! ሕይወት የአሁን ግልቢያ ናት!° የፈረሴ ኮቴ ደጋግሞ ይሰማል-----!

°በቅርቡ የምንለው እንዴት ዘገየ?
[ከኅያው ገጸ ባህሪዎች መኃል 1]

ስለ አልበርት ከሙ ብዙ ተብሏል ብዙ ተጽፏል በደረሳቸው ቲያትሮችና መጽሐፎች እንዲሁም በፍናፍንት(Absurdity) ፍልስፍናው ዛሬም ድረስ ገናና ነው። The Stranger የተባለው መጽሐፉ በእኛም አገር ገናና ነው ሚፍታህ ባይተዋሩ ብሎ ተርጉሞታል። ዛሬ ከአልበርት ከሙ ገናና መጽሐፍ ከሆነው The Plague መጽሐፍ አንዱን ገጸ- ባህሪ እናያለን! መጽሐፉ በአንድ መቶ ሃምሳ ገጽ የተቀነበበ ሲሆን ወደ ፊልም በሽግግር(Adopt) ተደርጎ ተቀይሯል።

ታዲያ ከዚህ መጽሐፍ ወስጥ አንድ ገጸ ባህሪ አለ አባት ፓኔሎክስ(Father Paneloux) ይህ ገጸባህሪ ዓለም ላይ እየሆነ ያለውን መከራ ያያል ይታዘባል የመከራው ርቀት ቪክቶር ሁግ(Victor-Marie Hugo) ሌስ ሚዘረብል(Les Misérables) ላይ ከገለጸው መከራ አቻ ይሆናል። ፈንቲንና ጎረቤቶቿ ያሳለፉት ሰቆቃ ተመሳሳዩ እዚህ መጽሐፍ ላይ ተተርኳል።

አባት ፓኔሎክስ እንደማንኛውም የሰው ልጅ በዓለም ላይ ያለ ስቃይን የሚመለከት ዓለም ትርጉም 0ልባ(Absurd) የሆነች ሙሉ በሙሉ ምድር የማይረባ ቦታ እንዳትሆን ለመረዳት የሚሞክር ሰው ነው።

አባት ፓኔሎክስ ህይወቱን መሰረት ያደረገና በእግዚአብሔር ላይ ባለው እምነት ላይ የሚሰብክ መምህር ነው። ይህ ማለት በአለም ላይ ያለው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ባለው ዓላማ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርጓል። ነገር ግን አልታመነም ምክንያቱም አልበርት ከሙ The Myth of Sisyphus ላይ የተቃርኖ ሐሳብ አስቀምጧል። "The principle can be established that for a man who does not cheat, what he believes to be true must determine his action." [መርህ ለሌለው ነገሩ ማጭበርበር ነው፥ እውነት ነው ብሎ የሚያምነው ነገር ድርጊቱን መወሰን አለበት።ገጽ-11]


አባት ፓኔሎክስ ወረርሽኙ(በመጽሐፉ የተተረከው) ያስከተለውን ስቃይ ትርጉም ባለው መልኩ ማስረዳት ከቻለ እሱና ተከታዮቹን የሚያዳምጡት እና በመከራቸው ላይ እምነት የሚሹ ሰዎች በእግዜር ማመንን ሊቀጥሉ ይችላሉ። ግን አልሆነም ለምን አልበርት ከሙ ይሄንኑ ጥያቄ The Stranger ላይ አንስቶ ይመስሰዋል። " is essential to consider as a constant point ofreference... the regular hiatus between what we fancy we know and what we really know, practical assent and simulated ignorance which allows us to live with ideas which, if we trtdy put them to the test, ought to upset our whole life"[p-18] ምስኪን አባት ፓኔሎክስ!
የተቃጠለ ግጥም
ንዑስ ርዕስ:- ሥነ - ጽሑፍና ፖለቲካ
[ከኅያው ገጸባህሪያት 2]

ሳሙኤል በለጠ

አንድ

ኅያው ከሆኑ ገጸ-ባህሪያት መምዘዝ ጀምረናል ሁለተኛ ላይ ደርሰናል። በዚህ ክፍል ከአንድ የራዲዮ ድራማ አንድ ገጸ-ባህሪ እንመዛለን ፖብሎ ኔሩዳ ድራማው በፖብሎ ኔሩዳ የእስር ሕይወት ላይ ያጠነጥናል። ፖብሎ ኔሩዳ የዛሬ አርባ አመት ገደማ በፊት ሕይወቱ ያለፈ ገጣሚ ነው።

አንዳንዶች በ21 ክፍለ ዘመን በስፔን ከተነሱ ምርጡ ገጣሚዎች ወደር የማይገኝለት ነው ይላሉ ለማህበራዊ ፍትህ መጉደል(Social injustices) ግጥሞቹ ድምጽ ናቸው ብለው ደምድመዋል ኀያሲያን ኔሩዳ ምንምኳ በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ቢሸለምም የፖለቲካ እንቅስቃሴውም ገናና እንደነበር ታሪኩን ያጠኑ ምሁራን ይናገራሉ ለምሳሌ በ 1936(እ.ኤ.አ) በስፔን የ 'ርስ በርስ ጦርነት መቀስቀሱ ኔሩዳ ፊቱን ወደ ኮሚኒስታዊ አስተሳሰብና ወደ ፖለቲካ አንዲያዞር አስገድዶታል።

የ'ርስ በ'ርስ ጦርነቱ የፈጠረውን ውድመት የባለ ስልጣናቱን ስግብግብነት በደማቅ ብዕር ጻፈ በዚህ ጉዳይ የተብሰለሰለበትን ጉዳይ "our heart in Spain" በሚለው ተከታታይ የግጥሞች መጽሐፉ ገልጾታል። ስለ ገጣሚ ፖብሎ ኔሩዳ ይህንን ካልን ዘንዳ የፖብሎ ኔሩዳ የእስር እንግልት የሚዳስስ የራዲዮ ድራማ ገጸ - ባህሪ እንዳስሳለን መሪ ገጸ-ባህሪው ፖብሎ ኔሩዳ ሲሆን በድራማው በርካታ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።

ኔሩዳ በግዛት በተያዘበት ክፍል ውስጥ ሁለት ወታደሮች አሉ ኔሩዳ የጻፋቸውን ግጥሞች እያዩ በግማሹ ይዘባበታሉ ከፊሎቹን ደግሞ ያቃጥሏቸዋል። ኔሩዳን ያጋዘው ወታደር በአንድ ግጥም ይገረምና እስኪ አንብበው ብሎ ኔሩዳን ይጠይቀዋል ኔሩዳ ቀጠለ:-

ኒክሰን፣ ሲኖቼ ከርሳም!
(ጅቦቹ - በማበር)
ደማችንን- አፍስሰን
(ስጋችንን በሳት ጠብሰን)
እስከ መስከረም ስልሳ
አምስት እስከዛሬ መራራ ዕለት
(ያ! ቆየናትን የድል ታሪክ)
ዘንጥለው - ቢበልቱት
ያውለበለብናትን - ባንዲራ
(አይጠ መጎጦች በጋራ)
ቦጫጭቀው - ሊያነዱብን
(ቢተባበሩብን)
በላቲን አሜሪካ - ሠፊ እርሻቸው
በጉቦ ወሲብ - ሰክረው
አብደው - የከሃዲያንን
( 'ርካሽ አንጎል ገዝተው)
(ደም ሱስ ጠመንጃቸው)
በሰማዕታት - ደም 'ረግቶላቸው
የአሜሪካን - ያንኪ ቡራ
(የሞት መላክቶችን ሲራራ)
ዘማ ነጋዴው - ሁሉ ሲኩራራ
በርሃብ ወረንጦ
(ሕዝቡን - ተልትሎ)
ጣይ ሕጋቸውን
(ካሳሪጋ - ሲነድፉበት)
በውል ጎዳና በለሊቱ
(ምድር ምሽሮ መሳፍንቱ)
በተኩላዎች - ተተኩ
መሳፍንቱ ተርበተበቱ!

አጋዡ በኔሩዳ ግጥም ሳቀ ተሳለቀ፣ ተዘባበተ፣ ለአጋዡ የሚያቃጥረው አንድ ገጸ ባህሪ ሌሎች ግጥሞችን እንዳገኘ ለአጋዡ ይነግረዋል። "አምጣቸው" ይለዋል። ሲያያቸው የፍቅር ግጥሞች ናቸው የፍቅር ግጥምማ አናቃጥልም ሲል ድራማው ያልቃል here it is the ideal deal ጭቆና ግፍ የመሪዎች በደል ከዓለም እስካልጠፋ ድረስ ይሄ ግጥም መቼም ሊቃጠል አይችልም።

@Poetry_Foundation_&_Poetry_ Magazine
ስድስት ትንግርታዊ የሐረር ቱውፊታዊ ታሪኮች
- ሳሙኤል በለጠ

መነሻ

ጋሽ ዓለማየሁ ገላጋይ ጎንደር የሕልሙ ከተማ ብትሆንበት እንዲህ አለ "ጎንደር የሕልሜ ከተማ ናት፤ ምናልባትም ከልደት በፊት-በፊት የማውቃት፤ ለአንዱ ጀግና አድሬ የተዘዋወርኩባት፣ ወይም በክፋት ያስጨነኩባት …" እያለ ይቀጥላል። እኔም ለሐረር እንዲህ ነው የሚሰማኝ በመንፈስ የነቃች ይመስለኛል። ከዓለማዊ መልክ የሸሸች በመንፈሳዊ ሥልጣኔ ያ' በበች ትመስለኛለች። በሥራ ምክንያት የተለያየ አገር ብሄድም ሐረር እንደ ሄድኩ ስገባ ልቤ ደንገጥ ብሏል። ትመስለኛለች ያልኳት ሐረር ገዝፋ ታየችኝ። ስልጣኔ ከቤት ይጀምራል፤ ጥንታዊነትና ዘመናዊነትን ከጥልቅ ትርጉም ጋር አቅፎ የያዘው ኪነ-ህንፃዊ አሰራሩ/architectural style፣ ቴክኖሎጂ ባልተወለደበት ዘመን የተጠቀሟቸው ለጤና ስሙም የሆኑ ንጥረ-ስሪቶች/materials፣ የእስልምና ኋይማኖትና የሐረሪ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑ ልዩ እሴቶች/values ኪናዊ ስብጥር ከብዙ ጥቂት መገለጫዎች ናቸው። ቤቱ የተቀባው ቀለም ሲታይ ዝምብሎ ይመስላል - ታሪኩ ሲነገር በቀለሙ ውስጥ የቁዛሜ ታሪክ ይዟል። እነዚህ የጥንት ስልጣኔያቸውን የሚናፍቁ የሚመስሉ የቤት ታሪኮች እልፍ ታሪኮችን ይዘው የቤቱ 'ዲካው'(ጣሪያው) ላይ ባሉት የዋንዛ ርብራቦች ቁጥር ልክ ታሪካቸው አይቆጠርም፤ አይቋጭም ።

የሐረሪ ሕዝብን ለመግለጽ ስለተቸገርኩ የባላዝ ሚዲያ አዘጋጅ የነበረው ግሊን ባክ በአንድ ወቅት ያለውን ልጥቀስ "ለአንተ መልካም ነው! ልብ አለህ አይደል? ነጻ መሆን ትችላለህ ግን ልብህን ከአእምሮህ ጋር አጣምረህ ወግ አጥባቂ መሆን ትችላለህ።" (Good for you, you have a heart, you can be a liberal. Now, couple your heart with your brain, and you can be a conservative.)
የሐረሪ ሕዝብ ነጻ ሕዝብ ነው። እዛ ያሉ ነፍሶች ልብና መንፈሳቸው ያ'ወሩ(ስሙም) ናቸው። ከልብ ለልብ የሚኖሩ ለልብ የቀረቡ ነፍሶች ከተማይቱን ሞልተዋታል።

የሥነ ጽሑፍ ኀያሲው ቴዎድሮስ ገብሬ "ቱውፊታዊ ታሪኮች የሰውን ነገረ ፍጥረትና የኅላዌ እንቆቅልሾችን (ontological and cosmological questions) ለተመሰቃቀለው ዓለም ሥርዓት (cosmic order) ለማበጀት የባተለበት እምነታዊና ፍልስፍናዊ ጥበብ ነው" ሲል ቱውፊታዊ ታሪክን ይገልጸዋል። እኔም በሐረር ቆይታዬ ያስደነቁኝን ቱውፊታዊ ታሪኮችን ላስከትል።

1. የሐረር አመሰራረትና ስያሜ

የዛሬይቱ ሐረር ከመመስረቷ በፊት ከአንድ ሺህ አመት በፊት በሰባት ጎሳዎች የሚመሩ በሰባት መንደሮች የተከፋፈለች ነበረች። ዊኪፕዲያ የታሪክ መዝገብ እንደሚለው ሐረር በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በተለምዶ ሼኽ አባድር በሚባሉ በመደበኛ ስማቸው ሸኽ ኡመር አል-ሪዳ (Abadir Umar ar-Rida) በተባሉ ብጹዕ የሐይማኖት አባት ከርሳቸው ጋር አራት መቶ አራት የሐይማኖት አዋቂና መምህራንን በማስከተል የሳውዲ ግዛት ከሆነችው ሂጃዝ ተነስተው የዛሬይቱ ሐረር እንደደረሱ በአፈ ታሪክ ይነገራል።

እነዚህ ሰባት የተከፋፈሉ ስምምነት ያልነበራቸው ጎሳዎች በማሰባሰብ የአንድ ነገድ ግንድ ጎሳዎች የሆኑ አካላት በሐይማኖትም በስነ-ምግባርም መለያየት አግባብ አይደለም በማለት አሰባስበው በማስታረቅ፣ በወንድማዊ ክር በማሰርና በማዋደድ አንዲት ጠንካራ መዲነቱል ሐረር እንደመሰረቱ በሐረር ቃለ ቱውፊት ብሎም በታሪክ መረጃዎች በወርቃማ መልኩ ተጽፏል።

2. የአጥንት ትውፊት

በጥንት ዘመን ሐረር ላይ ሥጋ ከተበላ በኋላ የስጋ አጥንት አይጣልም። ምክንያቱ ደግሞ፤ አንድ፣ አጥንት የመልካም ጂኖች ምግብ ነው፤ ሁለት፣ በአጥንቱ ውስጥ ክፉ ጂኒ(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ይኖራል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ አጥንቶቹ ተሰብስበው በጀጎል ግንብ ዙሪያ ይቀበራሉ። የአጥንቱ መቀበር በርካታ ጥቅም አለው አንዱና ዋነኛው ጥቅም ሐረር በምስጥ እንዳትወረር ይጠብቃታል ተብሎ ይታሰባል። ሌላው ዝማሚት(ምስጥ) ወደ ሐርር ግንብ እንዳይገቡ ይከላከላል። ከገቡ ግንዶች፣ ጥንታዊ መጽሐፎች ስለሚያበላሹ የተቀበሩት አጥንቶች እንደ ተከላካይ ሆነው አገልግሎት ላይ ይውላል።

3. የሐረር ጅቦች

ጅቦች በባህሪያቸው የሞተና የበሰበሰ ነገር እንደሚመገብ(Scavenger Animal) እንደሆነ የገባቸው የሐረሪ መንፈሳዊ አባቶች ከሐረር በሮች ልክ 'ወራባ ኑዱል' የተባለውን በር ለጅብ መግቢያና መውጪያ አበጁለት። ጅብም የማይታይ ጅን(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ማየት ስለሚችል እነዚህን እንዲሁም በየቤቱ የምግብና የስጋ ትርፍራፊ በልቶ ይወጣል። የሐረር ጅብ በአካል ያለን ፍጡር ስለማይበላ የሐረር መንፈሳዊ አባቶች ጅብን እንደ የቤት ድመትና መሰል እንስሳ አላምደዋል። በሰውኛ መጥሪያ ስሞች ጠርተው በእጅና አፍ ይመግባሉ። በየአመቱም ለጅቦች የሚዘጋጅ ልዩ ገንፎ የማብላት ትርኢተ-ድርጊት/festival አላቸው።

4. ጫት በሐረር

የዛሬን አያርገውና በጥንቱ ሐረር ጫት ጥቅሙ ለተከበረ ድርጊያ ነው የሚውል የነበር። ለስራ፣ ለጸሎት፣ ለኋይማኖታዊ አሰላስሎት/contemplation እንዲሁም ለጠቃሚ የጉልበት ስራ ነበረ የሚቃም። የመቃሚያ ሰዓት ደግሞ ፀሐይ ወጥታ አምስት ሰዓት ሲሆን ቆይታውም ፀሐይ እስኪከር ይሆናል፤ እንዳ'ሁኑ ምሳ በልቶ እስከመፍዘዝ መወዘፍ አልነበረም። ከዛ ገበሬ የሆነ ወደ እርሻው፣ ነጋዴ ወደ ንግዱ፣ የኋይማኖት ሼሁ ወደ ንባብና ወደ ፀሎት ይሄዳሉ። በዛች ሰዓት የቃሟት አንዲህ ፍሬ ጫት እስከ ለሊት ኢሻ(የቀኑ መጨረሻ ስግደት) ድረስ ሃይ/ህያው/ንቁ አድርጎ በማዝለቅ ጠሃይ ጠልቃ ጨለምለም ሲል በድካም ወደ መኝታቸው እንዲያመሩ ምትሃታዊ ጉልበት ይቸራቸዋል።

5. የሐረር ባለከለር ድመቶች

ሐረር ድንቅ የድመት ቃለ ቱውፊት አለ። በፊት የሐረሪ ባህላዊ ቤቶች ከአፈር ነበር 'ሚሰሩት። ሐረር ግንብ ዙሪያ ግንብ ውስጥም ጭምር እባብን ጨምሮ የተለያዩ ተሳቢ እንሰሳት ነበሩ። ስለዚህ እያንዳንዱ የሐረሪ ቤት ውስጥ የሚገኙ ድመቶች ስራ ይህን እባብና አይጦች ለመከላከልና ሌሎች ምስጢራዊ ሚስጥሮችን ያጨቁ ግብሮችን የሚያጎናፅፉ የሚያማምሩ ድመቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ!

6. የማይሞቀው የማይቀዘቅዘው የሐረር አየር

ሐረር ለሰው ልጅ እጅግ ተስማሚ አየር አላት። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪና ተጓዥ የሐረርን አየር እንዲህ ይገልጸዋል "ሐረር የምትሞቅ የማታቃጥል፤ የምትቀዘቅዝ የማትበርድ አየር(warm but not hot, Cool but not cold)" ያላት ከተማ ናት ይላል። ጥንት ሐረርን የመሰረቱ የሐረሪ በመንፈሳዊ ትምህርትና ጥበብ/ religious wisdom የመጠቁ አባቶች የከተማዋን ቦታ ሲወስኑ ለጤና ጥሩና ተስማሚ አየር እንዲኖራት በማሰብ ሙዳ ስጋ ቆርጠው ዛፍ ላይ ሰቀሉ፤ በነጋታዉ ሲመጡ ስጋው የተሰቀለበት ከባቢያዊ አየር ሙቀት ቢሆን ስጋው ይበላሻል፤ እጅጉን ቀዝቃዛ ከባቢያዊ አየር ካለ ደግሞ ስጋው ይደርቃል። የአሁኗ የሐረር ጂኦግራፊያዊ መገኛ ስፍራ በዚህ ጥበባዊ ስሌት ከብዙ የሙከራ መነሳትና መውደቅ/try and error በኋላ ስጋው ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ሳይበላሽና ሳይደርቅ በነበረበት ቆይቶ ምንም ለውጥ ባለማሳየቱ ለሰው ልጆች ተስማሚ አየር እንደሆነ ተምኖበት እዚህ ቦታ ሐረር ትቆርቆር ብለው ሐረርን መሠረቱ!
መቀንበቢያ

ባይለየኝ ጣሳው የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ባሳተመው የአባይን አፈ-ታሪኮች ጥናት መፅሓፍ ላይ ያሰፈረው አንድ ሐሳብ የአባይ ወንዝ ደራሲዎችና ገጣሚዎች እንዲሁም ሠዓሊዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ይላል። ለሐረር ብዙ ተዘፍኗል። በየአይነቱ ተዚሟል! አዲስ ዜማ ያለው ዘፈን መፍጠር አይቻልም! ግና ሐረር ስትታይ ሐረር ናት! ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊ ባኽዳድ! የምትንቦገቦግ የስልጣኔ አርማና አሻራ! ውስጧ ሲገባ ዓለም ናት! በአንጻሩ ስለ ባህልና ሥልጣኔ ሲወሯ አፍ መፍቻ ቋንቋችን አለመሆኗ ያስቆጫል።
2024/06/08 00:45:42
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243