Telegram Web
ጥያቄ
"""""""""""""""
ለሰላም መዘመር
እምነቴ ነው ላለኝ
ለዛ ባለ ጦማር
ጥያቄ ነበረኝ።
የተናገርከው ቃል
ፅንፍ እውነት ካለበት
ብዕር ይጣላል ወይ
ጠመንጃ ለማንገት

ብላችሁ በሉልኝ።

ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
#እንኳን_አደረሳችሁ🌼

ለመላው የገጼ ተከታታዮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም አደረሳችሁ።

ስኬታማ አመትን ተመኘሁላችሁ።

🌼መልካም አዲስ አመት።🌼

🎖
@cekuaa🎖
🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊
@poemers
ለጁምኣችን!
💛

'ጦርነት' ማለት ምን ማለት ነው? (እውነተኛ ፍቺው?)

ጦርነት ማለት፦

"አሳምረው የሚተዋወቁ፣ የሚጠላሉና ቅራኔያቸውን በሠላም መፍታት ያልቻሉ፣ ዕድሜያቸውን ያመነዠኩ ሰዎች - የማይተዋወቀውን፣ የማይጠላላውንና ቅራኔውን በሠላም ለመፍታት የማይገደውን ወጣት፣ በሠላም ከተቀመጠበት ከሞቀ ቤቱ ጠርተው፣ እርስበርሱ የሚያጨፋጭፉበት የተረገመ መንገድ ነው"

"War is an abominable situation in which old people, who knew each other, hate each other, and failed to solve their problems peacefully, would drag the young people, who do not know each other, who do not hate each other, and who are willing to make peace with each other, to kill each other."

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
"በአፍሪካ የትምህርት ስርአት እንግሊዝኛ ቋንቋን መማር ግዴታ ሲሆን ግብርናን መማር ግን ምርጫ ነው፡፡ ለዚያም ነው እንግሊዝኛ ተናጋሪ ረሀብተኛ የሆንነው!" — ሮበርት ሙጋቤ

አየህ ቋንቋቸውን የሚያስተምሩህ ትእዛዛቸውን እንድትሰማ ነው። እንግሊዝኛ ቋንቋቸው ሆድህን አይሞላ፣ ረሃብህን አያስታግስ። ደግሞም እንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ አይደለም፤ የአውሮፓ ታሪክ፣ የምእራባውያን ፍልስፍና ወዘተ ብዙ ኮተቶችን ትማራለህ። አንድ ቁራሽ እንጀራ ለመብላት ጠቅሞህ አያውቅ። የአፍረካ ትምህርት የሚፈጥረው የተማረ ደንቆሮ ነው።

ትምህርት ኑሮን ካላሻሻለ፣ አመለካከትን ካልሞረደ፣ ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ ምኑን ትምህርት ሆነ። ግቡ መመረቅ፣ ጋዋን መልበስ፣ በእንግሊዝኛ የበቀቀን ዲስኩር ማድረግ አይደለም። የማህበረሰቡን ኑሮ መቀየር ነው።

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
ረምሃይም ኢትዮጵያዊ ቀለም  ፤  የሐበሻ ጦማር
@YEHABESHA_TOMAR     @REMHAI
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
cover by Jone

ሆዴስ ማን አለው

@poemers
ነገን እንጃ ግን "አይዟችሁ!"

በአድዋ ጦርነት የጣልያን ወታደሮችን ያስደነገጠ ነገር ነበር::

የተጠመደ ቦንብ ላይ ለመውደቅ ውድድር የገጠሙ
ሐበሾችን ተመለከቱ::
መተኮስ ችሎ ጠላትን ባይጥል ግን ደረት በመስጠት የሚወድ ገበሬ ምነው ቢሉት "ጥይት ማባከን" ይላል::

ሌላ ጉምቱ ተኳሽ እንዳይፈነዳበት ፈንጂ ላይ በመውደቅ ማምከን ::
"እነዚህ ሀበሾች እብዶች ናቸው" አሉ::

ፍቅርን እንደዚህ ሲገለጥ አይተውት አያውቁምና::

ግን ሐበሾቹ አንድ ነገር ገብቷቸው ነበር:: "በመሞት መግደልን"

እኛም እንዲቀር የምንጠብቀው መከራ የለም እንድንችለው እንጂ::

ሸክም ካልቀረልን ትከሻችንን እናስፋ::
👉 እግዚአብሔርን እንታጠቀው!
👉 ለፈሩ ሁሉ መከታ እንሁን::
👉 ለተጨነቁ አለሁ እንበል::

ከኛ የሚጠበቅብን አንድ ነገር ነው:: እሱም "አንድ" መሆን::

ነገን እንጃ ግን "አይዟችሁ!"

ኤልያስ ሽታኹን
What is Nihilism ብለን ብንነሳ ቀላሉ ገለጻ ይህ ነው.. the rejection of all religious and moral principles, in the belief that life is meaningless ሕይወት ትርጉም የለሽ እንደሆነ በማመን ሁሉንም ሃይማኖታዊ እና ሥነ ምግባራዊ መርሆች አለመቀበል። Nihilist የሆነ ሰው የኒሂሊዝም አማኝ ነው ትርጉሙም በጥሬው "nothingism/ምንም" ማለት ነው።  በምንም ነገር አያምኑም ህይወት ትርጉም እንደሌለው መግለጽ እና ሁሉንም የሞራል እና የሃይማኖት እሴቶችን እንዲሁም የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተቋማትን አንቅረው ይጥላሉ። ይህ ጉዳት አለው ለሚለው ጥያቄ ፅንሰ ሀሳብ ይነሳበት እንጂ personal Attitude ነው። በግላዊነት ላይ ያለ ማንኛውም አመላከከት ወይ መጥፎ ወይ ጥሩ አልያም 'ምንም' ሊሆን ይችላል።


ከላይ "What is Woman" በሚል መነሻ Nihilism ጠቅሼ አብራርቻለሁ። እኔ ግን ከዛ በላይ feminism ያስፈራኛል ምክንያቱም ምንም ከመሆን በላይ የተሳሳተ አመለካከትን የሙጥኝ ብሎ ስለያዘ ነው።

What is feminism¿ Quite simply°°

feminism is about all genders having equal rights and opportunities. It's about respecting diverse women's experiences, identities, knowledge and strengths, and striving to empower all women to realise their full rights.

እና ይህ የፌሚኒዝም እንቅስቃሴ የሴቶችን ማኀበራዊ ምርጫን በመዳሰስ በምዕራቡ ማህበረሰብ ላይ ለውጥ አምጥቷል።  የበለጠ የትምህርት ተደራሽነትና ከወንዶች በበለጠ ክፍያ፤  የፍቺ ሂደቶችን የመጀመር መብት። እርግዝናን በተመለከተ የሴቶች የግል ውሳኔዎችን የመወሰን መብት (የወሊድ መከላከያ እና ፅንስ ማስወረድ ጨምሮ) ፌሚኒዝም የነዛው ፕሮፓጋንዳ ነበር።


የዚህ አብዮት ቀስቃሽ ማናት Mary Wollstonecraft በ1792 “A Vindication of the Rights of Woman” በሚል ርዕስ ባሳተመችው መፅሐፏ የመደብ እና የግል ንብረት በሴቶች ላይ የሚደርስ አድልኦ መሰረት ነው ስትል እና ይህ ክፍፍሎሽ ሴቶች ከወንዶች እኩል እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ቀስቅሳለች። ሴቶች የሚኖሩት ወንዶችን ለማስደሰት አይደለም ብላ ተቃውሞ አስነስታለች። ሴቶችና ወንዶች በትምህርት በሥራ እና በፖለቲካ እኩል ዕድል እንዲሰጣቸው ሐሳብ ደጋግማ አቅርባለች።ብዙዎችም የ feminist አስተሳሰብ መስራች አድርገው ይመለከቷታል።

ከዛ በኋላ ብዙዓነ እንስት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል ወንዶችም አድምጠዋል። ነገር ግን የዚህ ሁሉ ትግል ውጤት እኩልነት አይመስለኝም። ለምን ቢባል ወንዶች በፈጠሩት አለም በሰሩት ቤት ሴቶች የይገባኛል ጥያቄ ብቻ ነው ያነሱት ማንሳት ብቻ ሳይሆን የተዋጉት። 'Why¿' means efficiency and effectiveness እናም ወንድ በፈጠረው '/የስራ ዘርፍ/ፖለቲካ /Nihilism/capitalism/socialism/ Feudalism ውስጥ እኩል የይገባኛል መብት ፌሚኒዝም ነው።

በርግጥ አብዮት አብዮት የሚሆነው ቀድሞ ያለውን ስርዓት ንዶ አዲስ ስርዓት ሲያመጣ ነው። ሚስስ ሜሪ ግን ያደረገችው ቀድሞ ባለው ስርዓት ላይ የስም ለውጥ ብቻ ነው።

በቀላሉ ምን መሰላችሁ ሴት እንደሴትነቷ ሳይሆን የእርሷ ተቃራኒ ጾታዋ የሚያደርገው አደርጋለሁ የሚል የብልጭታ ሀሳብ Touch of madness ነው 😂


                 What is feminism?
   'እንደወንድ ለመሆን የምትጥር ሴት!'


@rasnflega
20231101_095902.aac
7 MB
ርዕስ : ዱላው
ምንጭ : የመኝታ ቤት ሚስጥሮች
ፀሀፊ : እንዳለጌታ ከበደ

@poemers
ርዕስ : የመስዋዕት ልጆች
ፀሀፊ : አሌክስ አብርሀም
ምንጭ : ከዕለታት ግማሽ ቀን


@poemers
@poemers
20231101_101405
Your recordings
ርዕስ : እናትና ሚስት
ፀሐፊ : እንዳለ ጌታ
ምንጭ : የመኝታ ቤት ሚስጥሮች


@poemers
@poemers
ከአንዲት ቆንጆ ልጅ ጋ ነበርኩ። መኪና ውስጥ ነበርን ፒዛ እየጋበዝኳት አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት

ቢል ይዞ መጣ

እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ
መልስ መጠበቅ ጀመርኩ አልመጣም ጠበኩት አልመጣም ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ

(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው )

ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ

"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው "አልኩት

"የሰጠኸኝ አራት መቶ ነው ሂሳቡ ደሞ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ ( ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው )

ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው ።

ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት

እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ

ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።
ከታሪክ ማህደር
"
"
"
"ጊዜው አጤ ቴዎድሮስ የእንግሊዝ ወታደሮችን ሊ'ጣሉ ወደ መቅደላ የሚሄዱበት ጊዜ ነበር። እናም በዚህ ጊዜ በመንገድ ላይ ሳሉ ሠራዊቶቹ የአንድ ሰውዬን ከብት እና ሚሽት ይነዱበታል። በዚህም ጊዜ ሰውየው ለአቤቱታ ከአጤው ፊት ይቀርባሉ። ከዚያም፤
" ኸረ ፈጣሪ ተው ምን በደልኩህ" ሲሉ ወደፈጣሪያቸው ፀለዩ ፤ አጤው" እንዴት ስለኔ ወደ አምላክህ ታማርራለህ? ወይስ እንድሞት ትወድዳለህን"? ሲሉ ሰውየውን ጠየቁት ፤ ሰውየውም መልሶ " ተዉ ጃንሆይ አያስጎመዡኝ" ብሎ መለሰላቸው ይባላል። አጤ ቴዎድሮስም የሰውየው መናገር ከሀዘን እና መበሳጨት የመጣ ነው በማለት አለፉት..................."


@poemers
@poemers
@poemers
@poemers
@poemers
"BE THE CHANGE YOU WANT TO SEE IN THE WORLD"....
"
ብርቅዬ አባባል አይደል? ብዙ ማውራት እንችላለን። ከነዚህ ብዙ ነጥቦች እስቲ ስለአንድ ነገር እናውራ።
"
"
በዚህች ታላቅ በነበረች፤ አሁን ላይ ከውስጥም ከውጭም በደረሰባት ቡጥበጣ፣ ግፍገፊ ምክንያት፤ ከ5ሺህ አመት በላይ ታሪክ ያላት፤ አሁን ግን ተቦጥቡጣ ተቦጥቡጣ የ 18አመት ሸንቃጣ ችክ የምትመስለዋ ሀገራችን "ኢትዮጲያ" ላይ በእኛ በልጆቿ የሚዘወተሩ አባባሎች አሉ።
....."እዚህች ሀገር ላይ የህግ የበላይነት የለም"!!
......" ሁሉም ያው ነው። ህዝቡም፣ መንግስቱም፣ ሀገሪቱም ያው ናቸው። ያበላን ጣት ነካሽ።" አዎ ልክ ነው። ከታሪክ ባንማርም ብዙ አይተናል። የሆነው ሆኖ፣ የተበደለው ተበድሎ፣ የበደለው ተፀፅቶ ተቀጥቶ አምልጦ ... ምናምን ምናምን አልፏል። ይሄ ለኛ የሚጠቅመው አንድ ነገር ቢኖር ስህተታችንን እንዳንደግም ማድረጉ ላይ ብቻ ነው። ከዛ ውጪ ዘመን ያሻገረው በዳይነት እና ተበዳይነት ትርፉ የምፅዐት ቀንን ማፋጠን ብቻ ነው።
ስለዚህ የኔ ጥያቄ፤ አክሱምን ላነፁ፣ ላሊበላን ለገነቡ፣ አድዋ ላይ በዠግንነት ለተዋጉ፣ ጣሊያንን ለ5አመት ሰላም አሳጥተው ለመከቱ፣ ኤርትራን ከኢትዮጲያ ጋር መልሶ አንድ ለማድረግ ለለፉ አብዮተኞች አይደለም። የኔ ጥያቄ የዚህ ትውልድ አካል ነን ለባዮች ነው።
?እስቲ በዚህች ሀገር ላይ አየኖራቹ ለሀገር ሸክም ከመሆን ውጪ ለሀገሪቷ የፈየዳቹት ነገር ምንድነው???????
....ከአንድ የግቢ ተማሪ ጋር እያወራው መምረጥ ስለሚፈልገው (ፊልድ) ጠየቁት። ተማሪውም" የህግ ተማሪ መሆን ነው የምፈልገው" የሚል መልስ ነበር የሰጠኝ። ጥሩ ነው አልኩት። ከዚያም ለምን ህግ መማር እንደሚፈልግ አክዬ ጠየኩት። " ከሀገር ለመውጣት አሪፍ እድል ስለሚከፍትልኝ ነው" ነበር መልሱ።......
ቆይ ቆይ ልቡ ከሀገር ለመውጣት የሚመኝ ህግ አስከባሪ ይዛ ፣ ለኔ ከማለት ወጥቶ ለኛ የሚል ትውልድ ካጣች፣ ሁሉም አማራሪ ከሆነ የዚህች ሀገር ተስፋ ምንድነው።? ወገን ያጣነው እኮ ከዳር ቆሞ ችግር ጠቋሚ አይደለም። ከመሀል ገብቶ ችግር ለመፍታት የሚሞክር እንጂ።

አዎ በሆነ መንገድ በsystemu ምክንያት የሆነ ነገር ሆነሃል። አዎ ለሆዳቸው ባደሩ አጋሰሶች ምክንያት ማግኘት የሚገባህን ተነጥቀሀል። ግን ደግሞ አስተውል የደረሰብህን ያደረሱብህ ሰዎችም አንድ ጊዜ ላይ በአንተ ላይ የደረሰው ደርሶባቿል። ሀገሪቷን የሞላው እኮ አኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ ነው።
.... ዐፄ ቴዎድሮስ የመቅደላን ጦርነት እንደተሸነፉ እርግጥ በሆነበት በዛች ቅፅበት መኳንንቱ " ጦርነቱን ማሸነፍ ባንችል ቢያንስ ለዚህ ጦርነት ምክንያት የሆኑትን ነጮቹን እንግደላቸው"ሲሉ ዐፄውን መከሩት። ዐፄውም " አንድ ላርግህ ብዬ ያንገላታውት ሳያንስ ለውጪ ጥቃት አሳልፌ አልሰጠውም" ነበር ያሉት። ኋላም ሀገሬው እንዲህ ሲል ለዐፄው ገጠመለት...
"ከመቅደላ አፋፍ ጩኸት በረከተ፣
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሞተ።"...

እስቲ ሁላችንም "ሴት" ከተባሉት " አድር ባዮች፣ በትንሽ ነገር ተስፋ ቆራጮች፣ ምን አገባኝ ባዮች፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዮች" ከመሆን ወጥተን "ከራሳችን ጥቅም የሰው ጥቅም የምናሰቀድም፣ ትንሽ ተነካሁ ብሎ የሀገር ሰውን ሁሉ ምን አገባኝ ብሎ ከመተው የምንቆጠብ፣ በእኛ የደረሰው በሌላ እንዳይደርስ የምንከላከል የሀገር መከታ ሆነን" በታሪክ ባይሆን በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ኩሩ፣ ዠግና "ወንድ" ለመባል እንጣር።

ደግሞ በሀገራቹ ተስፋ ከመቁረጣችሁ በፊት አንድ ነገር አስታውሱ፤ ሀገሪቷ እንዲህ ውጥንቅጧ የወጣው በየቀኑ እንደናንተ ተስፋ በሚቆርጡ ሰዎች ምክንያት ነው።

"ስለዚህ እንዲለወጥ የምትፈልጉት ነገር ካለ ለውጡን ከራሳችሁ ዠምሩ"።።።።

ፀሐፊ : የሱስራ

""""""NO ROOM FOR RACISM"""""
ሀሳብ ካላቹ leave comment 👇👇

@poemers
@poemers
@poemers
@poemers
@poemers
ግጥም-በእኛ 💌 pinned «"BE THE CHANGE YOU WANT TO SEE IN THE WORLD".... " ብርቅዬ አባባል አይደል? ብዙ ማውራት እንችላለን። ከነዚህ ብዙ ነጥቦች እስቲ ስለአንድ ነገር እናውራ። " " በዚህች ታላቅ በነበረች፤ አሁን ላይ ከውስጥም ከውጭም በደረሰባት ቡጥበጣ፣ ግፍገፊ ምክንያት፤ ከ5ሺህ አመት በላይ…»
The Tragedy of Julius Caesar


`` በታሪክ ውስጥ እጅግ አስቀያሚው የስለት ውግያ እና አስከፊ ግድያ ተብሎ የተፈረጀው..የዛር ጁሊየስ የተገደለበት ወቅት ነበር። ``

በእንግሊዛዊው ጸሃፊ ዊሊያም ሼክስፒር “ጁሊየስ ቄሳር” ከተሰኘው ተውኔት የተወሰደ ንግግር። ጁሊየስ ቄሳር ሲወጋ የተወጋው ቁስሉ በታሪክ ውስጥ ካሉ እጅግ አስቀያሚዎቹ የስለት ቁስሎች አንዱ ተብሎ ይመደባል።

የሮማው ንጉሠ ነገሥት ጁሊየስ ቄሳር የተገደለበት ወቅት ነው። በተመሳሳይ ሰዓት ከልብ ከሚያምነው ሰው ክህደትን የተቀበለበት ጊዜ። በዘመኑም ሁሉም ሰዎች አመጹበት ብቻውን እንደቆመ በኀብረት በመሆን በሳለ ጩቤ አጠቁት። ምንም እንኳን ደጋግመው ቢወጉት ወደ መሬት አልወደቀም፤ የድሮ ወዳጁን ‘ብሩተስን’ እስከሚያይ ድረስ።

ጁሊየስ በገዛ ደሙ እየሰጠመ ጓደኛውን ተመለከተና የተስፋና የእፎይታ እይታ በዓይኑ ውስጥ በራ። የህይወት ዘመን ጓደኛው ሊያድነው እንደመጣ በማመን  ለእርዳታ እጁን ዘረጋ ብሩተስ ግን እጁን በመያዝ አንድ ጊዜ ወጋው።

እዚህ ጋር ጁሊየስ ቄሳር እንዲህ ብሎ ነበር “አንተ እንኳን ብሩተስ አንተን የማውቅህ እንግዲያው ቄሳር ይሙት” ቄሳርም ለሞት ወደቀ። የብሩተስ ውግያ ከሌሎቹ ስለት በተለየ መልኩ ለሞት የዳረገው ጩቤ ነበር.. በገላው ሳይሆን በሰውነቱ የገባው እምነት እስኪፈርስ ድረስ ጽናቱ አቆመው። እነሆ ቄሳርም ወደቀ በውድቀቱም ክህደትን ተግቶ ሽንፈቱን አወጀ።

አምላካዊነት በሰጠው ነፃ ፍቃድ እንዲያነጻ የአብ ቀኝ የሰው ልጅ ተነሳ፤ ለትንሽ ዲናርም ሲባል ከአስራ ሁለቱ አልማዝ አንዷ ተበጥሳ ወደቀች!።እኛስ ስንት ብሩተስን እናስተናግድ¿ አንድ በአንድ እስክንረግፍ..



Kahlil Gibran says፡

“ጥይቱ ልቤ ላይ ሲያርፍ አልሞትኩም ነበር፤ ማን እንደተኮሰው እስከማይ ድረስ.. ”
ይህ ሁሉ ከስር 👇🏽 የምትመለከቱት በአለም ደረጃ ያሉ #እምነቶች ስለመልካምነት የተናገሩት ቃሎች ስብስብ ናቸው

ነገር ግን በምድር ያለ አህዛብ የጥቂት ዘረቢስ ቃል በልጦበት ይታያል የእኔ ሃይማኖት ከነዚህ ውጭ ነው ኤቲስት ይባላል 😂



#ክርስትና
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም ደግሞ እንዲሁ
አድርጉላቸው ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና:: (ማቴ 7÷12)

#እስልምና
ለራሳችሁ የምትመኙትን ለሌሎችም እንዲሆን እስካልተመኛችሁ ድረስ በትክክል
አላመናችሁም:: (የነብዩ
መሐመድ ተግባራትና ንግግሮች)

#የአይሁዶች_እምነት
አንተ የምትጠላውን ነገር በባልጀራህ ላይ አታድርግ ይህ ነው እግዚአብሔር
ለሙሴ የሰጠው ሕግ ሲጠቃለል:: (ሒላል ታልሙድ ሻባት 31)

#የባሃኢ_እምነት
በአንተ ላይ ሊጫንብህ የማትፈልገውን በሌላ ላይ አታድርግ በራስህም ላይ
እንዲደርስብህ የማትሻውን ለማንም አትመኝ:: (ባሀኡላህ)

#ቡዲሂዝም
ራስህን የሚጎዳ የሚመስልህን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ::
(ቡድሀ)

#ሒንዱዝም
አንተ ላይ ቢደረግ የሚያስከፋህ ከሆነ አንተም በሌሎች አታድርግ የተግባር ሁሉ
ማጠቃለያ ይህ ነውና:: (ማኅበራት 51517)

#ጃኒዝም
ማንም ሰው ለራሱ እንዲደረግለት የሚሻውን እርሱም እንዲሁም በዓለም ዙሪያ
ላሉ ፍጡራን ሁሉ ያድርግ:: (ማሃቪራ ሱትራክሪታንጋ)

#ሲኪሂዝም
ለማንም ባይተዋር አይደለሁም ማንም ለእኔ ባይተዋር አይደለም የሁሉም ወዳጅ
ነኝ:: (ጉሩ ግራንትዝ ሳሂብ ፒጂ.1299)

#ዩኒታሪያኒዝም
ሁላችንም አካል የሆነበትን የፍጥረታት አንድነትና ትስስር በጽኑ እንደግፋለን
እንዲሁም ልዩ አክብሮት እንዲሰጠው እንተጋለን:: (የዩኒታሪያን መርሆ)

#ታኦዝም
ጎረቤትህ ሲያተርፍ አንተ እንዳገኘህ ቁጠር ጎረቤትህ ሲከስር አንተ እንዳጣህ
አድርገህ ውሰድ:: (ቲአይ ሻንካ ካንዩንግ ፒዮን 213-218)

#ኮንፉሺያኒዝም
የመልካም ሥነ ምግባር መሠረት ማጠቃለያ የሆነ አንድ ቃል ነው እሱም
ሩህሩህ መሆን በአንተ ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን በለሎች ላይ አታድርግ::
(ኮንፍሺየስ አናሌክትስ 15.23)

#ዞሮአስትሬይኒዝም
አንተን የሚጎዳ ነገር ሁሉ በሌሎች ላይ አታድርግ:: (ሻያስት-ና-ሻያስት 13.29)


#ኔቲቭ_ስፒሪቹአሊቲ
የኛ ሕልውና የሚረጋገጠው የምድራችን ተፈጥሮ ይዞታ ሲጠበቅ ነው:: (ቺፍ ዳን ጆርጅ)
ካህሊል ጅብራን
============

ብቸኝነትን የፈለኩት:- ለማምለክ ፣ ለመፀለይ እና የአንድ ፃድቅ ህይወት ለመምራት ብዬ አይደለም ማምለክ ለብቻ ተነጥሎ መኖርን አይጠይቅምና

ብቻኝነትን የፈለግሁት:- ራሳቸውን ሽጠው ፣ በተመሳሳይ ዋጋ በመንፈሳዊም ሆነ በቁስ አካላዊ መስፈርት ከእነሱ ያነሰች ነገርን የሚገዙ ሰዎችን ፊት ላለማየት ስል ነው...

ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በመንገድ ላይ ከናፍሮቻቸው ላይ አንድ ሺህ አይነት ፈገግታዎችን ቢያሳዩም በሺዎቹ ልቦቻቸው ውስጥ በጥልቀት አንድ ብቻ አላማ ያላቸውን በኩራት የሚራመዱ ሴቶች ላለማግኘት ነው...

ብቸኝነትን የፈለግሁት:- የእውቀት መንፈሰ በህልሞቻቸው ውስጥ አይተው ግባቸውን እንደመቱ ከሚያምኑት ከእነዚያ በራሳቸው ከሚረኩት ሰዎች እራሴን ለመሸሸግ ስል ነው...

ከማህበረሰቡ የሸሸሁት:- እውነትን ባያዩም መንፈስ ከማይገነዘቡት እና ለአላማቸው መሳካት ሲሉ ብቻ የእውነትን ፍሬ ነገር ሙሉ በሙሉ እንዳገኙት አድርገው ከሚለፍፉት ለመራቅ ነው።

ከአለም ተነጥዬ ብቸኝነትን የፈለግሁበት ምክንያት:- ትህትናን ደካማነት ፣ ምህረትን ፍርሀት ፣ ትምክህትን ደግሞ የጥንካሬ መግለጫ እንደሆነ አድርገው የሚያምኑትን ህዝቦች በይሉኝታ መቅረቡ አሰልችቶኝ ነው።

ብቸኝነት የመረጥኩት:- ነፍሴ ከነዚህ ፀሀይ ፣ ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት በገንዘብ ካዝናዎቻቸው ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ እንደማይወጡና በእነሱ የአትክልት ስፍራዎች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንደማይጠልቁ ፅኑ እምነት ካላቸው ጋር አብሮ መኖሩ ስላንገፈገፈኝ ነው...

እናም በአይኖቻቸው ላይ ወርቃማ አቧራ እየጨመሩና ጆሮቻቸውን ትርጉም አልባ በሆኑ ወሬዎች እየሞሉ የህዝቦችንን ምድራዊ ዕጣ ፈንታ ከሚበጠብጡት ባለስልጣናት ሸሸሁ...

እንደስብከታቸው የማይኖሩትንና ህዝቦችን እነሱ የማይፈፅሙትን ነገር እንዲያደርጉ የሚመክሩትን (የሚያስገድዱትን) ቀሳውስት ለመሸሽ ስል ትቻቸው ሄድኩ...

ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በልቤ ሙሉ ዋጋ ካልከፈልኩ በስተቀር ከሰው ልጅ ዘንድ ርህራሄን በጭራሽ ባለማግኘቴ ነው...

ብቸኝነትን የፈለግሁት:- ሰዎች ስልጣኔ ብለው የሚጠሩትን ያ ታላቅና አስቀያሚ ህገመንግስት ፣ ያ በሰዎች ልጆች ላይ ዘላቂ ሙከራ ያመጣ ተመሳሳይ ጎኖች ያሉት ጭራቅ አንገፍግፎኝ ነው...

ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በውስጡ ለመንፈስ ፣ ለልብና ለአካል የሚሆን ሙሉ ህይወት ስሌለ ነው።

እናም የፀሀይ ብርሀን የሚያርፋባቸውና መጨረሻ የሌላቸው አበቦች መአዛቸውን ወደ ህዋ የሚተነፍሱበት እንዲሁም ጅረቶች እያዜሙ ወደ ባህር የሚያቀኑበትን የሳር መስክ አግኝቻለሁ።

የፀደይ ወራትን ትኩስ ግንዛቤ፣ የክረምትን ቀለመደማቅ ናፍቆት ፣ የመኸርን ጣፋጭ መዝሙሮች እና የበጋ ወራትን ውብ እንቆቅልሽ ያገኘሁባቸውን ተራራዎች ደረስኩባቸው...


ምንጭ •••የጠቢባን መንገድ ገፅ (115-117)
ደራሲ •••| ኻሊል ጂብራን

@gbw_dan |
Forwarded from 11:34 (Kalehiwot)
ክበር ለዐድዋ ሰማዕታት ዛሬ አፌን ሞልቼ ኢትዮጵያ እንድል ላረጉኝ ጀግኖች

ክብር ለነሱ! በመልክ ቀለሜ የበታችነት እንዳይሰማኝ ላረጉ አባቶቼ::

2024/05/01 01:25:19
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243