Telegram Web
🕊

[ ✞ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

🕊  †  ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ  †   🕊

ከ ፲፪ [12] ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም [አልቦ ትንሳኤ ሙታን] የሚሉ ናቸው::

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::

ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: [ዮሐ.፲፩፥፲፮] (11:16)

ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም :-

፩. ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
፪. አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ [ጌታየና አምላኬ]" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን [መለኮትን] ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ [ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት]" ሲሉ ያከብሩታል::

ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::

በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት :-

"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::

በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ፴፰ [38] ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

በመጨረሻም በ፸፪ [72] ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ [ቶማስስ] ማለት ጸሐይ [ኦርያሬስ] እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ †  ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ [ከ ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት]
፪. ቅድስት አርሶንያ [የቅዱስ ቶማስ ተከታይ]
፫. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፪. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፫. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: " [ዮሐ.፳፥፳፮-፳፱]  (20:26-29)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ 

https://www.tgoop.com/menefesawinet
        
🕊

† በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::  †

🕊  † አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ †   🕊

እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ [የራውዕይ] ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::

ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::

ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::

የ ፭ [5] ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::

ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::

- ባሕር ውስጥ ሰጥመው ፭፻ [500] ጊዜ ይሰግዳሉ::

- በየቀኑ ፬ [4] ቱን ወንጌልና ፻፶ [150] መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (µ[መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው]

- በ ፵ [40] ቀናት : ቀጥሎም በ ፹ [80] ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::

- ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::

- በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: [ካህን ናቸውና]

- ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::

- በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም::

በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::

፩. " ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ:
፪. ስለ ምናኔሕ:
፫. ስለ ተባረከ ምንኩስናህ:
፬. ስለ ንጹሕ ድንግልናህ:
፭. ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ:
፮. ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ:
፯. ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ ፯ [7] አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : ፭፻ [500] የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::

ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን [ግንቦት ፳፮ [26] ] ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}

አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

🕊

"እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .  ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፮-፴፩]   (36:28-31)

†  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  †


ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ
https://www.tgoop.com/menefesawinet
🕊

† በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::  †

[ ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ]

🕊  † አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ †   🕊


እግዚአብሔር በ፲፫ [13ኛው] መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::

አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ [ዳኅና] አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::

ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን [ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው] ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::

አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::

አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::

በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::

በአንዴም ከዳሞ [ትግራይ] ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ [ወሎ] አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::

ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ [ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው] ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::

በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::

ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::

ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::

እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::

ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው [በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ] በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}

" ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! "

" ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: " [፩ዼጥ. ፭፥፫ ]

†  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  †

[ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ
https://www.tgoop.com/menefesawinet
#ወዴት_እንታደስ ?
:
➊.ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና → ወደ የቱ ሐይማኖት?
:
➋.ከቀደመዉ መንገድ ወደ → የትኛዉ ህይወት?
:
➌.ከአባቶቻችን ሐይማኖት ወደ → እነማን እምነት?
:
➍.በክርስቶስ ደም ከተዋጀች ቤተ ክርስቲያን → ወዴት?
:
✞︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵✞
:
#ነዉ_ወይስ ....
:
➊.ከጾም → ወደ መብል ብቻ?
:
➋.ከጥምቀት → ወደ አለመጠመቅ?
:
➌.ከቁርባን → ወደ አለመቁረብ?
:
➍.ከስርዓት → ወደ ስርዓት የለሽነት?
:
➎.ከቤተ ክርስቲያን → ወደ አዳራሽ?
:
➏.ከቅዳሴ → ወደ ጩኸትና ሁከት?
:
➐.እግዚአብሔርን ከማምለክ ፈላስፎችን → ወደ መከተል?
:
➑.የክርስቶስን ክብር ከፍ ከማድረግ ዝቅ → ወደ ማድረግ?
:
➒.ፈራጁን ጌታ አማላጅ ነዉ → ወደ ማለት?
:
➓.ቅዱሳኑን ከመቀበል → ወደ አለመቀበል?
:
➊➊.ቅዱሳኑን ከማክበር → ወደ መቃወም?
:
➊➋.ቅዱሳኑን አማላጅ ከማለት → ምንም ቦታ የላቸዉም ወደማለት?
:
➊➌.ጸበልን እንደ ተራ ዉኃ → ወደ ማየት?
:
➊➍.ከበሮን በጊታር → ወደ መቀየር?
:
➊➎.ጸናጽልን በኦርጋን → ወደ መለወጥ?
:
➊➏.ዕጣኑን በዓለማዊ ሽታ → ወደ መተካት?
:
➊➐.እምነት ብቻ ብሎ ሥራን → ወደ መርሳት?
:
✞︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵✞
:
#እሽ_ወዴት_እንታደስ ? …....
:
➊.ራስን ለካህን ወደ → አለማሳየት?

➋.መጽሐፍትን እንደ ራስ ፈቃድ ወደ→ መተርጎም?
:
➌.መዝሙርን ዘፈን መሰል ወደ → ማድረግ?
:
➍.365 ቀን ራስን ለሆድ ወደ→ ማስገዛት?
:
➎.የሉተርን ፍልስፍና ወደ→ መከተል?
:
➏.የእግዚአብሔርን ታቦት ጣዖት ነዉ ወደ → ማለት?
:
➐.በቅዱሳን ስም ምጽዋትና ዝክርት ማድረግን ወደ→ መርሳት?
:
✞︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵✞
:
#ነዉ_ወይስ……..
:
➊.ሴቶች ራሳቸዉን ሳይሸፍኑ → ወደ ሚጸልዩበት?
:
➋.ሐሰተኛ ነቢያት→ ወዳሉበት?
:
➌.ነገረ ሥራቸዉ ሁሉ ተቃዉሞ ብቻ → ወደ ሆነበት?

➍.ስግደትን በዝላይ→ ወደ መቀየር?

➎.ጸሎትን →ወደ መተዉ?

➏.ገዳምን ንቀዉ የስጋን ዓለም →ወደ መረጡት?

➐.ብሉይ ኪዳን ተሽሯል→ ወደ ሚል ክህደት?

➑.ንዋየ ቅድሳትን እንደ ተራ ዕቃ →ወደ ማሰብ?

➒.ማዕተብን →ወደ መበጠስ?

➓.መንፈሳዊ በረከት ከሚገኝበት ብርና ዶላር → ወደ ሚቸረቸርበት?

➊➊.የጌታ እናት ወላዲተ አምላክን እንደ ማንም ፍጡር→ ወደ መመልከት?

➊➋.የቅዱሳን ተጋድሎ እንደ ተራ የሕይወት ጉዞ →ወደ መቁጠር?

➊➌.መስቀሉን ተራ እንጨት ነዉ→ ወደ ሚል ንቀት?

➊➍.በትዕቢት ተነፍቶ እኔ ቅዱስ ነኝ →ወደ ማለት?

➊➎.ከካህን →ወደ ፓስተር?

➊➏.የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸዉን መጻሕፍት→ ወደ አለመቀበል?

➊➐.የቅዱሳንን መታሰቢያ ዘላለማዊነት ጊዜያዊ→ ወደ ማድረግ?

➊➑.ከህይወት → ወደ ሞት?
:
✞︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵✞
:
#ተሃድሶ_ስትሉ_ወዴት ? ……..////
:
➊.በዓላትን → ወደ አለማክበር?
:
➋.ከምንኩስና → ወደ ዓለም ናፋቂነት?

➌.ወንጌልን → ወደ ማጣመም?

➍.ሴት ልጅ በድፍረት የወንድ ልብስ ለብሳ አስተማሪ ነኝ → ወደ ምትልበት?

➎.ከእዉቀት → ወደ ምንምነት?

➏.ከእዉነተኞቹ ነቢያትና ሐዋርያት →ወደ ሐሰተኞቹ?

➐.ከምሉዕነት →ወደ ባዶነት?

➑.ከቅድስና→ ወደ ርኩሰት?

➒.ከነጻነት→ ወደ ባርነት?

➓.ከንግስተ ሳባ እምነት →ወደ ዘመኑ ፈላስፎች?

➊➊.ከኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ ክርስትና→ ወደ ምንፍቅና?

➊➋.ከመንፈሳዊነት →ወደ ዓለማዊነት?

➊➌.ከክርስትና →ወደ ፍልስፍና?
:
#እሽ_ተሃድሶ_ስትሉ_ወዴት እንታደስ? ……..//

#እንንቃ_ጓደኞቼ !!!

#እኛ_ኦርቶዶክሶች_የሚያረጅ_እምነት_ስለሌለን_የሚ
ታደስ_ሀይማኖት_የለንም !!
:
[☞ምንጭ ፦ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጽሑፎች☜]
:
✞︵♡┈┈┈••✦✞✦••┈┈┈✞︵❀
:
#እኛ ኦርቶዶክሶች፦

➊.ተ = ተግባር የሌለበት እምነት፣

➋.ሃ = ሃሰት የነገሰበት ትምህርት፣

➌.ድ = ድብቅ የጥፋት ዘመቻ፣

➍.ሶ = ሶስትነት በአንድነት (ሥላሤ) ያልገባው ድርጅት አንፈልግም።
:
✞︵♡┈┈┈••✦✞✦••┈┈┈✞︵❀
:
#የተወደዳችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ድንግል ማርያም አስራት ልጆች ሆይ፥

በያለንበት → ደስ የሚል የተባረከ መልካም ቀንና ወር ያደርግልን ዘን የጌታ ፍቃድ ይሁን አሜን!
:
የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም → አማላጅነቷ፣ ጠብቆቷና በረከቷ በምልጃዋ ለምናምን ለእኛ በእውነት ዘወትር አይለየን! (አሜን)
:
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም→ በቃል ኪዳኗ በምልጃዋ ለምናምን ለእኛ በእውነት አትለየን!(አሜን)
:
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም → ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በምልጃዋ ለምናምን ለእኛ በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን!(አሜን)
:
የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም → ፍቅሯ በልባችን፣ ጣእሟ በአንደበታችን፣ ምልጃዋ ለህይወታችን በምልጃዋ ለምናምን ለእኛ በእውነት ይብዛልን!"(አሜን)

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም→ ጸሎቷም በምልጃዋ ለምናምን ለእኛ በእውነት ከክፉ ነገር ይጠብቀን አሜን!
:
የሕይወት የድህነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለልኡል እግዚአብሔር ምስጋና ስለ ስም አጠራሩ ይሁን አሜን!

ገናናው አምላካችን ልኡል እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላም ለምድራችንም በረከትን ያድልልን አሜን!
:
✞♡┈┈┈••✦✞✦••┈┈┈♡✞

➊.የልኡል እግዚአብሔር ቸርነት፣
:
➋.የድንግል ማርያም አማላጅነት፣
:
➌.የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣
:
➌.የጻድቃን፣ የሰማዕታት ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
:
➍.የቅዱሳን ሐዋርያት ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
:
➎.የቅዱሳን አበው መነኮሳት ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
:
➏.የቅዱሳት አንስት ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
:
➐.የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!! አሜን
:
➑.ለአባ ሕርያቆስ፣ ለቅዱስ ኤፍሬም፣ ለቅዱስ ያሬድ፣ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም፦

በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን፣

ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!

➒.ከዋክብት የሚያመሰግኑት፣ በስማቸውም የሚጠራቸው፣ የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፦

ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን።
:
#ለዘለዓለሙ_አሜን

#በእምነታችን_ጸንተን_በመኖር_የመንግስቱ_ወራሾች_ያድርገን
-አሜን!
:
#የልኡል_እግዚአብሔር_ጸጋና_በረከት_ከሁላችንም_ጋ
ር_ይሁን_አሜን ።
:
#አነሣሥቶ_ላስጀመረን_አስጀምሮ_ላስፈጸመን_ለልኡል
_እግዚአብሔር_ክብር_ምስጋና_ይግባው_አሜን ።
:
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመ
ስቀሉ_ክቡር !

[☞ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን ለዘላለም ትኑር!☜]
:
"በቤቱ ያጽናን"
@menefesawinet
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡   †

†    እንኳን አደረሳችሁ   †
ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

[  † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  †  ]

🕊   †  አርዋ ቅድስት  †   🕊

እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ::

ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት [ቁንጅና] በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ::

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" [የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች] አስብሏታል::

የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ::

አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል:: ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች::

አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት::

እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች :- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች::

እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል::

🕊  †  ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ  †   🕊

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል::

ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ [ ፸፪ቱ ] አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል::

ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር::

† ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን::   †

🕊

[  † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት አርዋ እናታችን
፪. ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
፬. አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኃዊ በዓላት    ]

፩፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫፡ አባ ሣሉሲ ክቡር
፬፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት
፭፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ

" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: " [ምሳሌ.፴፩፥፳፱] (31:29)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


       @menefesawinet
+ ለመላእክት ስግደት አይገባም የሚሉን +

ይህችን ይዘው በተረዱበት መንገድ ስላልሆነ መረዳታችን እንዲህ ትብራራለች ።


"ነገር ግን እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባርያ ነኝ ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ" (ራእይ19፥10፣ 22፥9)  በማለት መልአኩ የመለሰለትን መልስ በአግባቡ ሳይረዱ ለመላእክት መስግድ አይገባም ለሚለው የተጣመመ ትምህርታቸው ድጋፍ አድርገው የሚያነሡ ወገኖች አልታጡም። ቅዱስ ዮሐንስንም ሁለቴ ለመልአኩ መስገዱ "ካለማወቅ" ብለው በድፍረት ሲናገሩ ይደመጣሉ ። ግን ይህን ተቃውሞ ከመሠረቱ ለማፍረስ እስኪ ጥቂት ለመልአኩ ስለ ሰገደው ዮሐንስ ወንጌላዊ ማንነት ለመረዳት እንሞክር ፦

ቅዱስ ዮሐንስ በብዙ አስደናቂ ጸጋዎች የማናውቀው ታላቅ አባት ነው ። ምንም ከትሕትና የተነሣ በወንጌል የገዛ ስሙን ጠቅሶ ስለ ራሱ በዙ ነገር ባይጽፍልንም እንኳን ጌታ አብልጦ ይወደው የነበረ ሐዋርያ ፤ ከደረቱ የሚጠጋ ባለሟል እንደነበረ ግን ነግሮናል። ይህም ብቻ አይደለም ። ቅዱስ ዮሐንስ ነገረ ሃይማኖትን የመረዳት አቅሙ ጥልቅ እንደነበረ ሦስቱ ወንጌላውያን ባልተነሡበት መንገድ ወንጌሉን በረቀቀ ስብከት በመጀመሩ አውቀናል ። ቅዱስ ዮሐንስ የጻፈውን ወንጌሉን የተረጎመ ስመ ሞክሼው #ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ያገኘውን ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ክብር ሲናገር መላእክት የተፈጥሯቸውን ነገር ከእርሱ ሊማሩ ይፈልጉ እንደነበረ ከዚህ ቀደም ባጣቀስነው "በእንተ ኅቡዓት" በተሰኘ ድርሰቱ ላይ አስፍሮታል። ታድያ በመለኮታዊው ምሥጢር ባሕር ሲዋኝ የሚኖር ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፣ በመላእክት የሚጠየቅ ታላቅ ጻድቅ "ለመላእክት ስግደት ይገባል ወይስ አይገባም?" የሚለውን ጉዳይ በእርሱ ዘንድ እንዴት አወዛጋቢ ሊሆን ይችላል ? እንኳን መላእክት ለማየት የበቃ ቅዱስ ዮሐንስ አይደለም እኛም ይህን ሳንረዳው ብንቀር ከታላቅ ትዝብት ላይ ይጥለናል!። 

ቅድም በያዝናት ርዕስ ዙርያ (ራእይ19፥10፣ 22፥9) 

ደግሞሰ ያለ እውቀት የፈጸመውና የማይገባ ከሆነ መልአኩ አንድ ጊዜ "አትስገድልኝ" ካለው በኋላ ደግሞ ሊሰግድለት ስለምን አልተቆጣውም ወይም በተግሳጽ ቃል አልተናገረውም ? ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ መበደል የሚብስ ቅጣት ያመጣልና (ዮሐ5፥14) ። ቅዱስ ዮሐንስ ግን የመላእክትን ክብር ስለተረዳ አትስገድልኝ እንኳን እያለው በግንባሩ መሬት ነክቶ ሰግዶለታል ። መልአኩም "አትስግድልኝ"  አለው እንጂ "ስግደት ለመላእክት አይገባም " አላለውም ። መልአኩም ለምን አትስገድልኝ አለው ?

ከቅድስና ልዩ ልዩ መገለጫዎች መካከል አንደኛው "አይገባይኝም" የሚል ልባዊ ትሐትና ነው ። ለዮሐንስ የተገለጠው መልአክ ትሑታን ከሆኑት የቅዱሳን መላእክት ማኅበር የመጣ እንደሆነ ካመንን በዚህ የከበረ የእግዚአብሔር ሰው ስለ ቀረበው ስግደት "አይገባኝም" ብሎ ትሕትና ከመናገር ውጪ ምን እንዲል ይጠበቅበት ይሆን ?


በስተመጨረሻም መልአኩ ቅዱስ ዮሐንስን በንጽሕና ከመዓረገ መላእክት ላይ በመድረሱ እኩያው መሆኑን ስላወቀ ከአንተ ጋር....አብሬ ባሪያ ነኝ" ሲለው ፤ "ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት"/"ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ" እንዲል መላእክት ሊነኩ የማይቻላቸውን የአምላክ ሥጋ እና ደም የሚፈትት የሐዲስ ኪዳን ካህን ነውና በዚህስ ደገኛ ሹመት ስለበለጠው ደግሞ "አትስገድልኝ" በማለት አስጠንቅቆታል ። ( "መላእክት" ዲያቆን አቤል ካሳሁን ገጽ 91፥92-93)
@menefesawinet
                         †                      

" እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ ! "

---------------------------------------------

💖 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን ! 💖


" አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ ፥ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።

እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል። [መዝ.፵፯፥፭፥፰]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

† [  ዕርገት  ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል።

† [  ጰራቅሊጦስ  ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ።

† [  ፆመ ሐዋርያት  ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ።

† [  የጾመ ድህነት  ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
@menefesawinet
† እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ዕርገት እና ለጻድቁ አባ ዳንኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †


🕊      †    ዕርገተ እግዚእ     †       🕊

† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን ፪ [2] ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል" : ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ [በሕማሙ : በሞቱ] ዓለምን አድኖ: ፵ [40] ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

በ፵ [40] ኛው ቀን ፻፳ [120] ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው : ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጓል::

ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ፵ [40] ኛው ቀን ዐረገ::

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

† ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: † [መዝ.፵፮፥፮] (46:6)


🕊  †    ታላቁ አባ ዳንኤል  †     🕊

† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው:: በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው:: ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን አይቷልና:: አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ [መንኖ] ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው::

ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን [በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን] ነበር:: በገዳመ አስቄጥስ እና በደብረ ሲሐት ይታወቃል:: ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት : ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው::

ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል:: ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል:: ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም : ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው::

በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው:: አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል::

ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም:: ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ : ድውያንን ሲፈውስ : ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል:: ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል::

በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር:: በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል:: ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል::

እርሱ ገንዞ ቀብሮ : ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን [ለ፴፰ [38] ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች] እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን [መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት] መጥቀስ እንችላለን::

ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን : በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ ነው" ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል::

አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል::

ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባልድሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ድሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ::

ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ::

ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች::

"ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው::

ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ : በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

† በተረፈው ግን ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር :-

፩. በገዳመ አስቄጥስ [ግብጽ] አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ ባሳየው ትጋት::
፪. በሃይማኖት ጠበቃነቱ በደረሰበት ድብደባና ስደት::
፫. ብዙ የበርሃ ቅዱሳንን በየበአታቸው እየዞረ በመቅበሩ::
፬. የብዙ ስውራን ቅዱሳንን ዜና ሕይወት በመሰብሰቡ::
፭. በየጊዜው በእግዚአብሔር ኃይል ይፈጽማቸው በነበሩ ተአምራት:: እና
፮. ለድንግል እመቤታችን ማርያም በነበረው ልዩ ፍቅር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች::

† ቸር አምላክ ክርስቶስ ከዕርገቱና ከጻድቁ በረከት አይለየን::

🕊

† ግንቦት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱሳን የጌታ ቤተሰብ [፻፳ (120) ው]
፪. ቅዱስ አባ ዳንኤል ጻድቅ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ መክሲሞስ መስተጋድል
፭. አቡነ ዮሐኒ ዘደብረ ዳሞ [አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ለምንኩስና ያበቁ]

† ወርሐዊ በዓላት

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [አርባዕቱ እንስሳ]
፫. አባ ብሶይ [ቢሾይ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት]

† "እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" † [ሉቃ.፳፬፥፶-፶፫] [24:50-53]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
@menefesawinet
❗️❗️❗️አስደሳች ዜና


የክረምት ልዩ የቤት ለቤት ስልጠና
።።።።።። ክራር
።።።።።።። በገና
።።።።።።። መሰንቆ
።።።።።።። ከበሮ
በሚፈልጉት ቀን እና ሰአት ከሰኞ እስከ እሁድ

❗️❗️እንዲሁም ለአንድ ወር የሚቆይ ዩቲዩብ ለመስራት ያሰባችሁ❗️❗️❗️❗️ ከመጀመርያ እስከ ገንዘብ ክፍያ ያለውን ሂደት አሰራር  በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ እናሳያለን
☎️ +251900819497 ይደውሉ
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ?✟

          👇👇👇
https://www.tgoop.com/addlist/2TkBck2rFoxMjNk
https://www.tgoop.com/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk
2024/06/16 04:36:24
Back to Top
HTML Embed Code: