Telegram Web
Forwarded from ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት (ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት)
🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱

🌿🌿🌿

☀️ግንቦት ፲፪ በዚህችም ዕለት የመነኰሳት ሁሉ አለቃ ሐዋርያና ሰማዕት የታላቁ መምህር አባታችን ተክለሃይማኖት የስጋው ፍልሰት ኾነ !

🌿🌿🌿🌿

☀️በዚህችም ዕለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ዕለት ነው!

🌿🌿🌿

☀️ዳግመኛም በዚህች ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የከበረ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዐረፈ::

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

የቅዱሳኑ ረድኤት በረከት በኹላችን ላይ ይኹን አሜን! 🙏🙏

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ለጻዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ወምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል
" ኪዳነ ምህረት ማርያም" አተበቁዓኪ አነስ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍስ "እስመ በሥራይኪ ለቁስልየ ቅብዕኒ ፈውስ"
ኪዳነምህረት" ማርያም ሆይ! በመድኃኒትሽ ቁስሌን እንድትፈውሽ በኪዳንሽ ቤዛነት ነፍሴን እንድታዳኚ እማለድሻለሁ። አሜን። <
               +"+ <መልክአ ኪዳነምህረት"+"+
https://vm.tiktok.com/ZMMoeNFNg/

ንጽሕት በሆነችው ሃይማኖታቸው ቅድስት በሆነችው ጸሎታቸው ይጠብቀን
እንቆቅልሽ

በ21 ትነግሳለች የደሆች እናት በስሟ ለሚለምኑ በረከት የሆነች
ይህቺ አምላኳን የወለደች ማናት

መልሱን በኮሜንት ይጻፉልን
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
++++
** "የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ" (ቅዱስ ፓትርያርክ)
--------------
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
- ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
- ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን!

‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡

እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው። እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል። በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው። የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ "እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት…" የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል። በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡

ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም። ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም። አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡

እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል። አሁንም አልቆመም። ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ። ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ። ዛሬም አለ። ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡

በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል። በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል። ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ሥራ መሥራት ይኖርበታል፡፡

ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት!
የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም። በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል። የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጪው ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው። በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን፣ ካህናት፣ ምእመናን፣ አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል። ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡

በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው። ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መሥራት ይጠበቅባታል። ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ
እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም ፡-
ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡

መልካም ጉባኤ ያድርግልን!

እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን፡፡
+++
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
https://vm.tiktok.com/ZMr1fkvr5/

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
አላቲኖስ:
የዕለቱ መልእክት

ጠቃሚ የንስሐ ምክር
"ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡

ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡"

      .  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ
.        ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ምክረ አበው ዘቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

የምወዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ስለ አእምሮአችን ሕጸጽ ጸልዩልን፤ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከ መጨረሻ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናን ዘንድ ተስፋችን ይህ ብቻ ነው፤ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል  አሜን
    
መልካም ቀን
2024/06/01 15:04:06
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243