Telegram Web
ልሂድ አደን

ልቤ ተነሳስቶ፣ ጽድቅህን ፍለጋ፣
ከማዳንህ ጋራ ፡ ስምህን ሊጠጋ፣
ልሂድ ወደ ዱሩ፣ ካ'ባቶች ማደሪያ፣
ከለምለሙ መስክህ ከጽድቅ መነኻርያ፣
ዓለምን 'ሚረግጡት፣ ሰማዩን ሚመኙት፣
እሳቸውን ጥለው፣ ...ሰዉን ከሚወዱት፣
ስለስምህ ብለው፡ .........ከዋሻ ከገቡት፣
ቀንና ሌት ተግተው፣ ወንጌሉን ከኖሩት፣
የምድሩን ንቀው ፣ ቃልህ ጣፍጧቸው፣
የማዳንህን ሥራ ማንም ላይቀማቸው፣
እንትፍ ዓለሚቱ፣ ከነማርሽ ጥፊ፣
እየጎመዘዘ ፣ዓለማቸው ሰፊ፣
ኬት ይገኛል ያንተ ፣ልቡን ላልከፈተ፣
በደልን ምኞቱን ፣ ጉድጓድ ካልከተተ፡
በወንጭፍ አይቀልቡት፣ በጦሩ አይወጉት፡
ጅማሬው ይጥላል ፣ ልቡናን ካልረቱት፤
አደን ልሂድ ልውጣ ልጀግን ልጠንክር ፣
እኔም እዛ ልሂድ ፣ ከቅዱሳን አጥር
ልጨክን ላምርረው፣ ጦሬን ልታጠቀው፣
ልቤን አሸንፌ፣ ዓለሙን ልስቀለው፤
@kinexebebe
Forwarded from የያሬድ ውብ ዜማ🕇🕆 (ይለይብኛል12 @webzema)
ሞክሩት መሞከሩ አይከፋም
https://www.tgoop.com/tapswap_mirror_bot?start=r_394755665 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
የተፈተነ ህይወት ድራማ.pdf
86.3 KB
መንፈሳዊ ድራማ

🔴የተፈተነ ህይወት
የራሄል እንባ ያርግልሽ ! ተውኔት.docx
32.7 KB
መንፈሳዊ ተውኔት

🔴የራሄል እንባ ያርግልሽ
አበው ይናገሩ

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

@kinexebebe
ጸሎት ነገሮችን ለመጠየቅ ሳይሆን ስለ ግንኙነቶችን ማድረጊያ ነው።
 
ጸሎት ‘አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም’ ወደምናገኝበት ወደ እግዚአብሔር ልብ የሚያስገባን መኪና ነው [ፊልጵስዩስ 4፡7]። 
 
ጸሎት በአክብሮት እና በትህትና ወደ እግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ፣ የእውነተኛ ርስታችን የሆነውን የልባችንን መለወጥ የምንፈልግበት እድል ነው።  
 
ጸሎት ለእኛ ባለው ታላቅ ፍቅር ምክንያት ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለማሳየት ያ እድል ነው። 
 
ጸሎት ነገሮችን በመጠየቅ ሳይሆን ከእርሱ ጋር እንድንገናኝ ከጋበዘን አምላክ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር መፈለግ ነው።

አፍቃሪ በሆኑ ወላጆች እንክብካቤ ውስጥ ያለ አንድ ሕፃን ስለ ምግብ፣ ልብስ፣ ደህንነት፣ ደህንነት መጨነቅ የለበትም፤ ምክንያቱም ወላጆቹ የሚፈልገውን ስለሚያውቁ በብዛት ይሰጣሉ። 

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደዛ ነው። የሚያስፈልገንን እናውቃለን ብለን እናስብ ይሆናል፣ ነገር ግን እሱ ትምህርት ቤት መሄድ አያስፈልገውም ብሎ እንደሚያስብ፣ እና ወላጆቹ እንደሚያረጋግጡት፣ እግዚአብሔር ለእኛ መዳን የሚያስፈልገውን ነገር ይሰጠናል።

እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ካመንን ምንም ነገር መጠየቅ እንደሌለብን እናምናለን ነገር ግን አምልኮን እና ፍቅርን ብቻ እናቀርባለን እና ራሳችንን ለሰማዩ አባታችን አሳልፈን እንሰጣለን። በወላጆቹ እንደሚወደዱ እንደማንኛውም ልጅ እኛ የአብን ፍቅር እርግጠኞች ነን። 

አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት የሠሩ፣ ነገር ግን ንስሐ ያልገቡ፣ እና ሌሎች ኃጢአት የሠሩ እና ንስሐ የገቡ ሰዎችን እናገኛለን…

ላልሠሩት ኃጢአት ንስሐ የገቡ ሰዎች እና ሌሎች ስህተታቸውን በሌሎች ላይ ያደረጉ...

ምንም ኃጢአትን ላለማድረግ የታገሉ ሰዎች አሉ፤ ሌሎችም ኃጢአትን ለመሥራት የጸኑ አሉ።…

ስለሌሎች ኃጢአት የሚያስብ አለ፥ ስለ ራሱም ኃጢአት የሚጨነቅ...

ለኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ የሚጸልይ ሰው አለ፣ ሌሎችም የሚኮንኑአቸው...

እና “በኹለት ሀሳብ መካከል የሚንኮታኮት ሰው አለ” [1ኛ ነገ 18፡21] በትሩን ከመካከላቸው ሊይዙት ይፈልጋሉ፣ እሱ ንስሃ የገባ ወይም ኃጢአተኛ አይደለም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከዲያብሎስ ጋር…

እናም በንስሃ ህይወት የኖሩ ሰዎች አሉ እናም የመጽናኛ ስርአተ ትምህርት ሆነ በእርሱም የዘላለምን ሕይወት አሸንፈዋል…

ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱ እርስዎን የሚመለከት የግል ልምምድ ያድርጉት…
@kinexebebe
🕊

✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✞


🕊  ዕርገተ እግዚእ   🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን ፪ [2] ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ [በሕማሙ: በሞቱ] ዓለምን አድኖ: ፵ [40] ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

በ፵ [40] ኛው ቀን ፻፳ [120] ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል::

ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ፵ [40] ኛው ቀን ዐረገ::

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

" ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ::" [መዝ.፵፮፥፮] (46:6)

ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን::

"እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" [ሉቃ.፳፬፥፶] (24:50-53)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
@kinexebebe
❗️❗️❗️አስደሳች ዜና


የክረምት ልዩ የቤት ለቤት ስልጠና
።።።።።። ክራር
።።።።።።። በገና
።።።።።።። መሰንቆ
።።።።።።። ከበሮ
በሚፈልጉት ቀን እና ሰአት ከሰኞ እስከ እሁድ

❗️❗️እንዲሁም ለአንድ ወር የሚቆይ ዩቲዩብ ለመስራት ያሰባችሁ❗️❗️❗️❗️ ከመጀመርያ እስከ ገንዘብ ክፍያ ያለውን ሂደት አሰራር  በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ እናሳያለን
☎️ +251900819497 ይደውሉ
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ?✟

          👇👇👇
https://www.tgoop.com/addlist/2TkBck2rFoxMjNk
https://www.tgoop.com/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk
2024/06/15 20:13:02
Back to Top
HTML Embed Code: