Telegram Web
በዚኽች ዕለት ጥቅምት 20 ቀን በዓመታዊ በዓሉ ታስቦ የሚውለው የታላቁ ነቢይ የቅዱስ ኤልሳዕ ታቦት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ገብቷል። እናም በዛሬው ዕለት ጥቅምት20 ቀን 2013 ዓ.ም በርእሰ አድባራት ወገዳማት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

ኤልሳዕ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጠባቂ ነው›› ማለት ነው፡፡ ዐፅሙ የሞውተን ሰው ያስነሣ ታላቅ ነቢይ ሲሆን ኢዮራም፣ አካዝያስ፣ ኢዩና እንዲሁም ዮአስ በተባሉ በአራት ነገሥታት ዘመን ትንቢት የተናገረ ሲሆን የትንቢቱም ዘመን ከ50 ዓመት በላይ ነው፡፡ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በመንገድ ሲሄድ የሳፋጥ ልጅ አልሳዕን በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው፡፡ ኤልያስም ሄዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት፡፡ ኤልሳዕም እርሻውን ትቶ ተከተለው፡፡ ተመልሶም በመምጣት በሬዎቹን አርዶ ሕዝቡን መግቦ በፍጹም ልቡ ኤልያስን ተከትሎ ብዙ ዓመት ሲያገለግለው ኖረ፡፡

ኤልያስ በሚያርግበት ጊዜ ኤልሳዕን ‹‹ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ›› አለው፡፡ ኤልሳዕም ‹‹በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ሆኖ ይድርብኝ›› አለው፡፡ መምህሩም ‹‹…ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ብታየኝ ይደርብህ›› አለው፡፡ ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ በመሀል የእሳት ፈረስና የእሳት ሠረገላ መጥቶ ኤልያስን ነጥቆ ወሰደው፡፡ ኤልሳዕም ይህን በተመለከተ ጊዜ ‹‹የእስራኤል ኃይላቸውና ጽናታቸው አባ አባ…›› ብሎ ጮኸ፡፡ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ አላየውም፡፡ መጠምጠሚያውንም ጣለለትና በራሱ ላይ ወረደች፡፡ በእርሷም የዮርዳኖን ወንዝ ለሁለት ከፍሎ ተሻግሮባታል፡፡ 2ኛ ነገ 2፡1-14፡፡
ኤልሳዕም እንደምኞቱ በመምህሩ በኤልያስ ላይ ያደረሰውን የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በእጥፍ ስለተቀበለ ኤልያስ የዮርዳኖስን ወንዝ አንድ ጊዜ ሲከፍል ኤልሳዕ ግን ሁለት ጊዜ ከፈለ፡፡ ኤልያስ አንድ ሞት ሲያስነሣ ኤልሳዕ ግን ሁለት ሞታንን አስነሥቷል፡፡

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ ኢያሪኮ ሲገባ የሀገሪቱ ሰዎች ውኃቸውን ሲጠጡት ሴቶቹ እንደሚመክኑ ነገሩት፡፡ እርሱም ‹‹ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ›› ብሎ ወደ ምንጩ ውሃ ሄዶ ጨውን ጨመረው፡፡ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ፣ እርሱን ሲጠጡ የሚመክኑትም ሴቶች ወላዶች ሆኑ፡፡ ወደ ቤቴልም በወጣ ጊዜ ከከተማው ሲወጡ ታናናሽ ልጆችን አገኘ፡፡ እነርሱም ‹‹አንተ ራሰ በራ ውጣ›› እያሉ ሲዘባበቱበት የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢረግማቸው ወዲያው ሁለት ድቦች ከዱር ወጥተው 42 ልጆችን ገደሉ፡፡

ኤልሳዕ ሌላው የሚታወቅበት ነገር የመበለቲቷን ቤት በበረከት በመሙላቱ ነው፡፡ ሴቲቱ ወደ ኤልሳዕ መጥታ ‹‹የምታውቀው የእግዚአብሔር ሰው የሆነው ባሌ ስለሞተ አሁን ባለዕዳ ሁለቱን ልጆቼን ወስዶ በባርነት ሊገዛቸው›› አለችው፡፡ እርሱም በቤቷ ምን እንዳለ ጠየቃት፡፡ ‹‹ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም›› አለችው፡፡ እርሱም ከጐረቤቶቿ ባዶ ማድጋዎችን ተውሳ እንድታመጣ ነግሯት ማድጋዎቹን ሁሉ በጸሎቱ በተአምራት በዘይት ሞልቶላታል፡፡ እርሷም ዘይቱን ሸጣ ለባለ ዕዳው ከፈለች፡፡ የተረፈውንም ከልጆቿ ጋር ተመገበች፡፡
ነቢዩ ኤልሳዕ መካን ስለነበረችው ስለሱነማዊቷ ሴት ግያዝ ነግሮት ኤልሳዕ ካስጠራት በኋላ ‹‹በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊአለሽ›› ብለ ከነገራት በኋላ በዓመቱ ፀንሳ ወልዳለች፡፡ ልጁም ካደገ በኋላ ከአባቱ ጋር ወደ አዝመራ ወጥቶ ሳለ ታመመና በእናቱ እቅፍ እያለ ሞተ፡፡ በሞተም ጊዜ በእግዚአብሔር ሰው በነቢዩ አልጋ ላይ አስተኝታው በሩንም ዘግታበት ወጣች፡፡ ሎሌዋን ይዛ አህያዋን ጭና የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣችና የልጇን መሞት ነገረችው፡፡ ኤልሳዕም ሄዶ የሞተውን ልጇን ከሞት አስነሣላትና ‹‹ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ›› አላት፡፡ እርሷም ለኤልሳዕ ከሰገደችለት በኋላ ልጇን ወሰደች፡፡

ነቢዩ ኤልሳዕ የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንን በዮርዳኖስ ውኃ እንዲጠመቅ ካደረገው በኋላ ከለምጹ ፈውሶታል፡፡ ንዕማንም ከለምጹ ከዳነ በኋላ ለኤልሳዕ ወርቅና ብር ልብስም ሊሰጠው ሲል አልሳዕ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምሎ አልቀበልም አለው፡፡ ንዕማንም ‹‹እነሆ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ›› ብሎ ከመሰከረ በኋላ ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር ወስዶ ወደ ሀገሩ ሶርያ ሄደ፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ ግን ንዕማንን በመንገድ ተከትሎ ‹‹ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋልና አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ›› በማለት በኤልሳዕ ስም ዋሽቶ ተቀበለ፡፡ ኤልሳዕም ግያዝ በሥውር ያደረገውን ዐውቆ አዘነ፡፡ ወደ እርሱም ተመልሶ በመጣ ጊዜ ‹‹ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ‹‹ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? ›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ ‹‹እንግዲህስ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ለዘላለምም በዘርህ ላይ ይጣበቃል›› አለው፡፡ ግያዝም እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡ ከዚህም ሌላ ኤልሳዕ ውኃ ውስጥ የወደቀውን የብረቱን ምሳር በውኃው ላይ ዕንጨቱን ጥሎ የሰመጠውን ብረት ተንሳፎ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡

የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በዱር ሰፍሮና ተደብቆ ሳለ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ ‹‹ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ በዚያ ባለመሄድ ራሱን አዳነ፡፡ የሶርያም ንጉሥ ባሪያዎቹን ጠርቶ ‹‹ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ ንገሩኝ?›› አላቸው፡፡ ከባሪያዎቹም አንዱ ‹‹ጌታዬ ሆይ በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል›› አለው፡፡ የሶርያ ንጉሥ ኤልሳዕ ያለው በዶታይን እንደሆነ ሲነግሩት የዶታይንን ከተማ ከበባት፡፡ የኤልሳዕ ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ የከበባቸውን ጭፍራና ፈረሶቻቸውን ሲመለከት እጅግ ፈራ፡፡ ኤልሳዕም ‹‹ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ›› አለው፡፡ ‹‹አቤቱ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ›› ብሎ በመጸለይ የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፡፡ ኤልሳዕም በጸሎቱ ሁሉንም ዕውር አደረጋቸው፡፡ ወደ ሰማርያም እየመራቸው ከወሰዳቸው በኋላ ዳግመኛ ያዩ ዘንድ ጸለየና ሁሉም ማየት ቻሉ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን ‹‹አባቴ ሆይ?›› ባለው ሰዓት እንዳይገድላቸው ይልቁንም አብልቶ አጠጥቶ እንዲልካቸው ነገረው፡፡ እነርሱም በልተው ጠጥተው ሲያበቁ ወደ ጌታቸው ሄዱ፡፡

ከዚያም በኋላ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወጥቶ ሰማርያን ከበባት፡፡ በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ በሀገራቸው የሶርያ ሰዎች ሰፍረው ተቀመጡ፡፡ በዚህም ጊዜ እናት ልጇን ቀቅላ እስክትበላ ድረስ እጅግ አሠቃቂ ታላቅ ርሃብ ሆነ፡፡ ይህም ክፉ የርሃብ ዘመን በነቢዩ ኤልሳዕ ጸሎት በአንዲት ቀን ተለውጦ የጥጋብ ዘመን ሆኗል፡፡ 2ኛ ነገ 6፡8-33፣ 7፡1-20፡፡ ኤልሳዕም በዘመኑ ትንቢትን እየተናገረ እጅግ ታላላቅ ተአም
ራን እያደረገ እግዚአብሔርንም ሕዝቡንም ሲያገለግል ከኖረ በኋላ ሰኔ 20 ቀን ዐርፏል፡፡ ከሞተም በኋላ ዐፅሙ የሞተን ሰው አስነሥቷል፡፡ 2ኛ ነገ 13፡21፡፡ ይኸውም የሞአብ ሰዎች አገራቸውን ከበው ሳለ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አደጋ ጣዮች አዩአቸው፡፡ እነርሱም ደንግጠው ሬሳውን በአልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት፡፡ በዚህም ጊዜ ሬሳው የአልሳዕ ዐፅም በነካው ጊዜ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሥቶ በእግሮቹ ቆሟል፡፡

የነቢዩ የቅዱስ ኤሌሳዕ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 21-አምላክን በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተአምራት አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥር ቤት ያዳነችበት ዕለት ነው፡፡
+ ታላቅ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ጌታችን ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሥጋው ፍልሰት ሆነ፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ በተባለው በንጉሣችን በዐፄ ዳዊት ዘመን የነበሩትና ከእርሱም ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸው የኢየሩሳሌሙ አባ ዮሐንስ ዐርፈዋል፡፡
ነቢዩ ቅዱስ ኢዩኤል፡- ይኸውም ቅዱስ ነቢይ የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር፡፡ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም መኖርና የሕይወትን ትምህርት ማስተማሩን በትንቢት ተናግሯል፡፡ ደግሞም በጌታችን ላይ ይደርበት ዘንድ ስላለው መከራው ትንቢት ተናገረ፡፡ በሐዋርያት፣ በሰባ ሁለቱ አርድእትና በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- ‹‹በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ፤ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ፣ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ፡፡ ያንጊዜም ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል፡፡››
ነቢዩ ኢዩኤል ዳግመኛም ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት ትንቢት ሲናገር ‹‹ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፣ ከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል›› አለ፡፡ ነቢዩ የትንቢቱን ወራት ከፈጸመ በኋላ እግዚአብሔርን አገልግሎ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
የቅዱስ አልዓዛር የሥጋው ፍልሰት፡- ይኸውም ቅዱስ አልዓዛር ከሞተ ከ4 ቀን በኋላ ጌታችን ከሞት ያስነሣውና ተአምሩን ያደረገለት ሲሆን እርሱም ወንጌልን እየሰበከ ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገ ክርስትናን አስፋፍቷል፡፡ በተሾመባት ቆጵሮስ ከተማም የመጀመሪያው ጳጳስ በመሆን እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ መጋቢት 17 ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
ቅዱስ አልዓዛር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ ከክርስቲያን ነገሥታት መካከል አንዱ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቁስጥንጥንያ አፈለሰው፡፡ ሊያፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የድንጋይ ሣጥን ውስጥ ሆኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት፡፡ በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ፡- ‹‹ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው፡፡›› ይህንንም ጽሑፍ ባነበቡ ጊዜ ደስ ተሰኝተው ተሸክመው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰዱት፡፡ ካህናቱም ሁሉ በዝማሬ በክብር ተቀበሉት፡፡ ባማረ ቦታ አስቀምጠውት በዚህች ዕለት በዓሉን አደረጉለት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
የኢየሩሳሌሙ አባ ዮሐንስ፡- ከደጋግ ክርስቲያን ቤተሰብ ተወልደው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምረው ነው ያደጉት፡፡ በቅስና ማዕረግ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ አባ ዮሐንስ በጾም በጸሎት ምጽዋትም በመሥጠት፣ድኆችን በመርዳትና በስብከታቸው በእጅጉ ይታወቃሉ፡፡ ከብዙ ተጋድሎአቸውም በኋላ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት ሆኑ፡፡ ሰውም ስለ ቅድስናቸው በጣም ይወዳቸው ነበር፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔርን በትጋት እያገለገሉ ሳለ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስ አባ ዮሐንስን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ዐፄ ዳዊትን እንዲለምኗቸው ነገሯቸው፡፡ እስላሞች በእስክንድርያ እያመፁ ሲያስቸግሩ የኢትዮጵያው ንጉሥ ዐፄ ዳዊት ሄዶ ፈጅቷቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ዐፄ ዳዊት እስላሞችን እንዳይፈጃቸው መልአክት ይነግሩት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር አገሩ ንጉሥ ጠየቃቸው፡፡
አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያው ንጉሥ ዐፄ ዳዊት የሚላኩ ሰዎችን ከመኳንንቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ከሀገር ታላላቅ ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ የኢየሩሳሌምን አባ ዮሐንስንና የምስሩን አገር አባ ሳዊሮስን በአስተዋይነታቸው፣ በዕውቀታቸውና በቅድስናቸው መርጠዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ላኳቸው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን ታዛዥ ሆነው ወደ አገራችን መጡ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት አሽከሮቹን አስከትሎ ወጥቶ ሄዶ አክብሮ ተቀበላቸው፡፡ ከእነርሱም በረከትን ተቀበለ፡፡ እነርሱም የአባ ማርቆስን ደብዳቤ ሰጡት፡፡ ዐፄ ዳዊትም ደብዳቤውን ተቀብሎ አንብቦ ለሊቀ ጳጳሳቱ ቃል ታዛዥ መሆኑን ገለጠላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስን ወደ ሀገረ ስብከታቸውና ሕዝባቸው ተመልሰው ይሄዱ ዘንድ አልተዋቸውም ስለ ቅድስናቸውና ስለ ትምህርታቸው ጣዕም በጣም ወዷቸዋልና በእርሱም ዘንድ እንደ መላእክት ሆነዋልና፡፡ ከጥቂት ወራትም በኋላ አባ ዮሐንስን ከዚህ ዓለም ድካም ያሳርፋቸው ዘንድ እግዚአብሔር ወዷልና ጥቂት ሕማም ካገኛቸው በኋላ ዐርፈዋል፡፡ የአባ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
እመቤታችን ለሐዋርያው ማትያስ ያደረገችለት ተአምር፡- የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡ ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡
እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!
22 ዓመት ተረግዞ ኖሮ በኃላ በጸሎታቸው ኃይል ፂምና ጥርስ ያለው ልጅ እንዲወለድ ያደረጉት፣ ታቦተ ጽዮንን 40 ዓመት ያጠኑ፣ አንበሳን 7 ዓመት ውኃ ያስቀዱት፣ ንግሥናን ንቀው የመነኑ ታላቁ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ጥቅምት 21 ቀን ዕረፍታቸው ነው፡፡

አቡነ አላኒቆስ የትውልድ ቦታቸው ሸዋ አንኮበር ሲሆን አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ይኩኖ አምላክ ነው፡፡ ንጉሡ አባታቸው ‹‹አግባና መንግሥቴን ይዘህ ተቀመጥ›› ቢላቸው እርሳቸው ግን ንግሥናን በመናቅ እምቢ ብለው ሄደው ከእመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቀው ቢለምኗት እምቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹ክፍልህ ምናኔ ነው፣ የአባትህ መንግሥት ያልፋል የልጄ መንግሥት ግን ዘላለማዊ ነው›› አለቻቸው፡፡ ጻድቁም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሄደው በዚያው መንኩሰው ገዳሙን እያገለገሉ ተቀመጡ፡፡ ከጸሎታቸው በኋላ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበርና አንድ ቀን እንዲሁ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ሲጥሉ መላእክት አውጥተዋቸዋል፡፡ አቡነ አላኒቆስ ወደ አክሱም እንዲሄዱ ታዘው ከሄዱ በኋላ በዚያም የጽላተ ሙሴ የታቦተ ጽዮን አጣኝ ሆነው 40 ዓመት ተቀምጠዋል፡፡ እመቤታችንም ተገልጣላቸው በዓታቸውን እንዲያጸኑ ከነገረቻቸው በኋላ ከአክሱም ወጣ ብሎ የሚገኘውን ማይበራዝዮ ገዳምን መሠረቱ፡፡ በዚያም እጅግ አስገራሚ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እያስተማሩ አገልግለዋል፡፡

አንድ ቀን መኰንኑ ወደ ሩቅ ቦታ ሲሄድ ቤተሰባቸውን ለንስሓ አባታቸው አደራ ሰጥተው ሄዱ፡፡ የንስሓ አባታቸውም የአቡነ አላኒቆስ ጓደኛ ነበሩ፡፡ መኰንኑም ከሄዱበት ሲመለሱ ሚስታቸው ከአሽከሯ አርግዛ ጠበቀቻቸው፡፡ ‹‹ከማን አረገዝሽ?›› ብለው ጽኑ ግርፋት ቢገርፏት ዋሽታ ‹‹ያረገዝኩት ከንስሓ አባቴ ነው›› አለች፡፡ መኰንኑም መነኩሴውን እገላለሁ ብሎ ሲነሣ መነኩሴውም ወደ አቡነ አላኒቆስ ሄደው አለቀሱ፡፡ አቡነ አላኒቆስም የመኰንኑን ሚስት ቢጠይቋት ባሏን ፈርታ ‹‹አዎ ከመነኩሴው አባት ነው ያረገዝኩት›› አለች፡፡ እሳቸውም ‹‹የተረገዘው ከዚህ መነኩሴ ከሆነ በሰላም ይወለድ፣ ካልሆነ ግን አይወለድ›› ብለው በቃላቸው አስረውና ገዝተው ሸኟቸው፡፡
በግዝታቸው መሠረት ሴቲቱ ድፍን 22 ዓመት ሙሉ ሳትወልድ በጭንቅና በጣር ኖረች፡፡ በአልጋ ላይ ሆና ተጨንቃ ስትኖር በመጨረሻ ለቤተሰቦቿ ተናግራ ወደ አቡነ አላኒቆስ ዘንድ በቃሬዛ ወሰዷትና ይቅርታ ጠይቃ እውነቱን ተናገረች፡፡ እሳቸውም ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ቢሏት 22 ዓመት ሙሉ ተረግዞ የነበረው ልጅ ትልቅ ሰው ሆኖ ጥርስ አውጥቶ፣ ፂም አብቅሎ በሰላም ተወለደ፡፡ እርሱም ከተወለደ በኋላ አባቱ ማን እንደሆነ ተናገረ፡፡ ጻድቁ አባታችንም ልጁን አሳድገውት አስተምረው አመንኩሰውታል፡፡ ስሙንም ተወልደ መድኅን አሉት፡፡ በስሙ የተሠሰራ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ጽንብላ ወረዳ ይገኛል፡፡

ጻድቁ አቡነ አላኒቆስ ሌላም የሚታወቁበት አንድ ግብር አላቸው፡፡ የማይበራዝዮ ገዳማቸው አገልጋይ የሆነው መነኩሴ በሬ ጠምዶ ሲያርሱ አንበሳ ከጫካው ወጥቶ አንዱን በሬ በላው፡፡ መነኩሴውም መጥተው ለአቡነ አላኒቆስ ነገሯቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ጸሎቴን እስክጨርስ ድረስ ወደ ጫካው ሂድና አንበሳውን ‹አላኒቆስ ባለህበት ጠብቀኝ እንዳትንቀሳቀስ ብሎሃል› ብለህ ተናገር›› ብለው ለመነኩሴው ነገሯቸው፡፡

መነኩሴውም እንደታዘዙት ወደ ጫካው ሄደው ጮኸው በሉ የተባሉትን ተናገሩ፡፡ አቡነ አላኒቆስም ጸሎታቸውን ሲጨርሱ ወደ ጫካው ሄደው አንበሳውን የበላውን በሬ አስተፍተውት በሬውን ነፍስ ዘርተውበት ከሞት አስነሥተው ዕለቱን እንዲታረስ አድርገውታል፡፡ አንበሳውንም ገዝተው ወደ ገዳማቸው ወስደው ሰባት ዓመት ውኃ እያስቀዱት እንዲያገለግላቸው አድርገውታል፡፡

አቡነ አላኒቆስ አንበሳውን አስረው ያሳድሩበት የነበረው ዛፍና ውኃ ያጠጡበት የነበረው ትልቅ የድንጋይ ገበታ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ከ22 ዓመት እርግዝና በኋላ ሴቲቱ ጥርስና ፂም ያለው ልጅ እንድትወልድ ያደረጉበት ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይም ከነቅርጹ በገዳሙ በግልጽ ይታያል፡፡ ጻድቁ ጥቅምት 21 ቀን ዐርፈው በዚያው በማይባራዝዮ ገዳማቸው ተቀብረዋል፡፡ ጸበላቸው እጅግ ልዩ ነው፣ ያላመነውን ሰው አስፈንጥሮና ገፍትሮ ይጥለዋል እንጂ አያስቀርበውም፡፡
የአቡነ አላኒቆስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

(ምንጭ፡- ማይበራዝዮ ገዳም የሚገኘው ያልታተመ የአቡነ አላኒቆስ ገድል፣ የቅዱሳን ታሪክ-87)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 22-ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ሀገሩ አንጾኪያ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነው፡፡ ከአቴናና ከእስክንድርያ ሊቃውንት የሕክምና ሙያን አጥንቷል፡፡ ከሕክምና መያው በተጨማሪ የሥዕል ሙያም ነበረው፡፡ በይህ ምክንያት በወንጌሉና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ ሥዕላዊ አገላለጽን ሲጠቀም ተስተውሏል፡፡ በእጁ የሣላቸው ቅዱሳት ሥዕላትም በተለያዩ ሀገራት ይገኛሉ፡፡
ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕላት በእኛም ሀገር እንደ ደብረ ዠመዶ፣ ዋሸራና ተድባበ ማርያም፣ ደብረ ወርቅ ማርያም… ባሉ ታላላቅ ቅዱሳት ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሉቃስ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ጳውሎስን ያገለግላቸው ነበር፡፡ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈው እርሱ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በሰማዕትነት ካረፉ በኋላ በሮሜ ወንጌልን በሰፊው ሰብኳል፡፡ መልእክቶችንም ይጽፍላቸው ነበር፡፡ ጣዖት አምላኪዎችም ከክፉዎቹ አይሁድ ጋር ተማክረው በሐሰት ከሰውት በንጉሥ ኔሮን ፊት አቆሙትና ‹‹ብዙ ሰዎችን በሥራዩ ወደ ክርስትና እምነት አስገብቷልና በሞት ይቀጣ›› ብለው ጮኹ፡፡ ቅዱስ ሉቃስም በሰማዕትነት እንደሚሞት አስቀድሞ ዐውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ በመሄድ ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘና ወንጌልን ከሰበከው በኋላ መጻሕፍቶቹንና ደብዳቤዎቹን ‹‹ወደ እግዚአብሔር መንገድ ያደርሱሃልና እነዚህን መጻሕፍት ጠብቀቸው›› ብሎ በአደራ ሰጠው፡፡ ሽማግሌውም በክብር በዕቃ ቤቱ አስቀምጦአቸው ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፏቸዋል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ በንጉሡ ኔሮን ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ ‹‹በሥራይህ ሕዝቡን ሁሉ የምታስት እስከመቼ ነው?›› አለው፡፡ ቅዱስ ሉቃስም ‹‹ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ እንጂ እኔስ ሥራየኛ አይደለሁም›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይህችን እጅህን እቆርጣታለሁ›› ካለው በኋላ ቀኝ እጁን አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሉቃስም የጌታችንን ኃይሉን ያሳየው ዘንድ ወደደና የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታ ላይ በማገናኘት እንደ ድሮው ደኅነኛ እጅ አደረጋት፡፡ በዙሪያውም የነበሩ ሰዎች ሁሉ የንጉሡም የሰራዊት አለቃ ከነሚስቱ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 477 ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ፡፡ ንጉሡም እጅግ ተናዶ ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ እነርሱም ሰማዕት ሆነው የክብር አክሊልን ተቀበሉ፡፡ የቅዱስ ሉቃስንም ሥጋ በአሸዋ በተመላ ከረጢት ውስጥ አስገብተው ወደ ባሕር ጣሉት ነገር ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ አንድ ደሴት ደረሰና ምእመናን አግኘተውት ወስደው በክብር አኖሩት፡፡
የቅዱስ ሉቃስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 23-በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተተክለው በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት አቡነ ኤልሳ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ ሀገራቸው ሸዋ ነው፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን የነበሩ ሲሆን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው በደብረ ሊባኖስ ገዳም በእጨጌነት የተሾሙ የመጀመሪያ ዕጨጌ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከማረፋቸው በፊት ‹‹በእኔ ወንበር ኤልሳዕ ይሾም ነገር ግን ዘመኑ ትንሽ ስለሆነ ከእርሱ ቀጥሎ ፊሊጶስን ትሾማላችሁ›› ብለው ለቅዱሳን ተከታይ ሐዋርያቶቻቸው ተናግረው ነበር፡፡

በዚህም መሠረት አቡነ ኤልሳዕ ተሹመው ብዙም ሳይቆዩ አንድ ዲያቆን ሞተና ሊቀብሩት ሲወስዱት በመንገድ ላይ ሳለ ድንገት ከሞት ተነሥቶ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት ኤልሳዕ አሁን ወደኔ ስለሚመጣ ፊሊጶስን ሹሙት ብለህ ተናገር ብለውኝ ነው›› ብሎ ከተናገረ በኋላ ተመልሶ ዐርፎ ተቀበረ፡፡ አቡነ ኤልሳዕም ወዲያው ዐርፈው አቡነ ፊሊጶስ 3ኛ ሆነው ተሾሙ፡፡ አቡነ ኤልሳዕ ከተጋድሎአቸው ብዛት የተነሣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ጎናቸውን አሳርፈው ተኝተው አያውቁም ነበር፡፡ ነገር ግን ማረፍ ሲኖርባቸው በወንበር ላይ ተደግፈው ትንሽ ብቻ ያርፉ ነበር፡፡ አቡነ ኤልሳዕ በሞት ያረፉትም እንደልማዳቸው ጎናቸውን ሳያሳርፉ በወንበር ላይ እንደተደገፉ ነበር፡፡ አባታችን ስለዚህም ጉዳይ ሲናገሩ እንዲህ ይሉ ነበር፡- ‹‹ነፍስ ትጋትን ትወዳለች፣ ሥጋ ግን ይደክማል፡፡ ለመነኮሳትና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ መኝታ ማብዛት አይገባቸውም፡፡ መኝታ ማብዛት ሕልምን ያመጣል፣ ነፍስን ይጎዳል፣ ሰውነትንም ያደክማል፡፡››

አቡነ ኤልሳዕ በዘመናቸው ወንጌልን በማስተማርና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቁ ነበር፡፡ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ እሳቸውም ሙት አስነሥተዋል፡፡ ባሕር እየከፈሉ ቀደ መዛሙርቶቻቸውን ያሻግሩ ነበር፡፡ በጸሎታቸው የዠማን ወንዝም ለሁለት የከፈሉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡
✞ ✞ ✞

ዳግመኛም ዛሬ ለአባቶች ሊቃ ጳጳሳት 52ኛ የሆኑት የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም በዘመናቸው ከነበረው ከኢትዮጵያው ንጉሥ ጋር ለየት ያለ አስገራሚ ታሪክ የነበራቸውና ብዙ ተአምራትን ያደረጉ ናቸው፡፡

እንዲሁም በዚህች ዕለት የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ዲዮናስዮስ በዐላዊው ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክሲምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ እኚህንም ቅዱስ ከሃድያኑ ነገሥታት በያዟቸው ጊዜ ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ሥቃዮች አሠቃዩአቸው፡፡ ማሠቃየትም በሰለቻቸው ጊዜ በዚህች ዕለት የአቡነ ዲዮናስዮስን ራስ በሰይፍ አስቆረጡት፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ፡፡
✞ ✞ ✞

ልመናው ጸሎቱ በረከቱ በሁላችን ይደርብንና የልዳው ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡- አግበራ በምትባል አውራጃ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የታጸች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ በድላይ የተባለ አንድ አረማዊ ገዥ ወደ እርሷ በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በአመጽ ገብቶ ከሚስቱ ጋር ከሴሰነ በኋላ በእሳት አቃጠላት፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብም ይህን በሰማ ጊዜ በሰማዕቱ፣ በእመቤታችንና በተወዳጅ ልጇ ኃይል ይህን አረመኔ በድላይን ለመውጋት ተዘጋጀ፡፡

ከሃዲው በድላይም በበኩሉ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ለመውጋት ተነሣ፡፡ ውጊያውንም ለመጀመር በተነሡ ጊዜ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ፈረሰኛ ሰው በበድላይ የጦር ሠራዊት ውስጥ ታየ፡፡ ከኋላ ሆኖ ይነዳቸዋል፣ በሌላ ጊዜም ከፊት ሆኖ ይመራቸው ነበር፡፡ ከንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ አጠገብ ባደረሳቸው ጊዜ ግን ያ ነጭ ፈረሰኛ ከበድላ ሠራዊት ተለይቶ የበድላይን ጦር ለመውጋት ከንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብ ሠራዊት ጋራ ተቀላቀለ፡፡ በክርስቲያኖቹና በአረማውያኑ መካከል ጦርነቱ በበረታ ጊዜ አረማውያኑ ተሸነፉ፡፡ አለቃቸው በድላይም በጦርነቱ መካከል በጦር ተወግቶ ወድቆ ሞተ፡፡

በድላይም ክፉ አሟሟት ሲሞት ባዩት ጊዜ ከሠራዊቱም መካከል ብዙዎቹ ‹‹በድላይ ከልቡ ትዕቢት የተነሣ ክፉ አሟሟት ሞተ፣ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ይዋጋለቸው ነበርና በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ሰናክሬም እንደተዋረደ፣ በዮዲትም ዘመን ሆሎፎርኒስ እንደተዋረደ በድላይም ዛሬ ክፉኛ ተዋረደ›› ተባባሉ፡፡ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብም በእመቤታችንና በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የአረማውያንን ሬሣ ምድርን እስኪሸፍናት ድረስ በጦርነቱ አሸናፊ ሆነ፡፡ የሞቱትና ተማረኩትም ብዛታቸው በቁጥር አይታወቅም ነበር፡፡ ዘመናዊ የሆኑት የጦር መሣሪያዎቻቸውም እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ ራሱ ንጉሡ በድርሳኑ እንደገለጸው ‹‹ወደ ቤተ መግሥቴ የገባው የራሳቸው የሰዎቹና የፈረሶቻቸው ጌጥ በያይነቱ ሊናገሩት የማይቻል እጅግ አስደናቂ ነበር›› አለ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አረማውያንን ስለመውጋቱ አረማውያኑ ራሳቸው ሲመሰክሩ ‹‹በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በግልጽ ሲዋጋን የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር›› አሉ፡፡ ክርስቲያኖቹም ‹‹ሰማዕቱ እረዳን›› በማለት ተደሰቱ፡፡

በዚያም የጦርነቱ ቀን ሌሊቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ በስሙ በታነጸች ወደ አንዲት ሌላ ቤተ ክርስቲያን ሄደና የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ ወይም ወታደር ተመስሎ ለአንድ ቄስ ተገለጠለት፡፡ ጦሩን በእጁ ይዟል፣ ፈረሱም በጣም አልቦት ነበር፡፡ የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ አምሳል ለቄሱ የተገለጠለትም ‹‹ዛሬ ከበድላይ ጋር ጦርነት ውዬ መጣሁ›› አለው፡፡ ስለዚህም እኛ የክርስቶስ ወገኖች የቅዱስ ጊዮርጊስን የተአምራቱን ማረጋገጫ ምስክር ከራሱ አገኘን፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎቱ በረከቱ የረድኤቱም ሀብት የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችን ይጠብቀን፡፡ የዓሥራት ሀገሩን ቅድስት ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!!!
"አቡነ ዮሐንስ ዘውራ"
በዚኽች ዕለት ጥቅምት በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ስታስበው የሚውሉት አቡነ ዮሐንስ ውራ ኢየሱስ ገዳምን የመሠረቱት ሲሆኑ ጌታችን ከገነት ዕንጨቶች የተሠሩ ታቦታት አምጥቶ የሰጣቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የአባታቸው ስም የማነ ብርሃን የእናታቸው ስም ሐመረ ወርቅ ይባላል፡፡

የፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት፣ የቅኔ፣ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የፍትሐ ነገሥት እና የባሕረ ሐሳብ መምህር
የሆኑት ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ ይባቤ በላይ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረጕሙት የአቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ ገድል እንደሚናገረው ጻድቁ በሰባት ዓመታቸው ይኽችን ዓለም
ንቀው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ኹለተኛ ልጅ ወደሆነው አባ ጸጋ ኢየሱስ ዘንድ ሔደው 5 ዓመት እየተማሩ ተቀምጠው በ12 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡ ከዚኽም በኋላ አቡነ ዮሐንስ ወደ
ዋልድባ በመሔድ አባቶችን ማገልገል ጀመሩ፡፡ መነኰሳቱም ሌሊትና ቀን እንዲገለግሏቸው በሥጋ ቊስል ሁለንተናው ለተላና ለሸተተ ግብሩ ለከፋ ለአንዲ መነኵሴ ሰጧቸው፡፡ በሽተኛውም መነኵሴ አቡነ ዮሐንስን ይረግማቸው አንዳንድ ጊዜም ይደበድባቸው ነበር፣ ነገር ግን አቡነ ዮሐንስ በዚህ ከማዘን ይልቅ ደስ እያላቸው ያንን ሊቀርቡት የሚያሰቅቅ በሽተኛ በማገልገል ለዓመታት አስታመሙ፡፡

እንዲሁም የዋልድባ መነኰሳትን መኮሪታ በማብሰል፣ ቋርፍ በመጫር እና ዕንጨት በመልቀም፣ ውኃ በመቅዳት ገዳማውያንን ያገለግሉ ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን
በዋልድባ የሚኖር በክፉ በሽታ ተይዞ የሞተ አንድ መነኵሴ ሞቶ ሣለ ሽታውን ፈርተው መነኰሳቱ ለመገነዝ ፈሩ፣ ነገር ግን አበ ምኔቱ ለመገነዝ ወደ ውስጥ ሲገባ አቡነ ዮሐንስ
አብረው ገቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ወደሞተው መነኵሴ ቀርበው አቀፉት፣ በዚኽም ጊዜ ጥላቸው ቢያርፍበት ያ የሞተው መነኵሴ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሣና ‹‹ከሞትሁ 3ኛ ቀኔ
ነው፣ አይቶ የጎበኘኝ የለም፣ ዛሬ ግን የእግዚአብሔር ሰው የገዳማት ኮከብ የቅድስት ውራ ገዳም መነኰሳት አባት፣ የማይጠልቅ ፀሓይ፣ የማይጠፋ ፋና ወደ ሰባቱ ሰማያት ወጥቶ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን ዙፋን የሚያጥን አባታችን ዮሐንስ ባቀፈኝ ጊዜ ነፍሴ ከሥጋዬ ጋር ፈጽማ ተዋሐደች፤ አምላክን የወለደች እመቤታችን ማርያምም ‹ንዑድ ክቡር ቅዱስ በሆነ በዮሐንስ ጸሎት ከሞት አስነሥቶ ሕያው አደረገህ› አለችኝ›› ብሎ ተናገረ፡፡

ዳግመኛም እመቤታችን አባ ዮሐንስን ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው እርሳቸውን ሲጠብቁ የኖሩትን ሦስት ታቦታት ያመጡ ዘንድ አቡነ ዮሐንስን እንዳዘዘቻቸው ተናገረ፡፡ በዚኽም
ጊዜ የዋልድባ መነኰሳትና የገዳሙ አለቃ ‹‹ለፍላጎታችን አገልጋይና ታዛዥ አደረግንህ ይቅር በለን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወድቀው ለመኗቸው፡፡ አባታችንም ‹‹አባቶቼ ሆይ! እናንተ ይቅር በሉኝ፣ ይህ የሆነው ስለ እኔ አይደለም፣ ስለ ክብራችሁ ነው እንጂ›› አሏቸው። መነኰሳቱም በትሕትናቸው ተገርመው እያለቀሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሸኟቸው፡፡ በዚኽም ጊዜ አባታችን ዕድያቸው ገና 19 ነበር፡፡

አባታችን ዮሐንስም ጎልጎታ ደርሰው ከቅዱሳት ቦታዎች ተባርከው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ፡፡ በዚያም 500 ዓመት የኖረ ኹለተኛ እንጦንስ የተባለ አንድ ባሕታዊ አገኙ፡፡
እመቤታችንም አባ እንጦንስን ታቦተ ኢየሱስን፣ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ታቦተ ጽዮንን እያስጠበቀችው ይኖር ነበር፡፡ አባ እንጦንስም አቡነ ዮሐንስን ባገኛቸው ጊዜ በልቡ ተደስቶ በመንፈሱ ረክቶ ‹‹በዐይኖቼ አንተን ያሳየኝ በጆሮዎቼም ቃልህን ያሰማኝ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፣ እመቤታችን ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በእጇ የሰጠችኝን ያስጠበቀችኝን እነዚኽን ታቦታት ተቀበለኝ›› ብለው ሦስቱን ጽላት ‹‹ወደ ሀገርህ ይዘህ ሒድ›› ብለው ሰጧቸው፡፡ አባታችን ዮሐንስም ‹‹…እኔ እርሱ አይደለሁም፣ እንዴት አወከኝ?›› ሲሏቸው አባ እንጦንስም ፈገግ ብለው ‹‹ከሞተ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት የሆነውን ሰው በጸሎትህ ከሞት ካስነሣኸው በኋላ ከሀገርህ ከኢትዮጵያ ከዋልድባ ገዳም ከተነሣኽ ዘጠኝ ወር ነው፤ ይኽንንም የእግዚአብሔር መላእክት ነገሩኝ ‹መምጣቱን ተስፋ የምታደርገው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከሀገሩ ዛሬ ተነሣ› አሉኝ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ዮሐንስም ‹‹እመቤታችን ማርያምን እንዴት አገኘሃት?›› አሏቸው፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ከልጇ ከወዳጇ ጋር በብርሃን መርከብ ላይ ተቀምጣ መላእክት፣ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት ሲከቧትና በክብር በምስጋና ሲሰግዱላት ግንቦት 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ አገኘኋት›› አሏቸው፡፡

እመቤታችንም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹ፈቃድህን ለሚያደርጉ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ የመዳን ተስፋ ስጠኝ› አለችው፡፡ ጌታችንም ያንጊዜ መላእክትን ከገነት
ዕንጨትና ዕብነ በረድ፣ ከጎልጎታ መቃብሩና ከጌቴሴማኒ አፈር እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ መላእክትም የታዘዙትን አምጥተው በሰጡት ጊዜ ጌታችን ከገነት የመጡትን ዕንጨትና ዕብነ በረድ ሦስቱን ታቦታት አድረጋቸው›› በማለት አባ እንጦንስ ለአባ ዮሐንስ ነገሯቸው፡፡ አቡነ ዮሐንስም ሦስቱን ጽላት ይዘው አንዲት እንደፀሓይ የምታበራ ድንጋይ
እየመራቻቸው ሰኔ 12 ቀን ጎጃም ደረሱ፡፡ ድንጋዩዋንም መንገድ እንድትመራቸው የሰጣቸው ጌታችን ነው፡፡ ከዚያም ውሮ ተብሎ የሚጠራ አንድ ባላባት ቤት ገብተው አድረው በሚገባ ተስተናግደው በቀጣዩ ቀን ድንጋዩዋ እየመራቻቸው ቅዱሳን ከነበሩበት ጫካ ወስዳ አገናኘቻቸው፡፡ ቅዱሳኑም ለአቡነ ዮሐንስ ‹‹የጠበቅንልህን ይኽችን ቦታ ተረከበን የዘለዓለም ማረፊያህ ናትና›› ብለው እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ፡፡ አባታችንም ታቦተ ኢየሱስን በዚኽች ገዳም ተክለው ቦታዋን መጀመሪያ በተቀበላቸው ሰው በውሮ ስም ‹‹ውራ ኢየሱስ›› ብለው ሰየሟት፡፡

አባታችን ጊዜ ዕረፍታቸው ደርሶ ከማረፋቸውም በፊት ጌታችን እመቤታችንን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳንን፣ ሰማዕታትን አስከትሎ መጥቶ ‹‹…ጸሎት አድርጎ መልክህን የደገመ እባብ አይነድፈውም፤ መብረቅ አይገድለውም›› የሚል ድንቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹ስምህን የጠራውን፣ መታሰቢያህን ያደረገውን፣ በበዓልህ ቀን ማኅሌት የቆመውን፣ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውን ያጻፈውንያነበበውን የሰማውን፣ እጅ መንሻ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን እምርልሃለሁ፣ ልጆቹንም እስከ 15 ትውልድ እባርክልሃለሁ፤ በገዳምህ በውራ መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ እባብ ሰውን አይገድልም፣ የማይጸድቅ ሰው ወደ ገዳምህ አይመጣም›› አላቸው፡፡

የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!


“የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 65)
----------
11፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።

12፤ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።

13፤ ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም። "
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለሁላችሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን ወምእመናት እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።መጪውን ዘመን የሰላም የፍቅር የንስሐ ዘመን እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።


ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።
💐የመጽሃፍ ቅዱስ ፕሮግራማዊ ጥናት ተጀመረ💐👉ከመጽሃፍት ሁሉ የተለየውንና የከበረውን የእግዚአብሄርን ቃል ለማንበብ ያስባሉአስበውስ በስኬታማነት አንብበዋል ወይስ እንዳሰቡ አነባለው እንዳሉ እስካሁን ቆይተዋል
📖"ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም"📖
—ማቴዎስ 4: 4

🔷#ለእርስዎ የእግዚአብሄር ቃል ለጠማዎ ቤተሰቦቻችን እነሆ መልካም ዜና አለን። በየህይወት መንገድ ቻናላችን ከአዳዲስ አገልግሎቶቻችን አንዱ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ነውና።

📌 ፕሮግራሞን እና የእለት ተእለት ተግባሮን በማያሻማ መልኩ ሁሌም መጽሃፍ ቅዱስ የማንበብ ልምድ እንዲኖርዎ ከእግዚአብሄር ከፈጣሪዎ ጋርም ያለዎት ግንኙነት እንዲዳብር እያገዝን የሚያነቡትንም 📖የመጽሃፍቅዱስ📖 ክፍል በየእለቱ እያጋራንዎ አብረንዎ እንቆያለን።

👉አዎን ከእግዚአብሄር መቅረብ እፈልጋለው ለኔ ጽፎ ያስቀመጠልኝን ቃሉን አንብቤ አካሄዴን ከእርሱ ጋር ማድረግ እፈልጋለው። እርሱንም ማገልገል እፈልጋለው #የምትሉ የእግዚአብሄር ቤተሰቦች #መንፈሳዊ ቻናላችንን በመቀላቀል የጥናቱ ተካፋይ እንዲሆኑ እንጋብዛለን።

🔵ይቀላቀሉን🔵
👉@yehywetmenged
👉@yehywetmenged
👉@yehywetmenged
2024/06/03 07:08:55
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243