Telegram Web
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት ይጀመራል፡፡
--------------------------------------------
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር “Enrollment Kit” ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሶስት ሰሚስተሮችን ትምህርት ብቻ ይሸፍናል።
---------------------------------
የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ሶስት ሲሚስተሮችን ብቻ ያካተተ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ሚኒስቴሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ፡፡

በዚህም መሰረት የ11ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ12 ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር በፈተና አወጣጥ ሄደት ውስጥ የሚካተት ሲሆን በተመሳሳይ የ7ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር ብቻ በ8ኛ ክፍል ፈተና ውስጥ የሚካተት ይሆናል።፡

ትምህርት ቤቶችም ያለፉትን ሶስት ሲሚስተሮች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የማካካሻ ትምህርት ለ45 ቀን እንደሚሰጡ ተነግሯል።

ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እና አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የሚገኙ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ጀምረዋል፡፡

ያለፈው አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተፈታኞችም ከጥቅምት 16 እስከ 30 2013ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡
ጥቅምት 30 ቀን እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የክለሳ ትምህርት እንዲቀጥል መወሰኑንም አስተዳደሩ ገልጿል፡፡

አስተዳደሩ ተማሪዎችን ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ በተቀሩት ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተቀመጡ ደረጃዎችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስከሚጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቢሮው ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Grade 8
ቀን 18 / 3 / 2013 ዓ.ም

ማስታወቂያ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25/3/2013 ዓ/ም የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎቻችሁ በሰሃቱ በመገኘት ፈተናዉን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://www.tgoop.com/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/


ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
በአዲስ አበባ ከተማ የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እና 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እና 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በግል ትምህርት ቤቶቸ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21/3/2013 ዓ/ም እንደሚጀመር እና እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28/3/2013 ዓ/ም መሰጠት የሚጀምር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25/3/2013 ዓ/ም እንደሚሰጥም ምክትል ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆናል፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80% ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል።

የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ውጤታችሁን በየትምህርት ቤቶቻችሁ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
https://vm.tiktok.com/ZMe12AMpP/

Are you a full-time secondary, middle, or high school teacher serving students between 12 and 18 years old? Have you ever thought about applying for an exchange program? If so, you are in luck! The U.S. Embassy is pleased to announce that we are accepting applications for the 2021-2022 Fulbright Teaching Excellence and Achievement (Fulbright TEA) Program. The Program brings international secondary-level teachers to the United States for a six-week program. Successful applicants would attend academic seminars for professional development at a host university and observe and share their expertise with teachers and students at the host university and at local secondary schools. For the eligibility criteria and application, go to https://bit.ly/36gAwaD. The deadline to apply is February 16!
Share it with you teachers🙏

Tech01 Society in partnership with Admission Counseling Inc.
@tyoniit
ሰበር ዜና !!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ።
__________________________-

ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮሮና ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት የ2012ዓ.ምሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29, 2012ዓ.ም እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ከየካቲት 21-27,2013ዓ.ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIAL ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIAL ⇲◉
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ተለቋል።

ውጤት ለማየት http://result.neaea.gov.et የሚለውን በመጫን ይግቡ። በመቀጠለም የመለያ ቁጥሮን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ።

በሌላ አማራጭ 8181 ላይ የመለያ ቁጥራችሁን በመላክ ውጤት ማወቅ ይቻላል።
የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ተለቀቀ፡፡

ተማሪዎችም ከታች በተገለጸዉ በየነ መረብ መሰረት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ የምችሉ መሆኑን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችም እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት በማድረግ የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎችም አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- http://result.neaea.gov.et/Home/Placement
• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

👉 ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63 ነጥብ 9 በመቶ ያህሉ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆነ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት ዓመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጿል።

ለውጤቱ መመዝገብም የኹሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ጀምሮ በኦላይን መመልከት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የዌብሳይቱን አድራሻ ከጥቂት ሰዓታ በኋላ እንደሚያሳውቅም ቢሮው ገልጿል።

የኢትዩትዩብ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
2024/06/16 01:10:37
Back to Top
HTML Embed Code: