Telegram Web
ግንቦት 21 #ደብረ_ምጥማቅ
@eotcy
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነዉ

👉ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ
@eotcy
👉 እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ

👉ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል
@eotcy
👉ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል ሁለተኛም ደግሞ ፃድቃን በአንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ

👉ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር
@eotcy
👉 እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳይኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል
@eotcy
👉እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ

👉ለአባቶቻችን የተለመነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛም ትለመነን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን "አሜን"


👉 ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
#ለቻናሉ_ቤተሰቦቼ 😘

አንድ የቆሎ ተማሪ ይለምን ዘንድ ወደ ከተማዋ ወጣ በእንተ ስሟ ለማርያም እያለ ለመነ የሰጠው የለም ስለ እግዚአብሔር አለ የተመለከተው የለም ሁለም እግዚአብሔር ይስጥህ ከማለት በቀር አንድስ እንኳን የሚላስ የሚቀመስ አጣ በዚህ ተበሳጭቶ ወደ ቤተ ሲሄድ መንገድ ላይ የሚያስተምሩትን አባት አገኛቸው ምነው ልጄ ማዘንህ ቢሉት

ተወኝ የኔታ ከጠዋት ጀምሬ ስንከራተት ዋልኩ ግን እግዚአብሔር ይስጥህ ከማለት ውጪ ምንም አላገኘሁም ኧረ ሰው ከፍቷል አባ አለ ተማሪው

ልጄ ተሞኘህ እግዜር ይስጥህ ከማለት የበለጠ ቸርነት አለን
እግዚአብሔር የሚሰጠውስ ከሰው ጋር እኩል ይሆናልን አሉት ይሄን እያሰበ ወደቤቱ ሄደ ከሁሉ እርሱ እንዳተረፈ ገባው እናም እንዲህ አለ

እግዜር ይስጥህ በሉኝ ✟
የሀገር ሀብታችሁን እየነገራችው ከምታስደስቱኝ
የጣፈጠ ምግብ እያቀረባችሁ ከምትመግቡኝ
በለመለመ መስክ እያስቀመጣችሁ ከምታሳርፉኝ
ስለ ወላዲቷ እግዜር ይስጥህ በሉኝ
ቢበርደኝ የተዋበውን ልብስ አትስጡኝ
ቢጠማኝ ይጠማኝ ዘንድ ውሀ አትስጡኝ
ለእግሬ ጫማ አልፈልግም
ለፊቴ ዘይት አልመኝም
እተኛበት ንፁሕ ፍራሽ እበላ ዘንድ ትንሽ ቁራሽ
አልጠይቅም
ለመኖሬ ማህተም ከሞት ማምለጫ አይሆኑኝም
ይልቁን ከሻታችሁ የልቤን ደስታ
ከገባችሁ የኔ እውነት ምኑም ነገር አይመችም እግዚአብሔር የሌለበት

ቤተሰቦቼ ስለዚህ እኔም ልበላችሁ የምትወዱኝ እህት ወንድሞቸ እግዚአብሔር ይስጥህ በሉኝ በሱ ፈንታ እኔን በማርያም በእናቴ።

በቸር ቆዩልኝ 

ባይሆን ቻናሉን ለወዳጆ በመጋበዝ ካሱኝ🙏

https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌 አስራት በኩራት ምንድነው
📌 ጥቅሙስ

መስጠት ማለት በኩራት፣ አስራት፣ መባና ልዩ ስጦታን ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲሆን ማቅረብ  ይኸውም ያለንን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር እንደተቀበልን ማሳያና ለእግዚአብሔር ያለንን አክብሮት ፍቅርና አምልኮ የመግለጫ መንገድ ነው።

የስጦታ ዓይነቶችና ትርጉማቸው፦

👉 አስራት
ዘፍ 14፡20፣ ዕብ 7፡4-5
- አስራት በብሉይ ኪዳን ከአስር አንድ እጅ ማለት ነው - ዘፍ 28፡22።
አስራት በአዲስ ኪዳን ግን ከአስር አንድ እጅ ባለፈ በዘራኸው ልክ ነው - 2ቆሮ 9፡6-7
- አስራት የእግዚአብሔር ንብረት ነው - ሚል 3፡8-10
- አስራት የሚሰጡ (የሚያስገቡ) ሰዎች በታማኝነት የእግዚአብሔርን ንብረት መልሰው ለእርሱ የሚሰጡ ናቸው - ዘዳ 14፡22-23
- አስራትን በማስገባት (በመስጠት) ውሰጥ በረከት አለ - ሚል 3፡8-10

👉 በኩራት
በኩር (የመጀመሪያ) ከሚለው ቃል የወጣ ነው። በኩራት የእግዚአብሔር ነው - ዘፀ 23፡19፣ ዘሌ 23፡10-11
- በኩራት መስጠት ማለት እግዚአብሔርን በነገሮቻችን ሁሉ ማስቀደም ማለት ነው - ዘኁ 3፡13፣ ዘዳ 15፡19
- የበኩራት ስጦታ ትዕዛዝ ነው - ዘፀ 13፡2፣ ዘዳ 26፡2
- የመጀመሪያውን ስንሰጥ ያለን ነገር ይባረክልናል - 1ሳሙ 2፡20-21

👉 መባ -
እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ገቢ አስራት አውጥተን ከሚቀረው ድረሻችን ላይ ለወንጌል ስራ፣ ለድሆች መርጃ፣ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የምሰጠው ስጦታ ነው። ይህ አይነቱ ስጦታ በልብ ደስታ በራሳችን ውሳኔ በአቅማችን መጠንና ከዚያም በላይ የምንሰጠው ይሆናል - ዘፀ 25፡1-5፣ 2ቆሮ 8፡1-2፣ ዘፀ 34፡20

👉 የፍቅር ስጦታ
ለእግዚአብሔር ቤት ስራና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ፍቅርን ለመግለጽ የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ ጊዚያቶች ሊደረግ ይችላል - ሐዋ 11፡27-30፣ ፊሊ 4፡16-18

#የምንሰጥበት_ምክንያት እና #አላማ

#እግዚአብሔር_እንድንሰጥ_አዟል - ዘፀ 25፡1-5፣ ዘሌ 25፡31፣ ዘኁ 18፡21ቤት

ስጦታችን የእግዚአብሔርን መንግስት የማስፋፋት ስራና የእግዚአብሔር  አገልግሎት ላይ የሚውል ነው - 1ቆሮ 9፡4-14፣ 2ቆሮ 8፡4፣ ፊሊ 4፡15-18

በመስጠት እግዚአብሔርን እናከብራለን፣ እናመልካለን - ምሳ 3፡9-10

በመስጠት የእግዚአብሔርን በረከት እንለማመዳለን - ሚል 3፡10-12፣ ሉቃ 6፡10ታማኝ

በመስጠት ለእግዚአብሔር  እንሆናለን (አንሰርቀውም) - ሚል 3፡8-10

👉 እንዴት መስጠት እንዳለብን

❗️የምንሰጠው አስቀድመን ራሳችንን ለእግዚአብሔር በመስጠት ነው -

❗️የምንሰጠው በሃዘን (በግድ) ሳይሆን በደስታ ነው -

❗️የምንሰጠው እንደገቢያችን ብቻ ሳይሆን ከጉድለታችንም ጭምር መሆን አለበት -

❗️የምንሰጠው ለሰዎች ለመታየት መሆን የለበትም -

❗️የምንሰጠው በስጦታችን ለመመካት መሆን የለበትም -

ስለ ስጦታ ያስተማረንና አስቀድሞ ያሳየን ራሱ እግዚአብሔር ነው። ከስጦታዎች በላይ የሆነውን ስጦታ ለሰው ልጆች ሰጥቷል (ዮሐ 3፡16-30፣ ሮሜ 8፡32)። ይህ በምድራዊ ቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ ላመኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ አድርጓል። ቤተ ክርስቲያን ይህንን የምስራች ለአለም ሁሉ ለማድረስ እንድንችልና የእግዚአብሔርን ቤት ስራ እንድትሰራ አማኞች የታዘዙትን የፈቀዱትን ስጦታ ለወንጌል መስጠት አለባቸው።

https://www.tgoop.com/eotcy
+ረፈደ አትበል+

ሰይጣን እኛን ከሚያዘናጋበት መንገድ አንዱ ወደ ጽድቅ የምትሄድበት ጊዜ አሁን ረፍዷል "አሁን እኮ ትዳር መስርተሃል"ብዙ ሀላፊነት አለብህ "ደግሞም ብዙ ጓደኞች አፍርተሃል"እነሱን ትተህ ወዴት ትሄዳለህ?መፅሐፋም እሚለው በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ነው ሆኖም ግን አንተ ወጣትነትህን በአጋጉል ቦታ አሳልፈኸዋል "አሁን በቃ መንፈሳዊነት ካንተ protocol ጋር አይሄድም ፣በዚያ ላይ ያልሰራኸው ሀጢያት የለም ፣እንዴት ፈጣሪስ ይቅር ይልሀል ? እያለ ከተተበተብንበት የሀጢአት እስራት እንዳንወጣ የተቻለውን ያደርግል። እኛም ደግሞ ከዚህ ለመውጣት የተቻለንን አናደርግም! 😓


ወንድሜ ስማኝማ ልንገርህ አብርሃም የሀጢአት ምሳሌ ከሆነችው ከካራን በ 75 አመቱ ነው ነበር የወጣው፣ ከአገርህ ከዘመዶችህ ከአባትህ ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ሲለው ምክንያት አልደረደረም ፣እሺ ብሎ ነው የወጣው ። ወንድሜ በሃጢአት ያረጀህ ከመሰለህ ፣እንደ አብርሃም 75 ዓመት አልሞላህምና ተቻኩለህ ቶሎ ውጣ ፤ እንደ ሀገር መኖርያ ካደረከው በደል ቶሎ ውጣ !አባትና እናትህን ማክበር አስትተው አባት እና እናት ከሆኑብህ ኃጢያቶች ቶሎ ውጣ!!

ብቻ አንተ ውጣ እንጂ ፣ አንተን ታላቅ ሕዝብ ማድረግ ፣ ከነዓን ማስገባት ለእግዚአብሔር አይሳነውም ። የእርሱ ወዳጅ ስትሆን አብዝቶ ይባርክሃል በል ቶሎ በል ወንድሜ ዛሬውኑ ከካራን ውጣ እግዚአብሔርንም ይዘህ ጉዞ ወደ ከነዓን ጀምር !!!
         
   ውጣ ውጣ እባክህ ወንድሜ ረፈደ አትበል !ውጣ!!!
          ውጪ ውጪ እህቴ ረፈደ ሳትይ ውጪ !!!
እባካችሁን ወንድም እህቶቼ እንውጣ 🙏
መልዕክቱን ለጓደኞቻችሁም አስተላልፉ ዳግም።
    (ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ )
       ፣ተግባር ላይ ለማዋል እንጠንክር ችላ አንበል። 🥰
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

https://www.tgoop.com/eotcy
እውነት እስኪ ይችን እውነታ አንብቡልኝ

ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታየ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንደት ይሆናል
የሰላምታሽ ድምፅ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና" ሉቃ.፩÷፳-፵፫🙏
#ልብ_በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንደት የተመረጠች ናት
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ቃል አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሏታል ምን አይነት መመረጥ ነው
ሰላምታዋን በሰማ ጊዜ በማሕጸን ያለ ጽንስ እንኳ በደስታ የዘለለ ምን አይነት ቅድስና ነው
@eotcy
ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ኤልሳቤጥ ካመሰገነች ድንግል ማርያምን ፕሮቴስታንት አላመሰግንም የሚል ምን ተሞልቶ ነው
በመልአኩ አንደበት ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የተባለችን እናት እኛም እንደመልአኩ እናመሰግናታለን።
እኛስ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እመቤታችንን
እንዳመሰገነቻች ኤልሳቤት እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እናመሰግናታለን መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እንድትመሰገን
ሲያደርግ አይተናል። የጌታዬ እናት እንላታለን በመንፈስ ቅዱስ ሆና የጌታዬ እናት አንች ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንደት ይሆንልኛል፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፣ የማህጸንሸ ፍሬ የተባረከ ነው.....እያልን እናመሰግናታለን
ይህን ያደረገ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልፅ አይተናልና።
@eotcy
ሰማያዊ መልአክና ምድራዊት ሴት ተባብረው በአንድ ቃል በአንድ መንፈስ ቅዱስ ያመሰገኗትን አላመሰግንም የሚሉ በምን መንፈስ ሆነው ነውመንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን አስመሰገነ እንጅ ሲከለክል አላየንም። አላመሰግንም የሚሉ ከምን እንዳገኙት እንኳ አይነግሩንም።
ሰይጣንና ክፉ የገንዘብ ፍቅር ክብሯን ሸፍኖባቸዋልና።
እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተረዳነው እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳጼጥ እናመሰግናታለን።
ሁላችችንም እንደ ቅዱስ ዮሐንስ በእምነት ወደቤታችን ወስደናታል

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
@eotcy    @eotcy
"ባልሽን የገደልሽው መርዟ አንች ነሽ"

ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።

ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦ "እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።

እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ"። አለቻት።

ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"

እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦

1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ

2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ

3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው

4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር ታዘዥው

5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ

6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይው ድረስ ብቻ ነው።

እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።

ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።

እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽ ስጭው" አለች።

ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"

እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት

ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለ ፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።

እናትየዋ፦  ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላው ሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውን ትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠት ያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽ የምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።
ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ ፍቅር ስጭው!

እንዲህ በጥበብ ትዳርን የሚያክል ተቋም የሚታደጉ እናቶችን፣ አባቶችን እግዚአብሔር ያብዛልን።አሜን!

ብታጋሩት መልካም ታደርጋላችሁ።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy
@eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አምናለሁ_እና_አላምንም +

ልጁ የታመመበት አባት ነው። ጌታን " #ቢቻልህስ_ልጄን_ፈውስልኝ " አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።

ይህን ጊዜ ሰውዬው  " #ወዲያውም_የብላቴናው_አባት_ጮኾ#አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24

የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው "

ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም

ያምናል እንዳንል " #አለማመኔን " ይላል ፤ አያምንም እንዳንል " #አምናለሁ " ይላል። የቸገረ ነገር ነው ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም  ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው " የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::

እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው #የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::

አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ  "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::

ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ #አላውቀውም:: #የምተርከው_ክርስቶስ_እንጂ_የሚተረክ_ክርስትና_የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::

#መች_በዚህ_ያበቃል::

እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢኃት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::🙏

እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው::🙏
ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው🙏 እላለሁ::

እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ?
ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም:: 😭

ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው::🙏
እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው::🙏
አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው::🙏
እማራለሁ አለመማሬን እርዳው::🙏
ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy
@eotcy
@eotcy
ክርስቲያን ከሆንክ እነዚህን 7 ነገሮች መቼም አታድርግ

1. ለንስሐ ተዘጋጅ ወደ ቤተክርስቲያን ና ወገብህን ሱሪህን ታጠቅ

2. ነገርን ሁሉ በ3ቱ መሥፈርት ሳትመዝን አትቀበል
☞︎︎︎ መጽሐፍ ቅዱስ
☞︎︎︎ አዋልድ መጻሕፍት
☞︎︎︎ ቅዱስ ትውፊት

3. ለማብዛትም ሆነ ምን አለበት ብለህ መቼም ቢሆን
☞︎︎︎ ከአህዛብና
☞︎︎︎ ከመናፍቃን
ጋር አትተባበር። እነርሱ ካሉ እግዚአብሔር ይለይሃልና❗️
ብርሃን ከጨለማ ጋር ህብረት የለውምና❗️

4.ምንም ነገርን ከመቀበልህ ከመንቀፍህና ከመደገፍህ በፊት:-
☞︎︎︎ እንደ ክርስቲያን ለፈጣሪህ ንገር
☞︎︎︎ እንደ ሰው አገላብጠህ መርምር

5.ከእግዚአብሔር እና የርሱ የሆኑት በቀር ፈጽመህ ምስጢርህን አትግለጽ❗️
ኋላ ተወግተህ የምትሞተው ባወጣኸው ምስጢር:- አመንኩት ባልከው ሰው ነውና❗️

6.የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ትጠብቅ ታስጠብቅም ዘንድ ቸል አትበል❗️
አጥሩ ከፈረሰ ቤቱም መፍረሱ ፣ መዘረፉም አይቀርምና❗️

7.በሰማይ ካለው እግዚአብሔር እና ወዳዶቹ በቀር በሥጋ ለባሽ አትታመን❗️ አትከተለው፣ አታድንቀው፣ አታምልከው

በዚች በተቀጥተኛዋ ሀይማኖታችን ፀንተን የመንግስቱ ወራሾች ያድርገን

ወሰብሐት ለእግዚአብሔር

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
➲ ልብ የሚነካ አሳዛኝ ታሪክ 😢


🚺 በጣም ከወደድኩት ታሪክ ላጋራችሁ

እናቱን የሚወድ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ፅሁፍ መልካም ንባብ

ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለችኝ።

ውዷ ባለቤቴ ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት እማ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት ፈልጋለሁ አልኳት ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችሕ ምን ሆኑ ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ።

አብሽሪ እማ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው"አልኳት በጣም ደስ አላት ተስማማች ወደማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀችኝ ነበር እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫችጭኗታል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቺያት ጉዞ ጀመርን።

እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል "ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ" በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን "እማ ምረጪ" አልኳት ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ ላንብብልሽ አልኳት "ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር አሁን እዳህን ክፈል" ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት።

የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም ደስታ በደስታ ሆናለች
በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ "እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?" አልኳት በእንደዚ ቀን ና ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና " አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ ትጋብዥኛለሽ አልኳትና ተለያየን።

በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበትን
ምሽት ናፈቀኝ ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም እናቴ ወደ
ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን ወደነበረው ምሽት ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል።
@eotcy
ግራ ተጋባው ማነው እንዴት ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ ግብዣው ከደብዳቤው ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል :-"ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር
የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው በኔ ፋንታ ውዷባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!" ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት...!
@eotcy
ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን ወላጆቻችንን የምናስታውሰው ? ...ስንቶቻችን ነን ለራሳችን ስንሯሯጥ ወላጆቻችንን የረሳነው..? ስንቶቻችንስ ነን የእናት ፍቅር ያልገባን
ወላጆቻችን በህይወት ያሉ መቼም አይደለም ጊዜው አሁን ነው

እባካቹህ ሀሳባቹህን አካፍሉን🙏 👇👇 @eotcy_comment


"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ጉድለትህን ተጠቀምበት

ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶሰን ለማግኘት ተቸገረ። ሕዝቡ ብዙ ነው የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት። የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው።

እሱ ዛፍ ላይ ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም። ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኪዎስን ጠራው።

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው።
"ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው። ጌታ ወደ ቤቱ ገባ ለዘኪዎስ ቤት መዳን ሆነለት።

ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር። ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሊጣላ ሊቆይ ይችል ነበር።

ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር።
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉስ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው። የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር።
እግዚአብሔር የማዳኑን ቀን የቆጠረለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር። በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው።

ስለ ቁመቱ የማወራ እንዳይመስልህ።
ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ። እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም።

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም እሱን ማለቴ ነው። ይሄ ይጎለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር እጥረትህ መክበሪያህ ነው። ጉድለትህም መዳኛህ ነው።
ችግሮችህ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምታባቸው መስታዎቶችህ ናቸው

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን። በጉድለትህ እንደ ዘኪዎስ ከፍ በልበት። ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም።
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ።
በቤትህ መዳን ይሆንልሀል፡፡ ከዚያም ስላጠረህ ስለተጎዳህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ።

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው። ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2


@eotcy
@eotcy
@eotcy
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች በረሃ ውስጥ እየተጓዙ እያሉ ድንገት አለመግባባት ተፈጠረና አንደኛው አንደኛውን በጥፊ ይመታዋል። የተመታው ጥፊው ቢያመውም ምንም ሳይናገር ዝም አለና
አሸዋው ላይ ዛሬ የምወደው ጓደኛየ በጥፊ መታኝ ብሎ ፃፈ ከዛም እየተጓዙ እያሉ ትልቅ ባህር ያለበት ወንዝ ያገኙና መታጠብ ፈልገው ይገባሉ እየዋኙ እያሉ ያ በጥፊ የተመታው ልጅ ይሰምጣል በዚህ ስዓት ጓደኛው እንደምንም ብሎ ሂወቱን ያተርፈዋል ከሞት የተረፈው ልጅ ቋጥኝ ድንጋይ ፈልጎ ድንጋዩ ላይ እየፈለፈለ ዛሬ የምወደው ጓደኛዬ ሕይወቴን አተረፈኝ ብሎ ፃፈ ጓደኛውም ገርሞት ቅድም በጥፊ ስመታህ አሸዋ ላይ ፃፍክ አሁን ከሞት ሳተርፍህ ደግሞ ድንጋይ ላይ ለምን እንደዚህ አደረክ አለው። ጓደኛውም እንዲህ አለው የምንወዳቸው ሰዎች ሲበድሉን በደላችንን የይቅርታ እና የምህረት ንፋስ እንዲያጠፋው አሸዋ ላይ መፃፍ አለብን ጡሩ ነገር ሲያደርጉልን ግን ውለታቸውን እንዳንረሳ ሁሌም እንድናስታውሰው ድንጋይ ላይ መፃፍ አለብን አለው።

ባለህም በሌለህም ነገር ሁሉ አመስግን አንተ አለህና።
ሰላሙን ያምጣልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን
https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሳቹሁ  
 
           ዕርገት

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡

ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡    

እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
https://www.tgoop.com/eotcy
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡


@eotcy
✧━━━━━━━━━━━━━━━✧
     ❍ㅤ            ⎙ㅤ           ⌲                        ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ          ˢᵃᵛᵉ           ˢʰᵃʳᵉ
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
እንኳን አደረሳቹሁ                ዕርገት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ…
እንኳን አደረሳችሁ

ለመባረክም እጁን በሐዋርያቱ ላይ ያኖር ዘንድ ቆመ። ሰውነቱን ከመለኮት ክብር ያሳትፋት ዘንድ ወደላይ ከፍ ከፍ በማለት ራቃቸው። ስለሰው ልጆች ፍቅር በምድር ላይ ያገኛት ያለፈው መከራ ተፈጸመ አሁን ግን ያለመለየት በተዋህዶ በመለኮት ክብር ዐረገ። በአብም ቀኝ ተቀመጠ።

የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለመሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን ታጅቦ ዐረገ መለኮቱ ይተጋለታልና። ወደ አየራትም ነጥቆታልና። ኪሩቤል ሊያሳርጉት አልመጡም። እርሱ ራሱ በመለኮት ኃይል አብን ተካክሎ በቀኝ ተቀመጠባቸው። የማረጉም ምስጋና ለእኛ መሰላል ኾነን።

ከገሊላ ሴት እንደተወለደ በአሰብን ጊዜ ወደ አባቱ እንደአረገ እናስታውሳለን። በድንግል ማርያም ጭኖች እንደታቀፈ ስናስታውሰው በአባቱ እቅፍ እንዳለ እናስባለን። በደብረ ዘይት ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደተቀመጠ ባሰብነው ጊዜ በመላዕክቱ እልልታ እንደ ዐረገ በአባቱም ቀኝ እንደተቀመጠ እናስታውሰዋለን። ከምድር ወደሰማይ የሚያደርሰን የሃይማኖታችን መሰላል እርሱ ነው።

        🌺አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 🌺
     https://www.tgoop.com/eotcy
አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት
አንድ ቀን በምስጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው
መሬት ጠብ..ጠብ አለ። ምእመኖቹ ጨነቃቸው ምን ሆነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው "ጌታዬ ሆይ እባክህ ለቅዱስ ስጋህና ለክቡር ደምህ አብቃኝ" ነበር የሚሉት።

ምእመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም "አንተን ለማገልገል ለስጋና ለደምህ አብቃኝ" እያልኩ ነው። አሏቸው። ምእመኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርሰዎ እኛን እያቆረቡ እንዴት እንድህ ይላሉ አሏቸው። እርሳቸውም "የመስቀሉ ፍቅር ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለግልበት ስጋና ደሙንም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበትን ቀን ነው የምለምነው" ብለው መለሱ።

ወዳጆቼ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ። ለስው የምንሰራ ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። "አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው" እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው አይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን።

አንዳንዶቻችን፦ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መፆም፣ መስገድ፣ መፀለይ፣ መቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ፣ነጠላ መልበስ ግዴታ አልያም ህግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን። መቼ ነው ግን ፍቅሩ ገብቶን ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደረስብናል ብለን ሃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዙ ነን።

አምላክን ፈርተን ሲኦል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን ሁሉ እንተዋለን። ግን ስለ ፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ሃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን? ወገኖቼ እየሰበክን እየዘመርን እያስቀደስንና እየቀደስን ያልዳን አለንና እርሱ ፍቅሩን ይሳልብን።
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ

የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።

የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ  የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።

እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦

ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤  እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።

ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
       እኛ ግን፦
"አማንኬ ይደልወኬ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሊ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።
      ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

Https://www.tgoop.com/eotcy
ከቅዳሴው ማብቂያ ተዐምርሽ ሲነበብ ስሰማ የተፃፈው ያንስብኛል🙏🙏
ብዙዎች ጣዕምሽን ያልቀመሱ ቀምሰው ያላመኑ የካዱ ንጽሕት ሆነሽ ተገኝተሽ  አዳምን ከእስራት እንዳስፈታሽ የረሱ የሄዋንን  ታሪክ እንደቀየርሽ የዘነጉ ጌታ ጌታ እያሉ  እናቱን አንቺን የሚንቁ የሚያናንቁ ለክብርሽ  መንበርከካችን  የሚያስገርማቸው  ለምስጋናሽ ከሚገባሽ በታች  ጎንበስ ማለታችን የሚገርማቸው  ፍቅርሽን ያላጣጣሙት እናትነትሽን የካዱ ንዋይ አታሏቸው አንቺን መውደዳች ተዐምርሽን ሰምተን ለሚመስላቸው እንዴት ብዬ ላሳያቸው ለኔ ያደረግሽው_ለኔ_የሰራሽው በመጽሐፍ የሰፈረው  የተነገረልሽ  ለኔ  ካደረግሽው  እጅጉን  እንደሚያንስ  🙏🙏🙏🙏
ፍቅርሽን ቀምሶ ከመካድ  እናትነትሽን ከመካድ በምልጃሽ ጠብቂን 🙏 ለአዳም እህቱ የኖህ መርከቡ የያዕቆብ መሰላል የጌታዬ የመድኀኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስ  እናቱ  ላንቺ  ክብርና  ምስጋና  ይሁን🙏🙏🙏
ማርያም ሆይ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ምህረትና ይቅርታን አሰጪን🙏🙏
💚💛❤️

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
2024/06/16 08:14:53
Back to Top
HTML Embed Code: