ጎሪላን ለማየት ልዩ መነጽር
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) አንድ ጎሪላ ከእንስሳት መኖሪያው አምልጦ አንዲት ሴት ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ፣ የጎብኝዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ልዩ የሆነ መፍትሄ ተገኘ። በሮተርዳም መካነ አራዊት ውስጥ በ2007 ዓ.ም ቦኪቶ የተባለ ጎሪላ፣ በተደጋጋሚ ይመለከት የነበረችውን ጎብኚ በማሳደድ ከግቢው ማምለጥ ችሎ ነበር።
በመጥፎ አጋጣሚው ተጎጂዋ ሴት ከጎሪላው ጋር ቀጥተኛ የዓይን ግንኙነት በመፍጠር “እየተገዳደርኩህ ነው” የሚል መልእክት አስተላልፋለች በሚል ግምት፣ ከእርሷ እና ሌሎች ጎብኚዎች ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት እንዲኖረው አንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ “ቦኪቶ መነጽር” የሚል ልዩ መነጽር አዘጋጅቷል።
ይህ ካርቶን መነጽር ከጎን የሚያይ ዐይን ምልክት ያለበት ሲሆን፣ ጎብኚዎች መነጽሩን አድርገው ጎሪላውን በቀላሉ ለማየት የሚያስችላቸው ትናንሽ ቀዳዳዎችም አሉት። በዚህም ጎሪላው የሰውየውን ቀጥተኛ እይታ ስለማያይ ቁጣው ይቀንሳል።
ይህ ፈጠራ የዓይን ግንኙነት በእንስሳት ዓለም ውስጥ ምን ያህል ስሜታዊ እና ጠንካራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጨዋታ እንግዳ ላይ ከመዓዛ ብሩ ጋር በነበረው ቆይታ ላይ መዓዛ እንዲህ ስትል ጠየቀችው ፦ “ዶ/ር ዳዊት ላንተ የተሠጠህ ትልቁ ሥጦታ የቱ ነው ?" “ዶ/ር ዳዊት፦ ሁሌም ይህን ጥያቄ ስጠየቅ በተደጋጋሚ የምመልሰው መልስ ይሄንን ነው።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሬዝዳንት ሆኜ ስሠራ አንድ ምስኪን ገበሬ ከአምቦ አካባቢ ልጃቸው በጠና ታሞ ይዘው መጥተው እንከታተልላቸው ጀመር ልጁም ከቀን ወደ ቀን ለውጥና መሻሻል ማሳየት ጀመረ፡ አባትም ቢሮዬ ድረስ መጡ። “ዶክተር እንደው እባክህ ከድፍረት እንዳታይብኝ እባክህ ብለው ተጨናነቁ” ፤ ምንድነው አባቴ? አልኳቸው እሳቸውም ወጣ ብለው ማዳበሪያ ተሸክመው መጡ ። ማዳበሪያ ውስጥም በቆሎ እሸት ነበረ ። “ይሄ ነው የደረሰው ብለው” እሱን ሲሰጡኝ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር፡ ተርፏቸው ሳይሆን ካላቸው ላይ ነበረ ለኔ ሥጦታ ብለው ያመጡልኝ።”

❤2
ፋና ቴሌቪዥን እንዴት ከዚህ በላይ ሊወርድስ ሊዋረድስ ይችላል?
(ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)
****
ጉዳዩ የኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት የመዋልና ያለመዋል አይደለም። ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የዳመራ በዓል ነው። ነገ ደግሞ መስቀል ነው። ኢሬቻ ደግሞ ገና ሳምንት ቅዳሜና እሁድ የሚከበር ነው ።
ምንድነው ፋና ያሰበው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ተከታዮችን መበሳጨት ለምን ፈለገው? ምንድነው ያስቸኮለው? የዚህ ልጥፍ ዓላማውስ ምንድነው? ከእሁድ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በየቀኑ ሁለት ጊዜ ቢለጥፈውስ ምን አለ? ለምን ሆን ብሎ እልህ ማገባባቱንና የተገፊነት ስሜት መፍጠሩን?
አሁንም ግልጽ መሆን ያለበት ከኢሬቻም ሆነ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" ጋር ማንም ሰው ጠብ የለውም። ግን ምንድነው ትልቅ ሆኖ በጭቃ መጫወት? ሚዲያ ሕዝቦችን ለማቀራረብ እንጂ እንዴት ለልዩነት ይሰራል ? ምንድነው እየተፈለገ ያለው?

👍1
ይህ ባህል አገራችን ኢትዮጵያ ቢጀመር ባይ ነኝ በ40 አመታቸው እማዬ እራት ደርሷል ማለት ይቀር ነበር ⁉️
በአውሮፓዊቷ ሀገር ዴንማርክ "Kanelsvend" ብለው የሚጠሩት አዝናኝ ባህል አላቸው. አንድ ሰው ወንድም ይሁን ሴት እስከ 25ኛ አመታቸው ድረስ ትዳር ያልመሠሰረቱ ከሆነ የ 25ኛ አመት የልደት በአላቸውን በሚያከብሩበት ቀን ላይ እስካሁን ለምን ሳታገቡ ተብለው መንገድ ላይ አውጥተው ወንበር ላይ ታስረው እንዲቀመጡ ይደረግና በዙሪያቸው ያሉ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው የተፈጨ ቀረፋ እያመጡ እንዲደፉባቸው ይደረጋል
እስከ 30ኛ አመታቸው ድረስ ካላገቡ ደግሞ ቀረፋው ወደ በርበሬ ይቀየራል ...🙆♂😭😂

ስፖርትና ፖለቲካ! ራሺያና እስራኤል! ንጉስ ካንቶና
እኔ ኤሪክ ካንቶና እባላለሁ። ለፈረንሣይ ብሄራዊ ቡድንና ለማንቸስተር ዩናይትድ ተጫውቻለሁ። እግር ኳስ ዓለምን በሁሉ መስክ በፖለቲካው በኢኮኖሚው በባህል ያስተሳሰረ ኋያል የዓለማችን ተወዳጁ ስፖርት ነው።
ግን ፍትሃዊነቱን ከቅርብ ግዜ ወዲህ እጠራጠራለሁ ስፖርት በሚፈልገው አንድነት ሁሉን በዕኩል መነፀር በሚያይበት መንፈስ እየተጓዘ ነው ብየም አላምንም።
እግር ኳስ በጠቅላላው በዚህ ወቅት ሚዛኑን አዛብቷል። ፍትህን አጓሏል። ስፖርት እንደ እስራኤል ያሉ ሀገራትን ከመድረኩ ማገድ ነበረበት።
ለምን ካላችሁ? ራሺያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች ገና 4ኛ ቀኑ ዓለም ተረባረበባት። ገለልተኞቹ የሚባሉት እንደ FIFA, UEFA, IOC ያሉ የስፖርት ማህበራት ዘመቱባት። ራሺያ ይኸው እስካሁን ከአለም ዋንጫና ከአውሮፓ ውድድሮች እንዲሁም ከታላቁ የኦሎምፒክ ጨዋታ መድረኮች እንደታገደች ክለቦቿ ከማንኛውም ውድድር ተሳትፎ እንደተገለሉም ነው።
716 ቀናት ሙሉ ይኸው ዛሬም ድረስ የማያባራ ጭፍጨፋ በምስኪን ፍልስጤማውያን የምትፈፅመው እስራኤል ግን በሁሉም መስክ በስፖርቱ ትካፈላለች። ክለቦቿ ብሄራዊ ቡድኗ ስፖርተኞቿን ያገለለ የተቃወመ አንዳች ተቋም ወይ ሀገር ግን በምድራችን የለም። እኮ ለምን?
ስፖርት ዘር ሀይማኖት ቀለም የሌለው ሰላምን እኩልነትን ፍትሃዊነትን አንድነትን የሚሰብክ የሰው ልጆች ሁሉ የነፃነት መድረክ ከሆነ እስራዔልን ለምን ዝም አለ?
ለዚህ ነው ስፖርት እግር ኳስ ከወትሮ ድንቅ የሰላም የአንድነት ሁሉን የሰው ልጅ እኩል ከሚመለከትበት መርሁ አፈንግጧል የምለው። በጋራ ትብብር ይህንን ማውገዝ ያስፈልጋል። ስፖርት ያለኛ ደጋፊዎች ምንም ነው። ሀይላችንን ለዕንዲህ ዐይነት 2 መስመር በረገጡ ተግባራት ላይ በአንድነት ማሳየት መቃወም አለብን።

በእርዳታ ስም ኪሳቸውን የሚያደልቡ፣ እፍረት የሌላቸው ደፋሮች።
TikTok ላይ ለሀቅ የሚረዳ ሰው ቢኖር በቁጥር 2 ወይም 3 ብቻ ነው። ፍራኦል ከኪሱ አውጥቶ ለሚረዳው ግን በዚህ ልክ ለምን ዘመቻ እንደተከፈተበት ሊገባኝ አልቻለም። "ካለኝ ላይ ላካፍል፣ ለወገኖቼ ልድረስ..." ብሎ ላለፉት 4 አመታት 2021 ጀምሮ በ TikTok አማካኝነት የበርካቶችን ህይወት አቃንቷል። በእርዳታ ስራ ውስጥ የተሰማሩ እጅግ በርካታ አይን ያወጡ ሌቦች ፊትለፊታችን ቁልጭ ቁልጭ እያሉ በዘርና በሀይማኖት ስለተሸፈኑ ብቻ እነሱ ላሽ ተብለው ፍራኦል ከኪሱ አውጥቶ ለረዳው ግን የማንም አፍ መክፈቻ ሲሆን መመልከት ያናድዳል።
.
የፍራኦል ስም እ'ን'ዲጠለሽ ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት ደግሞ ሚኪ ፊታውራሪና ማስተር አብነት ናቸው። ፍራኦል ለተረጂዎቹ የሚያደርሰው በማስተር አብነትና በፊታውራሪ በኩል ነው። ገንዘብ ለእነሱ ልኮላቸው እነሱ ደግሞ ለተረጂዎች የሚያደርሱት።
ነገር ግን ቃል ለገባላቸው ሰዎች ልኮ [እያንዳንዱን ገንዘብ የላከበት ደረሰኝ አለ] በማስተር አብነት በኩልና በሌሎችም እንዲደርስ የተላከውን ገንዘብ በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ለተረጂዎቹ የሚደርሳቸው ግን ከግማሽ በታች የሆነው ነው። ፍራኦል ለረጅም ጊዜ በእነ ማስተር አብነትና በሌሎች 2 ግለሰቦች ሲዘረፍ ቆይቷል። እከሳቸዋለሁ እያለ ነው፤ ስላጭበረበሩት፣ ስለዘረፉት፣ መጠቀሚያ ስላደረጉት፣ ስሙ እንዲጠፋ ስላደረጉ።
በአሁኑ ሰአት ከገንዘቤም ከስሜም አልሆንኩም እያለ ነው። እስካሁን ድረስ ከ 100ሺ ዶላር በላይ [በአሁኑ ምንዛሬ 16 ሚሊየን ብር] የሚሆን ገንዘብ ለማስተር አብነትና ለሌሎች 2 ግለሰቦች እንደላከ የሚያስረዳ ሰነድ አያይዟል።
ማስተር አብነትንና ሌሎችን በህግ አጠይቃለሁ እያለም ነው። ታዲያ በዚህ ምክንያት TikTokን ትቶ ወደ FB መጥቷል።