Telegram Web
የዱር እንስሳት ፎቶግራፈር ከዛፍ ስር ከተኛበት ከእንቅልፉ ሲነሳ ከጎኑ እጁን ተንተርሳ ተኝታ ያገኛት ቺታ ግርምትን ፈጥሯል።

የዱር እንስሳት ፎቶግራፍ አንሺና የሥነ ሕይወት ተመራማሪ የሆኑት ዱልፍ ቮልከር በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ አንድ የጥበቃ ማዕከል ውስጥ እጅግ ያልተለመደና አስደናቂ ተሞክሮ አጋጥሟቸዋል። ቮልከር ከዛፍ ሥር በእንቅልፍ ላይ እያሉ ሲነቁ፣ ኤደን የምትባል ቺታ አጠገባቸው ተጠግታ በሰላም ተኝታ አገኙ።

ቮልከር ይህንን ጊዜ በካሜራው መዝግቦት የነበረ ሲሆን፣ ባልተጠበቀው እንግዳ መገኘት በፍርሃት ፋንታ መተማመን እና ንጹሕ ፍቅር ተሰምቷቸዋል። ለወራት ያህል በቺታ ኤክስፒሪያንስ ማዕከል በበጎ ፈቃደኝነት ሲሠሩ የቆዩት ቮልከር፣ ከቺታዎች ጋር ትዕግሥትንና አክብሮትን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ግንኙነት መሥርተዋል። የኤደን ረጋ ያለ ንክኪና ሰላማዊ መገኘት ጥቃትን ሳይሆን ጥልቅ ፍቅርን የሚያሳይ ነበር ተብሏል።

ቮልከር ውሻውን በሞት ካጡ በኋላ፣ ህይወታቸውን ለአደጋ የተጋለጡ የዱር እንስሳትን በተለይም ቺታዎችን ለመጠበቅ አሳልፈዋል። ቺታዎች ደግነታቸውና የማወቅ ጉጉታቸው ከሚታወቁ አዳኝ እንስሳት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

የቮልከርና የኤደን ታሪክ በዓለም ዙሪያ ተሰራጭቶ ከቫይራል ምስልነት ያለፈ ትርጉም አግኝቷል። ይህ ያልተለመደ ግንኙነት የዱር ፍጥረታት በሰው ልጆች ላይ እምነት ሊጥሉ፣ መውደድና በሰላም መኖር እንደሚችሉ የሚያሳይ ኃይለኛ ማሳሰቢያ ሆኗል።
የምድር #ባቡር ተሽከርካሪዎችን እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እያጓጓዘ ነው - ከ1940-ዎቹ አጋማሽ እስከ 1950-ዎቹ መጀመሪያ እንደተነሱ የሚገመቱ ፎቶግራፎች

#Flatbed #Freight #Wagons of the Franco Ethiopian #Railway Corporation bringing motor vehicles and construction equipment from the port of Djibouti to Ethiopia possibly in the 1950s/1960s. Source does not tell us the specific year/s
የሀገር ባለውለታ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)
ፍትህ ይፈልጋል!

ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ የተላለፈ አሳሳቢ ጥያቄ

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛና የኢትዮጵያ ስፖርት ሕያው ቤተ-መጻሕፍት የነበረው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) አሟሟት ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንዲደረግለት ጥሪ ቀረበ።

📌 የጥያቄው ዋና ነጥብ:

የሀገር ባለውለታ፣
የብዙዎችን ትውልድ ስፖርት ያስተማረውና ስለ እግር ኳስ እድገት ያልደከመው ገነነ መኩሪያ፣ በእርግጥ ራሱን አጥፍቷል በሚል የመጀመሪያ መረጃ ዙሪያ ጥርጣሬዎች መኖራቸውን ምንጮች ይጠቁማሉ።

* የመጀመሪያ ምርመራ ማስረጃ:
በጉዳዩ ላይ የመጀመሪያ ምርመራ ያደረጉ ግለሰቦች እንዳሉት፣ የተገኘው ማስረጃ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ራሱን አጥፍቶ ሞቷል የሚያስብል አለመሆኑን ያሳያል።

* የህዝብ ጥያቄ:
የገነነን ጽሑፍ ያላነበበ የስፖርት አፍቃሪ በሀገሪቱ የለም። ለኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ግለሰብ ትክክለኛ ፍትህ ሊያገኝ ይገባል።

🚔 ለፖሊስ የቀረበው ልባዊ ልመና:

ለፌዴራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ይህንን ጉዳይ ከስር ከመሰረቱ እንደ አዲስ እንዲይዙት እና እስከ መጨረሻው አጣርተው፣ ትክክለኛውን የሞት ምክንያት አውጥተው፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና ቤተሰቡ ፍትህ እንዲሰጡ በትህትና እንጠይቃለን።

ገነነ መኩሪያ በህይወት እያለ ሀገሩ ባትሸልመውም፣ ቢያንስ ከሞት በኋላ ፍትህን መንፈግ የለባትም።

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ፍትህ ይገባዋል!
2
አሳዛኝ መረጃ‼️

ከታች ምስሏን የምታዮአት ወጣት እህታችን #liza ትባላለች። በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ትምህርቷን ትከታተል ነበር።

መስከረም 27/2018 ዓ.ም ስልኳን ለማሰራት ከግቢው ወጥታ ሳትመለስ ቀርታለች።

መሰወሯን ተከትሎ በተደረገ ፍለጋም እጅግ አሳዛኝ በሆነ መልኩ የአስገድዶ መድፈር ተፈፅሞባት ተገድላ ተገኝታለች!

ይህቺ እህታችን ፍትህ ታገኝ ዘንድ ድምፅ ልንሆናት ይገባል!

#ፍትህ_ለሊዛ #jusice_for_liza
1
ተጠንቀቁ !!

እዚህ MRI ምሥል ላይ የሞታዩዎትው ሶስት ሰዎች በሙሉ አንድ መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው አደጋ ደረሰበትና ሁሉም በፅኑ ተጐድተው ሆስፒታል ገቡ ።

ከመካከላቸው አንዳቸውም የደህንነት ቀበቶ ( ሲት ቤልት) አላሰሩም ።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አደጋው በደረሰባቸው ወቅት..

በግራ በኩል ያለው ሰውዬ እግሩን አነባብሮ ነበር የተቀመጠው ።እንደምታዩት የሁለቱም እግሮች የጭን አጥንቶች ተሰባብረዋል ።

መሃል ላይ የሞታዩት ሰውየ ቀበቶ ባያስርም የተቀመጠው ግን በትክክል ነበር - የአንድ እግሩ አጥንቶች ሁለት ቦታ ላይ ተሰብረዋል .. አንድ እግሩ ተርፏል ።

በቀኝ ጥግ ላይ የሞታዩት 3ኛው ግራ እግሩን ዳሽ ቦርድ ላይ አድርጐ ነበር የተቀመጠው .. አደጋው ሲደርስ ውጤቱ ከአጥንቱም አልፎ እግሩን ቆርጦ ጥሎታል።

ወዳጆች ሆይ !
መኪና ስትነዱም ሆነ ስትሳፈሩ ቀበቶ እስሩ! ... መኪና ውስጥ በአግባቡ ተቀመጡ..

ያላችሁ ህይወትና አካል አንድ ብቻ ነው!
1
በሩሲያ ልጅ መውለድ ኢንቨስትመንት ሊሆን ነው

ሩሲያ ቤተሰቦች ልጆች እንዲወልዱ እያበረታታች ሲሆን፤ ለዚህም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ ልጆች ለሚወልዱ ቤተሰቦች ብዙ ጥቅማጥቅሞችን አቅርባለች፡፡ ጥቅማጥቅሞቹ የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

• እስከ 1 ሚሊዮን ሩብልስ የሚደርስ የገንዘብ ጉርሻ

• መኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት

• ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትና የት/ቤት ምገባ ለልጆች

• ነጻ የሕክምና አገልግሎቶች

• የመብራትና የነዳጅ ክፍያዎች ከቀረጥ ነፃና ቅናሽ

• ዓመታዊ የቤተሰብ ጉዞዎችና የእረፍት ጊዜያት

ይሄ ፖሊሲ ወደፊት ወላጅነትን ወደ ኢንቨስትመንት የሚቀይር ነው ተብሏል፡፡
2025/10/13 13:44:29
Back to Top
HTML Embed Code: