Telegram Web
#የኤሌክትሪክ_ጥገና_ለመስራት_መታወቅ_ያለባቸው_ሶስት_መሰረታዊ-ነጥቦች፦
=====================
👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃወች ወይም የቤታችን መሰመር ብልሽት ሲያስተናግድ የምናስተካክልበት መንገድ ጥገና ይባላል።
👉ብልሽት ሊይስከትሉ የሚችሉ ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው።
1. #ክፍት_የኤሌክትሪክ_መስመር ( #open_circuit)
👉የክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም
የጭነት መብዛት
የፊዉዝ መቃጠል
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መበጠስ
በደንብ አለመገናኘት ወይም አለመርገጥ
መዛግ
መላላት
2. #የተገናኘ_የኤሌክትሪክ_መስመር (#short_circuit)

👉የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም፦
የመቃጠል
የሙቀት መብዛት
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ
እርጥበት
3. #የኤሌክትሪክ_መስመር_ከአካሉ_ጋር_መገናኘት ( #grounding)
👉የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር እዲገናኙ የሚያደርጉ መንስኤዎች
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ
እርጥበት
የመቃጠል
የመላላት
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ብልሽቶች ይሁኑ እንጂ እያንዳንዱ ብልሽት አንዱ ሌላዉን እንደሚያመጣ ይታወቃል።ለምሳል የኤሌክትሪክ ሥርጭት በአቐራጭ መገናኘት ከአካሉ ጋር መገናኘትን መበጠስን ያመጣል።
ብልሽቶች በመብራት ፣ በሞተር፣ በትራንስፎርመር ላይ ተመሣሣይ ቢሆም ምልክታቸዉና የጥገና ሥራቸዉ ይለያያል።ለምሳል መብራትን የወሰድ እንደሆነ አምፖሉ ከተቃጠለ ያለዉ አማራጭ መጣል ነዉ።ሞተርን ወይም ትራንስፎርመር ሽቦ(winding) ከተቃጠለ ተጠግኖ በሥራ ላይ ይዉላል።
#ብልሽትን_የመለየት ዘዴ
👉ብልሽቶች በተለያዩ መንገዶች ይታወቃል።
👉መረጃን የማወቅ የመለየት ዘዴ አጠቃቀም አንደሰዉ ልምድ ቢለያይም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ።
በማየት
በመስማት      
በመመርመሪያ መሣሪያ በመጠቀም
#በማየት
👉የኤልክትሪክ ዕቃዎች ብልሽት ( ለምሳል ምጣድ,ምድጃ ) የተበጠሰ ወይም የተቃጠለ ከሆነ በመፍታተ ውስጡን በመመልከት ብልሽቱ ማወቅ ይቻላል።
#በመስማት
👉በመስማት ዕቃዎቹ ብልሽቱ ሲያጋጥማቸዉ ሙሉ በሙሉ ሥራቸዉን በማቐማቸዉ ብቻ ሳይሆን እየሰሩ በሚፈጥሩት ድምፅ ሊደርስ የሚችለውን ብልሽት አስቀድሞ ማስተካከል ይቻላል።
#በመመርመሪያ_መሣሪያ_በመጠቀም
👉ማንኛዉም የኤሌክትሪክ ዕቃ ብልሽት ሲገጥመዉ በቀላሉ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን በመጠቀም የብልሽቱ ዓይነት ለይቶ ለማወቅና ለጥገና አመቺ መሆኑንና አለመሆኑን መለየት ይቻላል።
የመፈተሻ መሣሪያዎች:-
መልቲ ሜትር
ሜገር
መብራት
ቴሰተር
#መልቲ_ሜትር
👉ይህ የመመርመሪያ የመፈተሻ መሳሪያ ቮልቴጅን ፣ከረንትንና የሬዚስታንስ መጠን የሚለካልን መሣሪያ ነዉ።
👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃዎች ሁሉ በዉስጡ ሬዚስታንስ (ከረንት ተቃዋሚ) አለዉ።
👉ከፍተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ አነስተኛ ነዉ።
👉አነስተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ መጠኑ ከፍተኛ ነዉ።
👉የተበጠሰ ገመድ ወይም ያልተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ በጣም ከፍተኛ ነዉ።
👉ያልተበጠሰ ገመድ ወይም በአቐራጭ የተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ ወደ ዜሮ ይጠጋል።
#በኤሌክትሪክ_የሚሰሩ_መሳሪያዎች_ጥገና
👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን ለመጠገን በመጀመሪያ እቃዎችን ጠንቅቆ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ።
👉በዚህ መሰረት አንድ ኤሌክትሪሺያን ማወቅ የሚገባዉ:-
እቃዉ እንዴት እንደሚሰራ መረዳት
በኤሌክትሪክ እቃ ላይ የተፃፉትን መረጃዎች ማወቅ
ለእቃዉ መጠገኛ የሚዉሉትን መለኪያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ
የሚጠገኑ እቃዎች ሲፈቱ በጥንቃቄ መረጃዎችን መሰብሰብ 
የጥገና ቅደም ተከተል መሰረት በማድረግ መታየት የሚገባቸዉ የመሳሪያዉ አካል በኃይልና በኤሌክትሪ መፈተሻ መሳሪያ መመርመር
ከኤሌክትሪክ መሳሪያው ወይም ከሚጠገኑ እቃዎች ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ሰራተኞ ወይም ግለሰቦች ስለ እቃዉ ሁኔታ ማነጋገርና መረጃ መሰብሰብ
#ለሌሎችም ያጋሩ❗️
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት_ወይም_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል
👇👇👇👇👇
0118644716
0991156969

#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
#አሜን_ኤሌክትሪካል_እና_ኤሌክትሮሜካኒካል_ስራዎች_ስራ_ተቋራጭ
👍499👏5🔥2🥰2😱1
#እጅግ_ጠቃሚ_የYOUTUBE_ትምህርቶችን_ይከታተሉ❗️
  #የትም_ሳይሄዱ_ወጪ_ሳይወጡ_በነፃ_የሙያ_ባለቤት በመሆን የራስዎን ስራ ይፍጠሩ!
#Subscribe, #Share እና  #Like በማድረግ ያበረታቱን❗️
https://www.youtube.com/watch?v=TEmw1PbmAmo?sub_confirmation=1

1. በ youtube ቻናላችን ስለሚሰጡ ስልጠናዎች ዝርዝር ማብራሪያ
https://youtu.be/sDFBV9eATRY?sub_confirmation=1
2. በህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ስለምናያቸው ዝርዝር ነጥቦች
https://www.youtube.com/watch?v=azoLC_Io30k&t=20s?sub_confirmation=1
3. ኤሌክትሪክ ስራ ከመጀመራችን በፊትና በኤሌክትሪክ ስራ ጊዜ መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች
https://m.youtube.com/watch?v=-cbxtwW5msQ&t=109s?sub_confirmation=1
4. መሰረታዊ ኤሌክትሪክሲቲ ክፍል-1
https://www.youtube.com/watch?v=eGrHbdA7Y0w?sub_confirmation=1
5. መሰረታዊ ኤሌክትሪክሲቲ ክፍል-2
https://www.youtube.com/watch?v=TEmw1PbmAmo?sub_confirmation=1
6. ኤሌክትሪክ ስራ ለመጀመር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች
https://youtu.be/b_m0Q3y63c8
7. የመልቲሜትር አጠቃቀም
https://www.youtube.com/watch?v=aQjoQyV-ypg?sub_confirmation=1
8. የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ምልክቶች/ Building Electrical Installation Symbols https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw/?sub_confirmation=1
9. ለህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ የምንጠቀምባቸው እቃዎችና ስታንዳርድ ክፍል-#1
https://youtu.be/2rtjPyOvrlo?sub_confirmation=1
10. ለህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ የምንጠቀምባቸው እቃዎችና ስታንዳርድ ክፍል-#2
https://www.youtube.com/watch?v=dn205-0E3K8?sub_confirmation=1

#በአይነቱ ልዩ የሆነውን የተግባር ስልጠናችን #ለመሰልጠን እና ማንኛውም #የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኙናል❗️
👇👇👇👇
0118644716
0991156969
👍8223🔥4🎉4😢3🥰1👏1
#የኤሌክትሪክ_ቆጣሪ_ውል_መታደስ_እንዳለበት_ያቃሉ

ደንበኞች ተቋሙ ላይ ለሚያነሷቸውን የትኛውም የመብት ጥያቄዎች ባአግባቡ መመለስ እንዲያስችል ከተቋሙ ጋር ያላቸውን ህጋዊ የቆጣሪ ውል ስምምነት ማደስ በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡

ተቋሙ ያሉትን ደንበኞች አውቆ ለሚጠይቋቸው የትኛውም አይነት የመብት ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ውል ከፈፀመ 5 አመት እና ከዚያ በላይ የሆነው ደንበኛ ህጋዊ የቆጣሪ ውል ዕድሳት እንዲፈፅሙ እያደረገ ይገኛል፡፡  

👉ውል ለማደስ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲወጡ፡-
↪️የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃ ፍቃድ፣
↪️አንድ ወቅታዊ 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
↪️የኪራይ ቤት ከሆነ ቤቶቹን ለማስተዳደር ስልጣን ከተሰጠው አካል ወይም የባለቤትነት ኃላፊነት በመውሰድ የተፃፈ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
↪️በተጨማሪም ያልተከፈለ እዳ ቢኖር ከአከራይ የተፈረመ የውል ግዴታ ሰነድ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ሰነድ በመያዝ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ማዕከል በመሄድ ውል መፈፀም ይኖርባችዋል፡፡

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ውል ማደስ የሚኖረውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውል እንዲያድሱ እንገልጻለን፡፡

ከየኢትዮጵያ ኤሌክትሪ ክአገልግሎት የተወሰደ

#በአይነቱ ልዩ የሆነውን የተግባር ስልጠናችን #ለመሰልጠን እና ማንኛውም #የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኙናል❗️
👇👇👇👇
0911585854
0991156969
#የቴሌግራም_ቻናላችን_ይቀላቀሉ❗️
👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/amenelectricaltechnology
👍27🔥31🥰1
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_አገልግሎት ከታች በተዘረዘሩት የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በካርድ ለሚሰሩ ቆጣሪዎች
ዘወትር #ከሰኞ እስከ #ዕሁድ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ መግለፁን እናስታውሳችሁ
=====================
የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ደንበኞቻችን በሙሉ

ተቋሙ በበዓላት እና በዕረፍት ቀናት ያለውን የካርድ መሙላት አገልግሎት ለደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ስር ባሉ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዕሁድ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት በተወሰኑ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የቅድመ ክፍያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን የኃይል መሙላት አገልግሎቱን ከሰኞ እስከ ዕሁድ ከላይ በተገለፁት ማዕከላት የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት የተወሰደ

#በአይነቱ ልዩ የሆነውን የተግባር ስልጠናችን #ለመሰልጠን እና ማንኛውም #የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኙናል❗️
👇👇👇👇
0911585854
0991156969
#የቴሌግራም_ቻናላችን_ይቀላቀሉ❗️
👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/amenelectricaltechnology
👍23
#አስቸኳይ_የቅጥር_ማስታወቂያ

ድርጅታችን አሜን የኤሌክትሪካል ሥራና  ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጥር ይፈልጋል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ጥር 07,2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ላይ የትምህርት ማስረጃ  ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ቦሌ ሚካኤል (ከሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ለቃለ መጠይቅ እንዲገኙ እናሳስባለን።

የስራ መደብ፡- ሬጅስትራር/የደንበኞች አገልግሎት
ደሞዝ፡- #በስምምነት
የት/ት ደረጃ፡- በኤሌክትሪካል  ኢንጅነሪንግ/በአይሲቲ ቴክኖሎጂ ድግሪ ያላት።
የስራ ልምድ፡- 0 አመት/በላይ
ፆታ፡- #ሴት
የስራ ቦታ፡-    አዲስ አበባ


አሜን ኤሌክትሪካል ሥራና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል

https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE2DpDe9fPGCTupqTg
👍31😢32👏2
#የኤሌክትሪክ_ስራ_ዋጋ_እንዴት_እንተምናለን 
#How_to_Estimate_Electrical_Work_Labour_Cost
========================
#ክፍል- 1
👉ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን በጣም ብዙ የቻናላችን ተከታታዮች ስለ #ኤሌክትሪክ_አሁናዊ_የፖይንት_ዋጋው በውስጥ መስመርና በስልክ በተደጋጋሚ ጠይቃችሁናል።
👉በመጀመሪያ በህንፃ ኤሌክትሪክ ሥራ  ፖይንት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ማየት ይኖርብናል።
👉 ፖይንት፡- በኤሌክትሪክ ሰርኪዮት ውስጥ ያሉ የሚገጠሙ ወይም የሚታሰሩ እንደ አምፖል፣ ሶኬት ወዘተ የመሳሰሉት ፖይንት ተብለው ይጠራሉ።
👉 ስራ ለመሰራት አንድ የኤሌክትሪክ ባለሙያ ወይም ድርጅት ከአሰሪው ግለሰብ ወይም ድርጅት ጋር በ3  አይነት መንገድ  ሊስማማ ይችላል።
1. #በቀን_ክፍያ(በተለምዶ ጆርናታ ተብሎ ይጠራል)
👉በሌላው አለም የኤሌክትሪክ ባለሙያ ክፍያ የሚሰላው ሥራው ላይ በሚያሳልፈው ሰዓት ተስልቶ ሲሆን በኛ ሀገር ደግሞ የሰዓት ክፍያ ብዙም ስላልተለመደ የኤሌክትሪክ ባለሙያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎችም በቀን  ክፍያ በመነጋገር በሀገራችን የስራ ህግ  የተቀመጠውን የስራ ሰዓት ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሰሩና  በቀን ክፍያ ተስማምተው የሚሰሩት ነው። በቀን ክፍያ ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሙያዎች አሁን ላይ በሀገራችን ከ 350-600 ብር ድረስ ይከፈላቸዋል። ነገር ግን አብዛኛው የክፍያ መጠን በዚህ ምድብ ውስጥ ይሁን እንጅ ከዚህ በታችም ሆነ በላይ የሚሰሩ አይጠፉም።
#ይቅጥላል----

#የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን❗️
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
👏11👍82🎉2
#ክፍል- 2
2. #በግምት (በፎርፌ)
👉ይህ ዘዴ ደግሞ አንደኛ ላይ እንዳየነው #በቀን ክፍያም 3ኛ ላይ እንደምናየው #በፖይንትም ሳይሆን በፍሎር ወይም ሙሉ ሥራውን ይህን ያህል ብሎው ዋጋ በማውጣት የሚሰራ የስራ ስምምነት አይነት ሲሆን ይህን ዋጋ ለመተመን የሚረዱ መነሻ ሀሳቦችን ከዚህ ፅሁፍ መጨረሻ ላይ የምናይ ይሆናል።
3. #በፖይንት
👉ይህ የስራ ስምምነት አይነት ሁሉም የስራ አይነቶች ተዘርዝረው ለእያንዳንዱ ስራ በፖይንትና በሜትር የሚከፈልበት የስምምነት አይነት ሲሆን እንደ አምፖል፣ ብሬከር፣ ፓወር ሶኬት ወዘተ ያሉ በፖይንት ዋጋ የሚተመኑ ሲሆን እንደ ፓወር ኬብል፣ እንደ ፒቪሲ ኮንዲዩት ወዘት ያሉት ደግሞ በሜትር ዋጋ ይተመናሉ። ለመነሻ ያህል እነዚህን ካየን የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ወደሆነው የዋጋ ትመና እንሄዳለን ተከተሉን❗️
#ይቀጥላል---

#የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን❗️
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

         
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን❗️"
🔹🔸🔹
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹
#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
👏15👍63
#ክፍል-3

#የኤሌክትሪክ_ስራ_ዋጋ_እንዴት_እንተምናለን
👉አብዛኞቻችሁ የኤሌክትሪክ ዋጋ በፖይንት ስንት ነው የሚሰራ እያላችሁ በደፈናው በተደጋጋሚ ስጠይቁን ነበር #አጭር_መልስ
🚫#ሽሮ ሁሉም ቦታ ዋገዋ እኩል አይደልም። ምክንያቱም ዋገዋና ጥፍጥነዋ እንደምትሰራበት ቤት ስለሚወሰን ነው። ሽሮ የበላችሁበትን #ዝቅተኛና #ከፍተኛ ዋጋ እናንተ #አስተያየት መስጫው ላይ እንድታስቀምጡ ለወው❗️እርግጠኛ ነኝ በዝቅተኛውና ከፍተኛው ዋጋ መሀል የብር መጠን ከፍተኛ ልዩነት አለው።
ሌላ #ምሳሌ እንውሰድ
🚫#በየአይነት
ሁሉም ቤት የሚሸጥበት ዋጋ እኩል አይደለም። ምክንያት እንደ ቤቱ እና እንደ አይነቱ ብዛት ስለሚለያይ። አስታውስ 2 አይነት ወጥ ከለው እስከ 9 አይነትና ከዛ በላይ እስካለው ድረስ ሁሉም በየአይነት ተብለው ነው የሚሸጡት። የበየአይነቱንም ዝቅተኛና ከፍተኛ ዋጋ ለናንተ አስተያየት መስጫ ላይ እንድታስቀምጡት ተውኩት።
👉ወደ ዋናው ነጥብ ስመለስ የኤሌክትሪክ ስራውም ዋጋ ልክ እንደ ሽሮዋና እንደ በየአይነቱ ነው። ይልቁንስ #ለዋጋ_ትመና እጅግ ወሳኝ ወደሆኑት ነጥቦች እንግባ፡-

#ይቀጥላል----

#የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን❗️
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

         
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን❗️"
🔹🔸🔹
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹
#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
👍304👏4🔥1💔1
#የኤሌክትሪክ_ስራ_ዋጋ_እንዴት_እንተምናለን
=====================
#ክፍል-4

👉#ለዋጋ_ትመና እጅግ ወሳኝ ወደሆኑት ነጥቦች ስንግባ፡-

1. #አሁናዊ_የባለሙያ_ክፍያ
👉አንድ ግለሰብ/ደርጅት ሰፊ ሥራ ከያዘና ከዚህ በፊት ቋሚ ሰራተኞች ከሌሉት ወይም ተጨማሪ ሰራተኞች የሚያስፈልጉት ከሆነ  አሁናዊ የባለሙያ ዋጋ (የኤሌክትሪክ ባለሙያ እንደ አስፈላጊነቱ ደግሞ  ቆርቋሪ፣ የፅዳት ሰራተኛ ወዘተ )ማወቅና ሥራውን በምን ያህል ጊዜ ስንት ባለሙያ ይጨርሰዋል የሚለውን ካወቀና ጠቅላላ ወጪውን ማወቅ ከቻለ የሚያዋጣውን ዋጋ ለማስገባት ወይም ለመነጋገር አይቸገርም።
2. #የሥራው_ስፋትና_ግንባታው_ያለበት_ደረጃ
👉የስራው ስፋት ሲባል ግንባታው ላይ ያሉት የኤሌክትሪክ ስራዎች ምን ያህል ሰፊ ነውደንበኛችን በግንባታ ዘርፍ የተሰማራና ቀጣይነት ያላቸው ስራዎችን ሊያሰራኝ ይችላል ወይወዘተ የሚሉትን ነጥቦች ማየትና ሰፊና ቀጣይነት ያላቸው ስራዎችን የሚያሰራን ከሆነ ከብዛት ትርፍ ስለምናገኝና ደንበኛችንም አላስፈላጊ ወጪ ላለማስወጣት ከመደበኛው ስራ ዝቅ ያለ ክፍያ መጠየቅ ይኖርብናል።
👉ሌላኛው ግንባታው ተገንብቶ ካለቀ በኋላ ወይም የግንባታ ማፍጠኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም  ከሆነና በተከታታይ ሰርተን የምንወጣ ከሆነ አሁንም ከፍያችን ተመጣጣኝ መሆን አለበት። ነገር ግን ግንባታው ሲጀመር ጀምሮ የኤሌክትሪክ ስራው የሚጀመር ከሆነና በየመሀሉ የሚቆራረጥ ስራ ከሆነ የምናስከፍለው ክፍያ ከፍ ያለ ይሆናል።
3.#ፕሮጀክቱ_የሚገኝበት_ቦታ
👉ፕሮጀክቱ የሚገኝበት ቦታ ግምት ውስጥ ማስገባት ዋጋ ለመተመን እጅግ አስፈለጊ ነው።
👉የስራ ቦታው ልትራንስፖርት አመች ነው ወይከቢሮየ/ከመኖሪያ ቤቴ ምን ያህል ይርቃልለትራንስፖርት  ምን ያህል ያስወጣልአካባቢው የምግብና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች አሉት ወይአካባቢው ላይ ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች አሉ ወይወዘተ የሚሉትን መረጃወች ጥንቅቅ አድርጎ ማወቅ ትክክለኛውን ወጪ ለማወቅና ዋጋ ለመተመን እጅግ አስፈላጊ ነው። ትክክለኛ ወጪን አለማወቅ እከስራለሁ በሚል ስጋት የተጋነነ ክፍያ እንድንጠይቅ ወይም ወጫችን ትንሺ መስሎን አነስተኛ ክፍያ እንድንጠይቅ ያደርገናል።
4. #የፕሮጀክቱ_ቆይታ
👉የፕሮጀክቱ ቆይታ ስንል ሁልጊዜ እየተሰራ በስራው ስፋት ምክንያት የሚቆየውን ለማለት ሳይሆን በግንባታ እቃዎች አቅርቦት ችግር ምክንያት የሚከሰትን የፕሮጀክት መዘግየት ለመግለፅ ነው።
👉በዚህ ጊዜ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ የማያልቅና የእቃ አቅርቦት ችግር የሚኖር ከሆነ ዋጋ ስንዋዋል በወራት ወይም በአመት ገድበን መዋዋልና የዋጋ ማስተካከያ መጠየቅ አስፈላጊ ነው።
👉ብሮጀክቶ የእቃ አቅርቦት ካለበትና በተያዘለት ጊዜ የማያልቅ ከሆነ የሰራተኛ ከፍያ ፣ የትራንስፖርትና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ስለሚጨምሩ እሱን ታሳቢ አድርጎ የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
5. #የፕሮጀክቱ_ውስብስብነት
👉ህንፃው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት(Mixed used building)  የሚሰጥ ከሆነ አንዱ ፍሎር ከሌላኛው ስለሚለያይ እንደ አንድ አይነት አገልግሎ እንደሚሰጥ ወይም ተመሳሳይ ዲዛይን(Typical) እንዳለው ግንባታ ስራው ቀላል አይሆንም። በመረዳት ችሎታቸው ከፍ ያሉ ባለሙያዎችንም መቅጠር ያስፈልጋል። ስለዚህ ዲዛይናቸው የተለያየ ወይም ውስብስብ ያለ ከሆነ ክፍያው ከፍ ሊል ይችላል።
👉እንዲሁም የስላቡ አይነት ሶሊድ ወይም ሪብድ መሆኑም በተወሰነ ደረጃ የክፍያ ላውጥ እንዲኖር ያደርጋል።
7. #የዋጋ_ጥናት_ማድረግ
👉ምንም እንኳን ግለሰቦችም ይሁኑ ድርጅቶች የሚሰሩበት ዋጋ ከላይ ባየናቸው ነጥቦች ምክንያት ከፕሮጀክት ፕሮጀክት ቢለያዩም አማካይ የሆነውን ወይም #ዝቅተኛውንና #ከፍተኛውን ዋጋ ማወቅ የኛን ዋጋ ለማውጣትና ተወዳዳሪ ለመሆን ይረዳናል።
8.#ባለሙያው_ያለበት_የሙያ_ደረጃና #ኮንትራት_የያዛቸው_ፕሮጀክቶች_ብዛት
👉ዘርፉ ላይ ያልቆየና ሙያውን በሚፈለገው ልክ ያላዳበረ ባለሙያ ብዙ ስራዎችን እየሰራና የረጅም ጊዜ ልምድ ካለው ባለሙያ እኩል ዋጋ ላያስገባ ይችላል።
👉በቂ ልምድ የሌለው ወይም ብዙ ደንበኛ የሌለው ባለሙያ በቂ ልምድና ደንበኛ ለመያዝ ሲል ዋጋ ቀንሶ ሊገባ ይችላል። ስለዚህ ልምድ ያለውና ትልልቅ ስራዎችን ከሚሰራ ድርጅት እኩል ዋጋ መጠየቅ ወደ ስራ ለመግባት ሊያስቸግር ይችላል። ነገር ግን ደንበኛንም ያልተገባ ክፍያ መጠየቅ ፣ በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ጥራቱን ያልጠበቀ ስራ መስራትም አግባብነት የለውም።
👉አሰሪዎች አንዳንዶቹ የስራ ጥራት ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ብዙዎች ግን ዝቅተኛ ዋጋ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ስለዚህ በስራው ብዙ ያልገፈህ/ሽ ባለሙያ ከሆንክ/ከሆንሽ ምርጫህ/ሽ መሆን ያለበት ዝቅተኛ ዋጋ ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርጉትን አሰሪዎች ፈልጎ ማግኘት ነው።

#ማጠቃላያ፡-
👉ከላይ ለማየት እንደሞከርነው የኤሌክትሪክ ስራ ዋጋ ከላይ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ሌሎች ምክንያቶች ይለያያል። እንኳን አይደለም ከድርጅት ድርጅት/ከባለሙያ ባለሙያ አንድ ድርጅት ከሚሰራቸው ፕሮጀክት ፕሮጀክትም እንደሚለያይ ላማሳወቅ እወዳለሁ።
👉አሁን ላይ የሚሰራበት የፖይንት ዋጋ ከ180-400 ብር ባለው  መደብ ውስጥ ሲሆን ከዚህ በታችም በላይም የሚሰሩ እንደሚኖሩ ግልፅ ነው። ለሌሎችም ልምድ እንዲሆን  ሌሎቻችሁም  ስራ ላይ ያላችሁ የምሰሩበትን አማካይ ዋጋ ኮመንት ላይ ፃፉልን።
👉የሥራው መጠን አነስተኛ ከሆነ በፖይንት መሆኑ ቀርቶ ከላይ  እንደገለፅነው በፎርፌ ወይም በግምት ዋጋ ቢሆን ይመከራል።


#የYouTube_Channel እና #የቴሌግራም ቻናሎቻችን #Subscribe እያደረጉ #እውቀትዎን_ያሳድጉ❗️
#youtube
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

#Telegram
👇👇👇👇
         
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE2DpDe9fPGCTupqTg

#በአይነቱ ልዩ የሆነውን የተግባር ስልጠናችን #ለመሰልጠን እና ማንኛውም #የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ያገኙናል❗️
👇👇👇👇
0118644716
0991156969
0911585854

"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን❗️"
🔹🔸🔹
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹
#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
👍336👏2😱2🎉2
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ !!
👍14
Amen Institute of Technology Official®
#አስቸኳይ_የቅጥር_ማስታወቂያ ድርጅታችን አሜን የኤሌክትሪካል ሥራና  ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጥር ይፈልጋል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ጥር 07,2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ላይ የትምህርት ማስረጃ  ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ቦሌ ሚካኤል (ከሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ለቃለ መጠይቅ እንዲገኙ…
#የቃለ_መጠይቅ_ውጤት

ድርጅታችን አሜን ኤሌክትሪካል ሥራና ማሰልጠኛ ማዕከል ከዚህ በፊት በሬጅስራር የስራ መደብ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በቀን 07/05/2016 ዓ.ም ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ጠርቶ ቃለ-መጠይቅ ማድረጉ ያታወቃል። በዚህም መሰረት ከ1-4 የወጡ እጩ ተወዳዳሪዎችን ውጤት ለይተን የለጠፍን ሲሆን ስማችሁ የተጠቀሰ ተወዳዳሪዎች የቅጥር ውል የምፈፅሙበትን ቀን ስልክ ደውለን የምናሳውቃችሁ ሲሆን እስከዛ እራሳችሁን እንድታዘጋጁ እናሳስባለን።
👍131
#የድህረ_ክፍያ_ደንበኞች_የኤሌክትሪክ_ሃይል_ፍጆታ_የሚከፍሉበት_የጊዜ_ሰሌዳና በወቅቱ አለመክፈል የሚያስከትለው ችግር 
======================
👉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት(EEU) ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በአሁን ወቅት ከ 3.3 ሚሊዮን በላይ የድህረ ክፍያ(ከተጠቀሙ ባኋላ የሚከፍሉ) ተጠቃሚ ደንበኞች አሉት፡፡ ንባብ በተጠቀሰው ጊዜ ካለተወሰደ በተቀመጠልዎ የጊዜ  ሰሌዳ መክፈል ስለማይችሉ #ለተጠራቀመ_የፍጆታ_ሂሳብ#የአገልግሎት_ክፍያና የተቋረጠን የኃይል አቅርቦት መልሶ ለማገናኘት የሚወጣን ወጪ እንዲከፍሉ ከማስገደዱም በላይ #ለባለ_ነጠላ_ፌዝ_ቆጣሪ 500 ብር እና #ለባለ_ሶስት_ፌዝ_ቆጣሪ 1000 ብር ቅጣት ይዳርጋል፡፡
👉ስለዚህ  የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን በተቀመጠው የመክፈያ የጊዜ ሰሌዳ ቢከፍሉ ከነዚህ ካልተፈለጉ ወጭወችና እንግልት ይድናሉ።
👉የቆጣሪ ንባብ በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ ካልተወሰደ  በአቅራቢዎ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ በማሳወቅ ንባብ እንዲወሰድ በማድረግ ካላስፈላጊ ወጪ መዳን ይችላሉ፡፡
👉 የድህረ ክፍያ ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ንባብ የሚወሰድበትና የሚከፈልበት የጊዜ ሰሌዳ  እንደሚከተለው ቀርቧል።
↪️ቡድን1 ንባብ ከ14-19 ሲሆን ክፍያ ከ26-02
↪️ቡድን2 ንባብ ከ21-26 ሲሆን ክፍያ ከ3-9
↪️ቡድን3 ንባብ 28-3 ሲሆን ክፍያ 11-17
↪️ቡድን4 ንባብ ከ6-10 ሲሆን  ክፍያ 19-25
#youtube
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

🔹🔸🔹
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹
#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
👍232
#አስቸኳይ_ማስታወቂያ
================
👉ከዚህ በፊት በማሰልጠኛ ተቋማችን በህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሰልጥናችሁ አሁን ሰራ ላይ ያልሆናችሁ ወይም የስራ ትስስር ያልተፈጠረላችሁ ካላችሁ 6 ባለሙያዎችን የሚፈልግ ድርጅት ሰልጠየቀን #ሙሉ_ስማችሁንና_ስልክ_ቁጥራችሁን በዚህ ሊንክ እንድትልኩልን እናሳስባለን። አስቸኳይ ነው!
@electricexpert
👉 አስቸኳይ ስለሆነ እስከ 28/05/2016 8 ሰዐት ድረስ ብቻ ነው የምትልኩልን❗️
👍21
Amen Institute of Technology Official®
#አስቸኳይ_ማስታወቂያ ================ 👉ከዚህ በፊት በማሰልጠኛ ተቋማችን በህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሰልጥናችሁ አሁን ሰራ ላይ ያልሆናችሁ ወይም የስራ ትስስር ያልተፈጠረላችሁ ካላችሁ 6 ባለሙያዎችን የሚፈልግ ድርጅት ሰልጠየቀን #ሙሉ_ስማችሁንና_ስልክ_ቁጥራችሁን በዚህ ሊንክ እንድትልኩልን እናሳስባለን። አስቸኳይ ነው! @electricexpert 👉 አስቸኳይ ስለሆነ እስከ 28/05/2016…
ሰላም የአሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ድርጅታችን እስካሁን በተለያየ ዙሮች ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች መቀጠር የሚፈልጉትን ሁሉንም በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ያስቀጠረ ሲሆን
ትላንት በቀን 27/05/16 ባወጣነው የስራ ማስታወቂያ መሰረትና ለሌላ አንድ 3 ባለሙያ ለሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች ስማችሁ የተዝረዘረውን መረጃችሁን ያስተላለፍን ሲሆን ስልክ ስለሚደውሉላችሁ ስልካችሁን ክፍት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
👉ከነዚህ ከ9ኙ ስማቸው የተዘረዘሩት ውስጥ 8ቱ ከማሰልጠኛችን በተለያየ ጊዜ የሰለጠኑ ሲሆኑ አንድ ሰው ከሌላ ተቋም የሰለጠነ ሰው አካተናል። እንዲሁም ከ 8ቱ አብዛኞቹ ከዚህ በፊት የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ስራ ላይ የቆዩ ሲሆኑ አሁን ላይ በፕሮጀክት መጠናቀቅና በተለያዩ ምክንያቶች ስራ ላይ ያልሆኑትን ሲሆን 2 ሰወች ብቻ ከዚህ በፊት የስራ ዕድል ሳይፈጠርላቸው የቆዩ ናቸው።
👉በቀጣይ ሌሎች ቀጣሪ ድርጅቶች ሲመጡ ለቻናላችን ተከታዮች እድሉን የምንሰጥ ይሆናል።

1. NATINAEL SEIFU
2. Abenezer Abera
3. Getachew mandie
4. Samrawit Wondwesen
5. Abrham Tadele
6. Yibeltal Agumasie
7. Tarekegn Abebe
8. Henok endale
9. Hizbawi Sisay
መልካም የስራ ዘመን❗️❗️❗️
#youtube
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
👍20🎉2
2025/10/17 17:11:42
Back to Top
HTML Embed Code: