Telegram Web
መልካም የእናቶች ቀን!
To all the amazing mothers on this special day — WE LOVE YOU!
Happy Mother’s Day from SPHMMC!
#MothersDay
የጤና ሚኒስቴር ሪፎርምን በተመለከተ ኢቢሲ ከጤና ሚኒስትርዋ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ያደረገውን ቆይታ ዛሬ ምሽት 3፡00 ይተላለፋል። ተከታተሉ: :
KOICA Donates Medical Equipment to St. Paul’s Hospital Millennium Medical College
In a ceremony held last week, the Korea International Cooperation Agency (KOICA) Ethiopia office donated a range of advanced medical equipment to St. Paul’s Hospital Millennium Medical College.
The donated items include a bronchoscopy simulator, bronchoscopy monitor, spirometers, computers, printers, and other essential medical supplies. The support is aimed at strengthening the college’s capacity in medical education and lung health diagnostics, as well as establishing a dedicated bronchoscopy laboratory.
KOICA’s Country Director in Ethiopia, Mr. Han Deog Cho, officially handed over the equipment to the college's Provost, Dr. Sisay Sirgu. “KOICA is committed to supporting Ethiopia’s health system. This donation will enhance both the quality of education and healthcare services,” said Mr. Han.
Dr. Sisay Sirgu expressed his appreciation for the generous support, noting that it will significantly boost the college’s teaching and diagnostic capabilities in lung health. The donation was made possible through the initiative of Professor Yu Diok Jong.
SPHMMC Welcomes Third Cohort of PhD in Public Health Students
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) welcomed its third cohort of PhD in Public Health students with an orientation and induction program on May 12, 2025.
The event introduced five new doctoral candidates to the PhD program, covering curriculum structure, degree requirements, research opportunities, and funding options. Students were also briefed on essential administrative procedures, including registration, grading policies, and academic integrity.
This orientation marks an important milestone for the third cohort as they begin their rigorous academic and research journey, equipped with the knowledge and resources needed to address global public health challenges.
Graduate Nursing Class Completes Team Training Program at Kolfe and Felege Melese Health Centers

The Graduate Class of Post-Basic Nursing, representing five specialty areas, has successfully concluded their five-week Team Training Program (TTP) at Kolfe Health Center and Felege Melese Health Center in Addis Ababa. During their field placement, students actively engaged in a range of impactful community-based initiatives. These included the renovation of public latrines, the delivery of health education on chronic and communicable diseases, waste disposal, and capacity-building efforts within the health centers, among others.

Additionally, in collaboration with the nursing staff of the college, students provided essential training on Neonatal Resuscitation for health center staff and First Aid to Health Extension workers, further strengthening local service delivery. Their work exemplified the college's ongoing commitment to developing compassionate, community-oriented professionals capable of mobilizing local resources for the public good.

The symposium celebrating their work featured student presentations on their experiences, challenges, and accomplishments, underscoring the power of applied learning. The gathering also acknowledged essential collaborators—local health offices and community members—for their invaluable assistance, expressing a common vision for meaningful, collaborative education.

This initiative highlights the importance of practical training in nursing education and its positive impact on community health outcomes.
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በተቋሙ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን አመሰገነ.።
ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ ተገቢውን አገልግሎት በተመላላሽ ህክምና ድንገተኛ እንዲሁም በአስተኝቶ ማከም ሕክምና የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን ሳይስተጓጎል አየሠጡ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ኮሌጁ አመሠግኗል::
የኮሌጁ ባለሙያዎች ቃላቸውን ጠብቀው ተጨማሪ የስራ ጫናን ወስደው እየሠሩ ያሉ የጤና ባለሞያዎችን ምሥጋና ተችሯቸዋል: :
በዛሬው እለትም በተመላላሽ ህክምና ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሚደርሱ ተገልጋዮች በተቋማችን ተገልግለዋል: :
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
ኮሌጃችን በሚከተሉት የሥራ መደቦች :መሥፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል: :
በትምህርትና በሥራ ላይ ባልተገኙ ኢንተርን(የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች) ላይ የኮሌጁ ሴኔት ውሳኔ አሳልፏል: :( ሙሉ የውሳኔው መግለጫ ተያይዟል)
በትምህርትና በሥራ ላይ ባልተገኙ ሪዝደንቶች ላይ የኮሌጁ ሴኔት ውሳኔ አሳልፏል: :( ሙሉ የውሳኔው መግለጫ ተያይዟል)
በሥራ ማቆም አድማ የተሠተፉ ባለሙያዎች በተመለከተ ኮሌጁ ያሳለፈው መግለጫ የሚከተለው ነው::( ተያይዟል)
ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 17/2017 ዓ.ም
#Mpox
ኤም ፖክስ
#MPox
____

ምንነቱ! አጠቃላይ እውነታዎች!

ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡

የበሽታው ታሪካዊ ዳራ

የኤም ፖክስ ቫይረስ በዴንማርክ (1958) በዝንጀሮዎች ውስጥ የተገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ላይ የተገኘው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነው፡፡ በቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዘው የዘጠኝ ወር ህጻን ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1980 የፈንጣጣ በሽታን ማጥፋት እና የፈንጣጣ ክትባት በአለም አቀፍ ደረጃ ማብቃቱን ተከትሎ ኤም ፖክስ በመካከለኛው፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ያለማቋረጥ ብቅ እያለ ይገኛል። በ2022-2023 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ተከስቷል። እንደ ሽኮኮዎች እና ጦጣዎች ያሉ የተለያዩ ትናንሽ አጥቢ እንስሳት ለበሽታው የተጋለጡ ናቸው፡፡

ከ1970 በኋላ የኤም ፖክስ በሽታ በመካከለኛው እና ምስራቅ አፍሪካ (ክላድ I) እና በምዕራብ አፍሪካ (ክላድ II) አልፎ አልፎ ተከስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2003 በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተከሰተው ወረርሽኝ ከውጭ ከሚገቡ የዱር እንስሳት (ክላድ II) ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ከ2005 ጀምሮ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የተጠረጠሩ ህሙማን ሪፖርት ይደረጋሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2017፣ የኤም ፖክስ በሽታ በናይጄሪያ እንደገና ብቅ አለ እና በመላ አገሪቱ እና ወደ ሌሎች መዳረሻዎች በሚጓዙ ሰዎች መካከል ተስፋፍቷል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በ Clade I MPXV ምክንያት የኤም ፖክስ ወረርሽኝ በሱዳን ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ተከስቷል፡፡

የበሽታው ምልክቶች

ኤም ፖክስ በሽታ ቫይረሱ ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያለው ሰው የሚከተሉት ምልክቶች በሚታዩበት ወቅት ማለትም ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የእጢ እብጠት፣ የቆዳ ቁስለትና ድካም፣ የጡንቻና የጀርባ ህመም ሲያስተውል በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን የምርመራና ህክምና አገልግሎት ማግኘት ይኖርበታል።

መከላከያ መንገዶች

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ባሉባቸው ታማሚዎች አካባቢ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም፥ የኤም ፖክስ መሰል ሽፍታ የሚታይባቸው ሰዎች ጋር ባለመነካካት እና ታማሚዎቹ የተጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና መኝታ በአግባቡ ሳያጸዱ ባለመጠቀም፣ የግል እና የእጅ ንፅህና በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል።

በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በሚገኝበት ጊዜ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት እንዲያደርግ ወይም በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
2025/05/28 20:37:56
Back to Top
HTML Embed Code: