Telegram Web
BREAKING G12‼️

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ክልል መረጋጋት እስኪፈጠር እና የኢንተርኔት አገልግሎት እስኪመለስ ይቆያል‼️

ሆኖም በሌሎች አካባቢዎች ያላችሁ ተማሪዎች ዝግጅታቹን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን::

ከዚህ ቻናል በተጨማሪ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃዎች ብቻ የሚለቀቅበትን የ #ልዩ_መረጃ ቻናል ይቀላቀሉ👇
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAEyYjxSHWM66afKljA


@Ethiostudente @Ethiostudente
Forwarded from Sasi G/eyesus
Forwarded from Sasi G/eyesus
👏👏😂
የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የመፈተኛ ቀን በዚህ ሳምንት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል‼️

🎲 በትግራይ ክልል መረጋጋት እስኪፈጠር እና የኢንተርኔት አገልግሎት እስኪመለስ ይቆያል የተባለው የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሁን ሁሉም ክልል ባለው ፀጥታ እና የሰፈነ ሰላም ምክንያት በቅርቡ ይፋ ሲደረግ እኛም መረጃው እንደደረሰን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።

https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFjmHytEWWbWoq3PAQ
@ethiostudente
የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ ሸገር ኤፍኤም የትምህርት ሚንስቴር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን ጠይቆ ተከታዩን መልስ አግኝቷል።‼️

⁉️ ህግ የማስከበሩ ስራ መጠናቀቁ ተነግሯል እና ስለ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ምን አዲስ ነገር አለ

🎲 የ12ኛ ክፍልን በተመለከተ ህግ የማስከበሩ ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም ፣ ሌሎች የሚሰሩ ስራዎች አሉ፣ ፈተናው በቴክኖሎጂ የታገዘ ስለሆነ ብዙ ግብአቶች ከውጪ እየገቡ ይገኛሉ።

🎲 ፈተናው የሚሰጠው እነዚህ ግብአቶች ተጠናቀው ሲገቡ እና ፈተናውን የሚያስተዳድሩ አካላት ሰልጥነው እንዲሁም ተማሪዎችም ከቴክኖሎጂው ጋር ተዋውቀው መሆኑን ገልፀዋል።

🎲 ታህሳስ መጨረሻ ሳምንት ድረስ ግብአቶቹ ከውጪ ተጓጉዘው ይጠናቀቃሉ ተብሎ ያታሰባል ያሉ ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበትን ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልገለፁም።

⁉️ ፈተናው በትግራይ ክልል ያሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማካካሻ ት/ት እስኪሰጣቸው ይጠበቃል ወይ

🎲ችግሮች ሲያጋጥሙ የግድ ሁሉንም አንድ ላይ ለመፈተን አንገደድም። የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እስክንጨርስ በትግራይ ፈተናውን ለመስጠት ወደ ሚያስችል ሁኔታ ካልተቀየረ ሌሎች አማራጭ ፈተናዎች ስላሉ እነሱን የምንሰጥ ይሆናል።

https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFjmHytEWWbWoq3PAQ
@ethiostudente
ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ‼️

🎲 በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጿል።

🎲ሚኒስቴሩ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።

🎲 የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

🎲 መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ እንደሆኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ 450 ሺህ ታብሌቶች ደግሞ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አብዛኛዎቻቹ በቴሌቪዥን የምታውቁት መረጃ ቲቪ በቴሌግራም መጣ ይቀላቀሉ👇👇👇

https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAEsS4Bd8ZcRsgI8dZg
@Mereeja_Tv @Mereeja_Tv

@ethiostudente @ethiostudente
የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከጥር 27 እሰከ 30 ድረስ በOnline እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

¤ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

¤ ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

¤ ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል። ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

¤ 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

¤ በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

Share and Support Us.
@Ethio_Students
@Ethio_Students
ለ 12 ክፍል ተፈታኞች ‼️
#FakeNewsAlert

👉 የ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከጥር 27 ጀምሮ ይሰጣል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት ነው።

👉 ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ ለፈተና የሚሆኑ እቃዎችን እስከ ታህሳስ 30 ድረስ አዘጋጅተን እንጨርሳለን ብሏል። የፈተናውም ቀን የሚወሰነው ከዛን ቡሃላ ነው።

🔥 ተማሪዎች ያለምንም መዘናጋት ማንበብ ይኖርባችኃዋል።

ለተማሪዎች ያጋሩ🕹

◉⇲ @STUDENT_PAGE ⇲◉
◉⇲ @STUDENT_PAGE ⇲◉
የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀዋል።

በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

Share and Support Us.
@Ethio_Students
@Ethio_Students
This is my new account
እንኳን ፡ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ፡፡🎄🎄🎄🎄 #አመታትን አቀናጅቶ በየእለቱ አዲስ ነገርን የሚሰጠን እግዚአብሄር ስም ብሩክ ይሁን፡፡🌿🌿🌿🌿🌿🌿🎄🎄🎄🎄🙏🙏🙏🙏#ህፃን ተወልዶልናልና ወንድልጅ ተሰቶናልና ፣አለቅነቱም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ፣መካር ሀያል አምላክ የዘላለም አባት #የሰላም አለቃ፣ተብሎ ይጠራል #በዳዊት ከተማ ተወልዶ ያየነው እርሱ የአለም መድሀኒት የሰላም አለቃ የዘላለም አባትነው፡፡ እንኳን ተወለደልን መድሀኒታችን
🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄
🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄🌿🎄
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የዛሬ ወር ገደማ ይሰጣል!

ለሚሰጠውም ፈተና ተበሎ 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

ትክክለኛ መፈተኛ ቀን በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቀኑም መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER
#Grade12NationalExam

በዘንድሮ አመት በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

ይህንን በተመለከተ ብዙ ቤተሰቦቻችን መረጃ እንድናደርሳቸው ጠይቀውናል። እስካሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

* ተጨማሪና የተሟላ መረጃ ስናገኝ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

TIKVAH-ETH
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ፥ "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ ታብሌቶች ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እንዳስረዱ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2025/07/06 03:29:50
Back to Top
HTML Embed Code: