Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1508 - Telegram Web
Telegram Web
#RemedialExam

የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) በቀን መጋቢት 15/2017 ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል እንደሚሆን አስታውሰዋል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዚህ በፊት 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ይወስዱ የነበረ ሲሆን፤ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% ከማዕከል እንዲሰጥ በጥቅምት 2017 ዓ.ም መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህም የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም የሚሰጥ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ከዛም በማዕከል በሚሰጥ ፈተና የተማሪዎቹ መቀጠል እና አለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡፡
👍3
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ ሆነ
****

ከሰኔ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡ ተገልጿል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚመቻችም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝና ከከፍተኛ ትምህርት መረጃ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘት እና የሚሰጡ ሀገር ሀቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
👍102
learnethiopia.com.pdf
556.8 KB
for university, private collage, secondary school student only
👍2
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከሚያዚያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ሁሉም ተፈታኝ ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል፣ የመለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እና የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትሔዱ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) መያዝ ስለሚኖርባችሁ Print አድርጋችሁ መያዝ ያስፈልጋል።

ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ከመሔዳችሁ በፊት በጤና ሚኒስቴር የተለቀቀውን የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያ መመልከት ይኖርባችኋል። ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
👍13
Indet qoyachu
Zare 10:30 lay kenantega meweyayet silemifelg live lay inditigegu. From Biniam
👍151
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ
👍103
2025/10/17 18:20:22
Back to Top
HTML Embed Code: