Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
#MoE #AAU #ExitExam

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሰኞ ይፋ ባደረገው የተሻሻለ የአካዳሚክ ካላንደር በሰኔ ወር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

ተማሪዎቹንም ሰኔ 21 እንደሚያስመርቅ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ ስም ይፋ ተደርጎ የተሰራጨውን የአካዳሚክ ካላንደር ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር ማረጋገጥ ችሏል። አንድ የተቋሙ አመራር " ከመጨረሻው ሐምሌ 2 ከሚለው ውጪ ሁሉም ትክክል ነው። የመጨረሻው ሐምሌ 8 ነው የሚሆነው " ብለዋል።

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ይፋ ባደረገው ካላንደር የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ቢጠቁምም ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ስለ ፈተናው ቀን በይፋ ያሳወቀው ቀን የለም።

በሌላ በኩል የመውጫ ፈተና በድጋሜ የሚፈተኑ ተፈታኞች  በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገምን እንገኛለን " ሲል ገልጿል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱም አመልክቷል።

ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

እስካሁን ድረስ ምዝገባ ያልፈጸሙ ተማሪዎች የመመዝገቢያው አድራሻ / ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በአግባቡ እየሰራላቸው እንዳልሆነ በጠቆም የምዝገባ ጊዜው እንዲራዘም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ገምግሞ ይፋ የሚያደርገው አዲስ ነገር ካለ የምንከታተለው ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪ ደሞ " በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታቸው ተሰርዟል " የተባሉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ አለባቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


source: tikvahethiopia
👍93
በድጋሜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ጊዜ አለመራዘሙን #ቲክቫህ ዩንቨርስቲ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጋርቷል👇


አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገመ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

በቀሩት ሰዓታት ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et

Note:
በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታችሁ የተሰረዘባችሁ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች፤ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ የምትችሉ መሆኑ በሚኒስቴሩ መገለፁ ይታወሳል፡፡
👍71😁1
#MoE
#ተራዝሟል

በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በድጋሜ ተፈታኝ አመልካቾች ምዝገባ እስከ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በመሆኑም ዳግም ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ቀነ ገደብ ውስጥ እንድታጠናቅቁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et

የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ የግድ ነው፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የቪዲዮ ቲቶሪያል ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=C9KkQ9AHd2o

Source: tikvahuniversity
👍4
#መውጫ ፈተና #ተፈታኞች በሙሉ፡-

ስለ ሀገራዊ ድጂታል መታወቂያ (National Digital ID card) ይመለከታል፡፡

#NationalIDEthiopia  *9779# በመደወል ማግኘት ይችላሉ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መደረጉ ይታወቃል። 

ዕጩ ተመራቂዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አስፈላጊ የፋይዳ አገልግሎቶች፦

➫ የፋይዳ ቁጥር ከጠፋባችሁ ወይም ካልደረሳችሁ *9779# በመደወል በድጋሚ ማስላክ ትችላላችሁ።

➫ በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን ለማደስ በ National ID Ethiopia ድረ-ገፅ
id.gov.et/update ላይ በመግባት ወይም የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ላይ በመግባት በቀላሉ ማደስ ትችላላችሁ።
👍41
#ExitExam

" ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስከ አሁን ያልተመዘገቡ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህ በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም https://exam.ethernet.edu.et በኩል ገብተው ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ብሏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል መመዝገባቸውን እንዲያረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ፈተናው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

ለፈተናው የሚያመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ሊኖራቸው እንደሚገባና ፤ ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቦኋላ ምዝገባ እንደማያስተናግድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

Source: tikvahethiopia
👍74
#TVTI
#ExitExamRegistration

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዋና ግቢ እና በሥሩ በሚገኙ የሳተላይት ተቋማት በ2017 ዓ.ም ለምትመረቁ የመደበኛ እና የተከታታይ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015፣ 2016 እና በ2017 (1ኛ ሴሚስተር) የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 09-17/2017 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦

➫ በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር ለምትጨርሱ መደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች ምዝገባው በምትማሩበት ግቢ በየትምህርት ክፍላችሁ ይሆናል፡፡

➫ በሳተላይት ተቋማት ለምትጨርሱ መደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች በሳተላይት አስተባባሪዎች አማካኝነት በየሳተላይቱ ይሆናል፡፡

➫ በ2015፣ 2016 እና በ2017 አንደኛ ሴሚስተር በተሰጠው የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በዋናው ግቢ ICT ትምህርት ክፍል ህንጻ 2 አንደኛ ፎቅ ይሆናል፡፡ በአቅራቢያው የሳተላይት ተቋም ያለ ተፈታኝ በሳተላይት ተቋሙ መመዝገብ ይችላል፡፡
ይመዝገቡ!

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ምዝገባ ነገ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል፡፡

እስካሁን ያልተመዘገባችሁ የድጋሚ ተፈታኞች (Re-sitters) በመመዝገቢያ ፕላትፎርሙ (https://exam.ethernet.edu.et) ገብታችሁ ምዝገባችሁን በቀሩት ሰዓታት አድርጉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የምትቀመጡ ተፈታኞች በተቋሞቻችሁ በኩል መመዝገባችሁን እንድታረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴሩ ማሳሰቡ ይታወቃል።

የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 02-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ለፈተናው የምታመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የፋይዳ መታወቂያ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
👍52
#RemedialExam

የሪሚዲያል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

በዚህም ተማሪዎቹ ለኦንላይን ፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና በበይነመረብ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በኮምቦልቻ እና በደሴ ግቢ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ከ2000 በላይ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና በበይነመረብ መስጠት ጀምሯል።
👍64
Indet qoyachu zare 9:30 lay live meeting yineorenal ena hulachum bitigebu dess yilegnal
Melkam gize
learnethiopia.com
👍113👏2
2025/10/15 14:26:46
Back to Top
HTML Embed Code: