Telegram Web
ሶደቃ
---
ታላቁ ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
ሶደቃ፣ በላእ በመመለስ፣ አይነናስን በመመለስና የምቀኛን ተንኮል በመመለስ ረገድ የሚደንቅ የሆነ ተፅእኖ አላት!!።” [በዳኢዕ አል'ፈዋኢድ 2/234]

#join ⤵️ ቴሌግራም
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
👉  በውጭም በሀገርም ላሉ ሰለፍዮች

    አላህ ካለ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 25/2017 ለሀራ ሰለፍዮች ሀገር አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ የሀገራችን ሰለፍይ መሻኢኾች አደራ ብለዋል ። በመሆኑም በዚሁ እለት ለሀራ ሰለፍዮች የቦታ ግዢና የመስጂድ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይኖራል ።
     አላህ ካለ በዚህ ፕሮግራም ላይ ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያሉ መሻኢኾች የሚሳተፉ ይሆናል ። የተለመደው አይነት ተራ ፕሮግራም ሳይሆን በአይነቱ ለየት ያለ ለመላው የሀገራችን ሰለፍዮች የሀራ ወንድሞቻችን ላቀረቡት ከጎናችን ሁኑ አንገታችንን ቀና እንድናደርግ አድርጉን ለሚለው ጥሪ ምላሽ የሚሰጥበትና በወሎ ምድር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሸይኽን አስሮ ደረሶችን የማባረር ጥቁር ታሪክ ፍቀን ሌላ ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ። ታዲያ ውድ የሀገራችን ሰለፍዮች በሙሉ በየሰፈራችንና መንደራችን ያሉትን ፕሮግራሞች ለአንድ ሳምንት ቆም አድርገን በዚህ ታሪካዊ የሰለፍዮች ርብርብ አሻራችንን ለማኖርና የሸይኻችንን የተሰበረ ቅስም ለመጠገን የምንችለውን እናድርግ ።
    በሚያልፍ ቀን የማያልፍ ታሪክ ሰርተን ሀራ ላይ የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት ወደ አስደሳች ታሪክ በመቀየር የተባረሩ ደረሶች እንዲመለሱ እናድርግ ። ወኔና ፍላጎት ከሌለ ገንዘብ ምንም አይሰራም ። ፍላጎት ካለ ተባብሮ የማይሰራ ነገር የለምና ከልባችን እንነሳ ።
https//
www.tgoop.com/haraselefi
ታላቅ ብስራት!!
—— ተክቢር እና ላ! ኢላሀ ኢለላህ ለሚል ሰው
———
አምላካችን አላህን (ጥራት ይገባውና) በሚገባ ልናልቀው ይገባል!!። በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏልና:-

﴿…ِّ وَكَبِّرهُ تَكبيرًا

አላህን ማላቅንም አልቁት።” አል-ኢስራእ 111

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪ (ረሂመሁላህ) ይህን የቁርኣን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:- “አላህ፣ አንተ ሙሀመድ ሆይ! ጌታህን እንድታልቀው ባዘዘህ ነገርም ሆነ በከለከለህ ነገር ላይ በተግባርም ሆነ በንግግር አልቀው!፣ ብሏል።” አሉ፣ [ጃሚዕ አልበያን… 9/179]

ታላቁ ዓሊም ሙሀመድ አሚን አሽ-ሺንቂጢይ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል:- “እጅግ በጣም ጠንካራ የሆነ ማላቅን አልቀው ማለት ነው፣ አላህን ማላቅ እውን የሚሆነው ደግሞ አላህ ያዘዘውን በጥብቅ በመታዘዝና የከለከለውን በመከልከል፣ እንዲሁም ወደሚወደው ነገር ሁሉ በመሽቀዳደም ነው!።” [አድዋኡል በያን… 3/635]

ብስራት ተክቢርና ተህሊል ላለ ሰው!!

ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድም ላ! ኢላሀ ኢለላህ የሚል ሰው (ይህን ቃል) አይለውም ቢበሰር እንጂ፣ አንድም  ተክቢር የሚል ሰው ተክቢር አይልም ቢበሰር እንጂ።” የአላህ መልእክተኛ ሆይ በጀነት ነው ሚበሰረው? ተባሉ፣ “አዎን” አሉ። [አልባኒ ሲልሲለቱ አስ-ሶሂሃ 1621 ላይ ሀሰን ብለውታል።]

ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድም ላ! ኢላሀ ኢለላህ የሚል ሰው (ይህን ቃል) አይለውም ቢበሰር እንጂ፣ አንድም  ተክቢር የሚል ሰው ተክቢር አይልም በጀነት ቢበሰር እንጂ።” [ሶሂሁ'ል ጃሚዕ 5569]

ታላቁ ዓሊም ሙሀመድ ቢን ኢስማኢል አስ-ሶንዓኒይ (ረሂመሁላህ) ይህን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ አሉ:- "ተክቢርና ላ! ኢላህ ኢለላህ ማለቱ በሐጅ ወቅትም ሊሆን ያመቻል ከሐጅ ውጭም ሊሆን ያመቻል።

በጀነት ይበሰራል፣ የተባለው:- ተክቢርና ላ! ኢላሀ ኢለላህ በማለቱ የቂያማ ቀን መላኢካዎች በጀነት ያበስሩታል ማለት ሲሆን ይህን ዜና በመንገር ደግሞ መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህን ያለን ሰው በመልካም ነገር አብስረዋል።" [አት-ተንዊር ሸርህ ጃሚዕ አስ-ሶጊር 9/364]
ተክቢርና ተህሊል፣ ላ! ኢላሀ ኢለላህ ማለት ላይ እንበርታ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: (www.tgoop.com/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
ሱና እንደ ኑህ መርከብ ናት!!
———
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:-
ቢድዓ ሰዎችን ከትናንሽ (ወንጀል) ወደ ከባባድ (ወንጀል) ከማውጣት አትወገድም፣ ወደ አፈንጋጭነትና ኒፋቅ እስክታደርሰው ድረስ። ሱና እንደ ኑህ መርከብ ምሳሌ ናት፣ የተሳፈረባት ድኗል፣ (ሱናንም የተከተላት ድኗል) ከርሷ የተቃረነ ሰው ሰምጧል፣ (ሱናንም የተቃረነ ልክ እንደዛው ነው።)
ዙህሪይ - ረሂመሁላህ - እንዲህ አለ:- ከቀደምቶቻችን ያለፉ ሊቃውንቶች እንዲህ ይሉ ነበር:- “
በሱንና መጣበቅ መዳን ነው።
[ምንጭ:- መጅሙዕ አልፈታዋ 22/306]
ኢብን ሽፋ…✍🏻
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
👉  በውጭም በሀገርም ላሉ ሰለፍዮች

    አላህ ካለ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 25/2017 ለሀራ ሰለፍዮች ሀገር አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ የሀገራችን ሰለፍይ መሻኢኾች አደራ ብለዋል ። በመሆኑም በዚሁ እለት ለሀራ ሰለፍዮች የቦታ ግዢና የመስጂድ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይኖራል ።
     አላህ ካለ በዚህ ፕሮግራም ላይ ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያሉ መሻኢኾች የሚሳተፉ ይሆናል ። የተለመደው አይነት ተራ ፕሮግራም ሳይሆን በአይነቱ ለየት ያለ ለመላው የሀገራችን ሰለፍዮች የሀራ ወንድሞቻችን ላቀረቡት ከጎናችን ሁኑ አንገታችንን ቀና እንድናደርግ አድርጉን ለሚለው ጥሪ ምላሽ የሚሰጥበትና በወሎ ምድር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሸይኽን አስሮ ደረሶችን የማባረር ጥቁር ታሪክ ፍቀን ሌላ ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ። ታዲያ ውድ የሀገራችን ሰለፍዮች በሙሉ በየሰፈራችንና መንደራችን ያሉትን ፕሮግራሞች ለአንድ ሳምንት ቆም አድርገን በዚህ ታሪካዊ የሰለፍዮች ርብርብ አሻራችንን ለማኖርና የሸይኻችንን የተሰበረ ቅስም ለመጠገን የምንችለውን እናድርግ ።
    በሚያልፍ ቀን የማያልፍ ታሪክ ሰርተን ሀራ ላይ የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት ወደ አስደሳች ታሪክ በመቀየር የተባረሩ ደረሶች እንዲመለሱ እናድርግ ። ወኔና ፍላጎት ከሌለ ገንዘብ ምንም አይሰራም ። ፍላጎት ካለ ተባብሮ የማይሰራ ነገር የለምና ከልባችን እንነሳ ።

https//
www.tgoop.com/haraselefi
የኢኽላስ አንገብጋቢነትና የሺርክ አስከፊነት!!
ኡስታዝ ሙሀመድ ሰልማን (ሀፊዘሁላህ)
አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- የኢኽላስ አንገብጋቢነትና የሺርክ አስከፊነት!!

🎙በኡስታዝ ሙሀመድ ሰልማን (ሀፊዘሁላህ)

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/DarASSunnah1444
https://www.tgoop.com/DarASSunnah1444
Audio
የዑዱህያ እርድ ያለው ቱርፋትና በረካት በአራጁ ላይ  ወሳኝ ወቅታውይ ነጥብ ተወስቶበታ

ርዕስ"
ለዑዱህያ የማይታረዱ እንስሳቶች ምን አይነት ናቸው

1.አንድ አይኗ መጥፋቱ ግልፅ የሆና ወይም የሆነች
2.እግሯ  አንካሳና ሰባራ  ያልሆነች ወይም ያልሆነ
3.ከመክሳቷ የተነሳ ስብ ነገር የማይታይበት ወይም ስብ የለለው
4.እርጅናዋ ግልፅ የሆነች ወይም የሆነ ለኡዱህያ እርድ እንደማይሆኑ ተወስቷል ተ

➮የቀንድ መሰበርና የጆሮ መቆረጥ እንደሁም መተልተል የሚለውም ተነስቷል

🎤 በሸይኽ ሙሐመድ ሀያት
{ሀፊዘሁሏህ}
➴➴➴

@SheikMohmmedHyatHara
@SheikMohmmedHyatHara
Audio
የዑዱህያ እርድ ያለው ቱርፋትና በረካት በአራጁ ላይ  ወሳኝ ወቅታውይ ነጥብ

ጥያቄናመልስ

1.ጥያቄ አንድ ሰው የኡዶህያ እርድ ለቤተሰብ አንድ ፍየል ነው ወይስ የግድ መጨመር ይኖርበታል
2.ኡዱህያ ለማረድ የሚገብት እንሳዎች ሴት ወይስ ወንድ ነው መታረድ ያለበት
3.ለኡዱህያ የሚታረዱበት ቦታ የትና መቸ በምን ሰአት ነው

🎤 በሸይኽ ሙሐመድ ሀያት
{ሀፊዘሁሏህ}
➴➴➴
@SheikMohmmedHyatHara
@SheikMohmmedHyatHara
ለዒድ አል-አድሃ በዓል የሀገር ቤት ጉዞ
—————ክፍል 1
ለሙስሊሞች መደሰቻ ሁለት ታላላቅ በዓላትንና የጁምዓ እለትን ለደነገገው ለዓለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!!። እንደሚታወቀው ከነዚህ ውጪ ሌላ በሸሪዓ የተደነገገ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ያለው ኢስላማዊ በዓል የሚባል ነገር የለም!!። እነዚህ በዓላትም መለኮታዊና ከአምልኮ የተያያዙ ናቸው።

በዚህ በተከበረው የዚል-ሒጃ ወር አቅማቸው የፈቀደላቸው ሰዎች፣ የጉዞውን ጣጣ የቻሉ ሰዎች የተከበረውንና መጎብኘቱ ግዴታ የሆነውን ብሎም መጎብኘቱ ከአምስቱ የእስልምና ማእዘናት የሆነውን የአላህን ቤት ለመጎብኘት የሚጓዙት በርካቶች ናቸው።

ይህን ያልቻሉ ደግሞ ቤተሰባቸው የተለያየ ክ/ሀገራትና ገጠር ያሉ ወገኖች ከቤተሰባቸው ለማሳለፍ ወደተለያዩ ክ/ሀገር ከተሞችና ገጠር ይጓዛሉ። ይህ ጉዞ አላህን ማመፅ ካልተቀላቀለበትና እስከ ፍፃሜው አላህን መታዘዝ ከሆነ ምንኛ ያማረ ጉዞ ነው!።

ይህ ጉዞ ለመልካም ነገርና ለቤተሰብ ዚያራ በመሆኑ የሚያስደስትና እጅግ የሚወደድ ቢሆንም፣ ተጓዦች አላህ (ይጠብቀንና) አላህን አያምፁበትም ፍፁም የሆነ ጉዞ ነው ማለት ግን አይደለም። በመሆኑም ተጓዦች ከእነዚህ አላህን በእጅጉ ከሚያስቆጡ ስህተቶች እንዲቆጠቡ ማስታወሱ ግድ ነው።

» እንዲያውም ገና ጉዞው ሲጀመር በተከበረው ዘጠነኛው ቀን፣ ያንን (የዚል-ሂጃ 9ኛ) ቀን መፆሙ ያለፈውንና የሚቀጥለውን ዓመት ወንጀል ያስምራል በተባለው የተከበረ ታላቅ ቀን፣ አላህ ሀራም ያደረገውን የከበደ ወንጀል አደንዛዥ እፅ የሆነውን ጫት እየበላ የሚጓዘው ህዝብ ከተጓዦች አብዘሃኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም!። ጥቂት አላህ ያዘነላቸው ባሪያዎቹ ሲቀሩ አብዘሃኛው ተጓዥ ይህን አደገኛና አላህ ሀራም ያደረገውን አደንዛዥ እፅ እየበላ መጓዝ የተለመደ እየሆነ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ ጫትን ለማይቅሙትና የዲን እውቀት ላላቸው ለጥቂቶች አንድ መልእክት አለኝ:- (ከሚቅሙ ሰዎች ጋር ተቀላቅላችሁ የምትሔዱ ካላችሁ በራሳችሁ ላይ አንድ ግዴታ ነገር ጥላችኋል፣ እሱም:- የተወገዘን ነገር ማውገዝ ነው!። አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ሲተገበር ዝም ካላችሁ እንደ ዲዳ ሸይጧን መሆናችሁን አትዘንጉ!፣ ማውገዝ ወይም መከልከልና ደዕዋ ማድረግ ካልቻላችሁ ጫት ከማይቅሙና ዘፈን ከማይከፍቱ ከቢጤዎቻችሁ ነው መሄድ ያለባችሁ።)

ታዲያ በጥቅሉ ጫትን በየተኛውም ጊዜ የምትቅሙ ሰዎች አላህን ልትፈሩ ይገባል!! ምንም ጥቅም የሌለውን አካልን የሚጎዳ፣ ገንዘብን የሚያባክን፣ አደንዛዥ የሆነን ነገር ሸሪዓችን እርም አድርጓል።

↪️ ጫት አካልን ጎጂ መሆኑን ታምኑበታላችሁ! እራስን የሚጎዳ ነገር መጠቀም ደግሞ አላህ ሀራም አድርጓል!!

↪️ ጫት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ገንዘብን እንደሚያባክን ታውቃላችሁ!!
አባካኞች የሸይጧን ጓዶች መሆናቸውን ደግሞ አላህ በቁርኣኑ ተናግሯል።

↪️ ጫት አዕምሮን እንደሚቀይር ታምናላችሁ! አዕምሮን የሚቀይር ነገር ደግሞ ከአስካሪ መጠጥ ነው።
አስካሪ መጠጥ በእስልምና ሀራምነቱ ደግሞ እንኳን ለሙስሊሞች ለከሀዲውም ግልፅ ነው!!

እነዚህን ጥቂት ጫትን ሀራም የሚያደርጉ ነጥቦች አብዘሃኛው ጫት ቃሚ "ለእውነት ሲባል" ብሎ ያመነባቸውና የጤና ባለ ሞያዎች ያረጋገጡት እውነተኛ ጫት የሚያስከትላቸው አደጋዎች እንጂ ከራሴ የሆኑ ፈጠራዎች አይደሉም!።

ከላይ ለጠቀስኳቸው ነገሮች ማስረጃን ያልጠቀስኩት ከምንም በላይ ማስረጃው ግልፅና የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ፅሁፉ እንዳይረዝም ብዬ ነው።

➡️ ከዚህ ጉዞ ሌላው ጥፋትና ከባድ ወንጀል ዘፈን፣ ነሺዳና መንዙማ እየተደመጠ መጓዙ ነው!!። ዘፈን አንዳንዶች ዘንድ ባህላዊ (በቋንቋቸው) ሲሆን ልክ እንደ ሙሃደራ (ሀዲስ) የሚቆጥሩት አሉ፣ ይህ ደግሞ በጥፋት ላይ ሌላ ጥፋት ነው። 
በዘፈን ሀራምነት ሙስሊም ሆኖ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም። አውቆ ማጣመም ፈልጎ ካልሆነ በስተቀር!፣  ምናልባትም ከአንዳንድ ጠሞ አጥማሚዎች ብዥታ የሚወድቅበት ሊኖር ስለሚችል እስቲ በጥቂቱ የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እንመልከት፣ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

{وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ} الإسراء ٦٤

ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል።” አል-ኢስራእ 64

በድምፅህ አታል” የሚለውን በዘፈንና በአሎባልታ ጫወታ በዛዛታ ማለት ነው ተብሏል። ኢብን ከሢር የተሰኘው የቁርኣን ማብራሪያ ላይ ይህን አንቀፅ በሚያብራራው ቦታ ይመልከቱ።

አላህ የመልካም ባሪያዎችን ባህሪ ሲገልፅ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

{وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا} الفرقان ٧٢

እነዚያም በውሸት የማይመሰክሩ፣ በውድቅ ቃልም ተናጋሪ አጠገብ ባለፉ ጊዜ የከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው።” አል-ፉርቃን 72

ውድቅ ቃል” በማለት የተጠቀሰው ዘፈን ነው ተብሏል። ኢብን ከሢርን ይህን የቁርኣን አንቀፅ በሚያብራሩበት ቦታ ይመልከቱ።

አላህ በተቀደሰው ቃሉ ሙሽሪኮች ቁርኣን ከመስማት እንቢተኛ መሆናቸውንና ለቁርኣን ጀርባ መስጠታቸውን ሲያወግዝ እንዲህ ብሏል:-

{أَفَمِنْ هٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ{٥٩}وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُون {٦٠}وَأَنتُمْ سٰمِدُونَ} النجم ٥٩–٦١

«ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?፣ ትስቃላችሁምን?፣ አታለቅሱምን? እናንተ ዘንጊዎች ናችሁ።» አን-ነጅም 59-61

እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ” የሚለውን ታላቁ ሷሃባ ዐብደላህ ኢብን ዐባስ እና ሱፍያን አስሰውሪ…የመሳሰሉ ሌሎችም “እናንተ ዘፋኞች ናችሁ” ማለት ነው የተፈለገበት በማለት ተናግረዋል። ኢብን ከሢር የቁርኣን ተፍሲርን ይመልከቱ።

ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ በጠንካራ ሰነድ “ዘፈን በልብ ውስጥ ንፋቅን እንደሚያበቅል” መናገራቸውም ተዘግቧል።

ስለ ዘፈን ሀራምነት ከቁርኣን አንቀፆች ባሻገር የተለያዩ እጅግ በርካታ ሶሂህ (ትክክለኛ) ሀዲሶች አሉ! ጊዜን ለመቆጠብና ፅሁፉ እንዳይረዝም ከሀዲስ ምንም አልጠቀስኩም።

ዘፈንና ነሺዳን በተመለከተ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን በሰፊው ማንበብ የፈለገ የሚከተለውን ሊንክ ተጭኖ pdf ን አውርዶ ያንብብ።
ስለ ነሺዳና ዘፈን ⤵️ pdf
https://www.tgoop.com/IbnShifa/933
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
2025/05/31 22:43:30
Back to Top
HTML Embed Code: