Telegram Web
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ተባለ‼️ ጠ/ሚኒስትሩ ጠፈር ላይ በመሆን ለአለም ህዝብ የሰላም መልዕክት ለማስተላለፍ አቅደዋል። የጉዞ እቅዱ ከተሳካ ወደ ጠፈር የተጓዙ የመጀመርያው የአለማችን መሪም ያደርጋቸዋል። በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት…
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው' ዝርዝር ዘገባ...!!!

በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።

መሠረት ሚድያ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም በዋናነት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ ምንጮቹ ለበርካታ ቀናት ሲያሰባስበው የነበረው መረጃ እንደሚጠቁመው በአለም ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የአንድ የሀገር መሪ ወደ ጠፈር ሊጓዝ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፣ መንገደኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናቸው።

በኤምሬቶች የሚገኙ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡልን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጠፈር የመጓዛቸው አላማ በርካታ ግቦችን አካቷል፣ ከእነዚህም መሀል የሰላም እና የአንድነት መልዕክት ለአለም ብሎም ለኢትዮጵያውያን ማስተላለፍ እንዲሁም ወጣቶች ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሳቡ እና እንዲነሳሱ ለማድሩግ ታስቧል።

"ውይይቱ በኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም በተባበሩት ኤምሬቶች በኩል በስፋት ንግግር እየተደረገበት ነው" ያሉት አንዱ በዱባይ የሚገኝ የመረጃ ምንጭ በተለይ ከጠፈር ላይ ሆኖ ለአለም ህዝብ መልዕክት ማስተላለፍ የእቅዱ ዋና ግብ ነው ብለዋል።

'Project X' የሚል ስም ተሰጥቶት እየተሰራበት እንደሆነ የሚነገርለት ይህ የጠፈር ጉዞ ወጪው በተባበሩት ኤምሬቶች የሚሸፈን መሆኑን አንድ ሌላ እዛው ዱባይ የሚገኝ ምንጭ ለሚድያችን ተናግሯል።

ለመዳሰስ የሞከርናቸው ፅሁፎች እንደሚጠቁሙት ወደ ጠፈር የሚደረግ ጉዞ ለአንድ ሰው ከትንሹ 250 ሺህ ዶላር እስከ ከፍተኛው 55 ሚልዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ።

ለምሳሌ 'Blue Origin' እና 'Virgin Galactic' የተባሉት መንኩራኩሮች ከንፍቀ ክበብ በታች ለሚደረግ እና ርካሽ የተባለ ጉዞ ከ200 ሺህ ዶላር እስከ 400 ሺህ ዶላር ያስከፍላሉ፣ ራቅ ያሉ እና ከንፍቀ ክበብ ውጪ የሚደረጉ የጠፈር በረራዎችን የሚያከናውኑት እንደ 'Space X' ያሉ ሮኬቶች ደግሞ በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር (7.3 ቢልዮን ብር) እንደሚያስከፍሉ ታውቋል።

ጠ/ሚር አብይ ሊጓዙ እቅድ የያዙት ከንፍቀ ክበብ ውጪ ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል (International Space Station) እንደሆነ ታውቋል፣ ወጪውም ከላይ እንደተጠቀሰው በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር እንደሚደርስ እና በኤምሬቶች እንደሚሸፈን ታውቋል።

አንድ ሌላ የስፔስ ባለሙያ ግን የጉብኝቱ አይነት 'lunar' የሚባለው እንደሆነ ሲገለፅ እንደሰሙ ጠቅሰው ይህም ጨረቃ ላይ ሳይታረፍ፣ ዙርያውን በመሄድ የሚደረግ ጉዞ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬት የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ሀዛ አል-ማንሱሪ የተባለ ዜጋዋን ወደ ጠፈር ልካ ነበር። ከዛ ወዲህም ከአሜሪካው የጠፈር ድርጅት ናሳ ጋር በመተባበር በመጪው የፈረንጆቹ አመት 2026 ላይ ሰው ወደ ጨረቃ ለመላክ እየተዘጋጀች መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከጉዞው ጋር በተገናኘ ሂደቱን ተከታትለው እንዲያስፈፅሙ ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የመንግስት ሀላፊዎች የቤት ስራ እንደተሰጣቸው የሀገር ቤት ምንጮች አረጋግጠዋል። ይህ የቤት ስራ እስከ ሀምሌ 2017 ዓ/ም ድረስ ንግግሮችን በመጨረስ ከመስከረም በሗላ ጉዞው እንዲከናወን ማድረግ ነው ተብሏል።

ነገር ግን ጠ/ሚሩ ወደ ጠፈር ከመጓዛቸው በፊት ለበርካታ ወራት ልምምድ እና የጤና ሁኔታ ክትትል ማድረግ እንደሚጠብቃቸው አስረድተዋል።

አንድ ስማቸውን የማንጠቅሳቸው የመንግስት ሀላፊን በጉዳዩ ዙርያ መረጃ ጠይቀን "በመጪው አመታት ከተያዙ እቅዶች ውስጥ አንዱ ነው። ለኢትዮጵያ እና ለአለም ሕዝብ የእርቅ እና ሰላም ጥሪ ይደረጋል" ብለው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

መሠረት ሚዲያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ፓሪስ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓሪስ ሲደርሱ በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ተደርጎላቸዋል።

በጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
‹‹መንግስት በአድማ ላይ ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር ድርድር ያድርግ፣ የታሰሩትንም ይፍታ›› ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ይህ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አድማው ከተጀመረ አንስቶ በመላው አገሪቱ 212 የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ መስማቱንና የታሰሩት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደተላከለትም አስረድቷል፡፡

የታሰሩት ሰዎች ቤተሰቦችና ጠበቆችን ማነጋገሩን የጠቀሰው አምነስቲ ሰዎቹ ሲታሰሩ ምክንያቱ እንዳልተገለፀላቸው መግለፃቸውን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም ያለ ብርበራ ትእዛዝ የጤና ባለሙያዎቹን ቤት ‹‹ጦር መሳሪያ ይኖራል›› በሚል መፈተሻቸውንና የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶቻቸው መወሰዳቸውን ገልጿል፡፡

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ትግሪ ቻጉታ ሲናገሩ ‹‹ይህ አድማ ምንም አይነት መፍትሄ ሳይገኝለት ወደሁለተኛ ሳምንቱ እየተሸጋገረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመላ አገሪቱ ወሳኝ በሆኑ የጤና አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎልን ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም መንግስት የታካሚዎችን መብት የሚገድበውን ይህንን ቀውስ ከዚህ በላይ ማራዘም የለበትም፡፡ መንግስትም ሆነ የጤና ባለሙያዎቹ ይህንን አለመግባባት በድርድር ሊፈቱ ይገባል›› ብለዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹የዘፈቀደ እስር ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ጉዳዮች ኢትዮጵያ ውስጥ የታየ ሲሆን አሁን ደግሞ ተገቢ ክፍያና የስራ ሁኔታ በጠየቁ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡›› ብለዋል፡፡ አምነስቲ በመግለጫው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ መብታቸውን ተግባራዊ ባደረጉ የጤና ባለሙያዎች ላይ እየተደረገ ያለው የእስር ዘመቻ እንዲቆምና ችግሩ በንግግር እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲ "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን የማውገዝ መልዕክት ለወጠ

የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ፣ ከሰዓታት በፊት አውጥቶት የነበረውንና አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ የፌደራል መንግሥት "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጽማቸውን የድሮን ጥቃቶች "በአፋጣኝ እንዲያቆም" ጥሪ ያቀረቡበትን ልጥፍ ከፌስቡክ እና ከቲውተር ገጾቹ ላይ አንስቶ ለውጥ አድርጓል።

በአዲስ መልክ በወጣው የአምባሳደሩ መልዕክት ላይ፣ የድሮን ጥቃትን በተመለከተ ለፌደራል መንግሥት የቀረበው ጥሪ "መንግሥት ከኃይል ውጪ ያሉ ሰላማዊ አማራጮችን መፈለጉን እንዲቀጥል" በሚጠይቅ ጥሪ ተተክቷል።

አምባሳደር ማሲንጋ ያስተላለፉት የመጀመሪያ መልዕክት በኤምባሲው የፌስቡክ እና ቲውተር ገጾች ላይ የተለጠፈው ዛሬ አርብ ግንቦት 15/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 4 ሰዓት ተኩል ገደማ ነበር። በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶችን ማቆምን የተመለከተው የአምባሳደሩ መልዕክት፤ ለፌደራል መንግሥት፣ እንዲሁም ለፋኖ ኃይሎች እና ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተለያዩ ጥሪዎች የቀረቡበት ነበር።

ለፌደራል መንግሥቱ ቀርቦ የነበረው የአምባሳደሩ የመጀመሪያ መልዕክት ሁለት ሀሳቦችን ያዘለ የነበረ ሲሆን፣ አንደኛው በመንግሥት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ የሚጠይቅ ነበር። የአምባሳደሩ የተጠቀሙት አገላለፅ የመንግሥት የድሮን ጥቃቶች "በራስ ሕዝብ ላይ" የሚፈጸሙ እንደሆኑ የሚያመለክት ነበር።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ ባለሙያዎችንና ተማሪዎችን አሰናበተ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ፣ በቅርቡ በሥራ ማቆም አድማ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎችንና የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎችን (ኢንተርን) ለማሰናበት ወስኗል። ኮሌጁ በእነዚህ የሥራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎች ምትክ አዲስ ቅጥር እንደሚፈጽምም አስታውቋል።

ኮሌጁ ባወጣው መግለጫ፣ ቅሬታ ያላቸው ባለሙያዎች እስከ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል ቀርበው ይቅርታ መጠየቅ እንደሚችሉ ገልጿል።

በተመሳሳይ፣ ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርትና በሥራ ላይ ባልተገኙ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎች (ኢንተርን) ላይም ውሳኔ ተላልፏል።

የኮሌጁ ሴኔት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እነዚህ ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዲሰናበቱ ተወስኗል። በዚህም ምክንያት፣ በእጃቸው ላይ የሚገኝ ንብረት አስረክበው ከግቢው እንዲወጡ ኮሌጁ አሳስቧል። ይሁን እንጂ፣ ቅሬታ ያለው ኢንተርን ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል ኮሌጁ አስታውቋል።
ፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

የፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንና ምርመራ እያደረገባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ በምርመራ ላይ ያሉት የጤና ባለሙያዎች ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በመተባበር "ሕገወጥ የሥራ ማቆም አድማ" በማድረግ፣ "ሁከት" በመፍጠር፣ "የታካሚዎችን ሕይወት አደጋ ላይ በመጣል" እና በሥራ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎች አድማውን እንዲቀላቀሉ "በማነሳሳት" ተጠርጥረዋል።

ፖሊስ በተጨማሪም፣ ተጠርጣሪዎቹ በጤና ተቋማት ውስጥ "የአድማ መረቦችን" በመዘርጋት፣ የጤና ባለሙያ ያልሆኑ ግለሰቦችን ነጭ ጋዋን በማስለበስ በሆስፒታሎች ቅጥር ግቢ "ሁከት" እንዲፈጥሩ በማድረግ፣ እንዲሁም በሥራ ላይ በተገኙ የጤና ባለሙያዎች ላይ "ዛቻ" እና "ማስፈራሪያ" በመፈጸም ጭምር እንደተጠረጠሩ ጠቅሷል።

የፌደራል ፖሊስ በመጨረሻም፣ ሁከትና ብጥብጥ ለማስፋፋት በሚሞክሩ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል በማስጠንቀቂያ ገልጿል።
ዲሽታ ጊና በሚል ተወዳጅ ዘፈኑ የሚታወቀው ድምጻዊ ታሪኩ ጋንኪሲ ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት የቪዛ ጥያቄ አቅርቦ መከልከሉን መዝናኛ መጽሔት ዘግቧል።

በአሜሪካን ሐገር የሚገኘው ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ዲቪሎፕመንት ካውንስል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተመሰረተበትን 42ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አስመልክቶ፡ ለሰላም እና ለፍትህ የቆሙ ሦስት ግለሰቦችን በደመቀ ስነ ስርዓት የዕውቅና ሽልማት ባለፈው ሀሙስ መስጠቱ ተገልጿል።

"ታሪኩ ጋንጋሲ ለሰላም እና ለፍትህ መስፈን ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋፅዖ እንዲሸለም" ወደ አሜሪካ እንዲመጣ ተቋሙ ለኢምባሲው ደብዳቤ ጽፎ የነበረ ቢሆንም፤ ድምጻዊው ታሪኩ ጋንጋሲም ቪዛ ለመውሰድ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ፣ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ፈረንጁ የቪዛ ኦፊሰር “ለምንድን ነው ወደ አሜሪካን ሀገር የምትሔደው?” ብሎ በአማርኛ ይጠይቀዋል።

ታሪኩም “በአሜሪካ፡ በቋሚነት ለመኖር” በሚል፡እንደመለሰና በዚህ የተነሳ የቪዛ ኦፊሰሩም ወደ ሃገርህ የመመለስ ዕቅድ የለህም በሚል ቪዛውን እንደከለከለው መጽሔቱ ዘግቦ አንብበናል። በዚህም ምክንያት ታሪኩ በሌለበት ሽልማቱ ተበርክቶለታል።

የዲሽታ ጊና ሙዚቃ አቀንቃኙ ታሪኩ፤ ከሽልማቱ በኋላ በቪዲዮ ተቀድቶ ከጂንካ ባስተላለፈው መልዕክት “ይህንን ሽልማት ስለሸለማችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፣ ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት አስቤ አልተሳካም፣ አሁን ጂንካ ተመልሼ በግብርና ሥራዬ ላይ ተሰማርቻለሁ" ብሏል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማንኪፖክስ ቫይረስ ተገኘ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አንድ የ21 ቀን ህፃን ልጅ በMpox ( ማንኪፖክስ) ቫይረስ መያዙን አረጋገጠ። ይህ በአገር ውስጥ የተመዘገበ የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ተገልጿል ።

ህፃኑን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ የእናቱም ለቫይረሱ መጋለጥ ተረጋግጧል። የህፃኑ አባት ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ከእሱ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችን የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ህፃኑ እና እናቱ በተዘጋጀ የለይቶ ማከሚያ ክፍል ተገቢው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ እስካሁን ከባድ የጤና እክል እንዳልገጠማቸው ሁሉቱ መንግስታዊ የጤና ተቋማት ባወጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

የMpox በሽታ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለ ህመም ሲሆን፣ የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል እና የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ተጠቁሟል ።

Capital Newspaper
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews የኢንሹራንስ ዘርፉ ለዉጪ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን የሚያስችል አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርግ አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ውሳኔው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እየተደረገ ካለው ሰፊ ጥረት አንዱ አካል ነው ተብሏል።

ይህ የተገለጸው 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ተቋም ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት፣ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ክፍት ያደረገው አዲሱ አዋጅ "የፋይናንስ ዘርፋችንን ለማዘመን በተደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ" እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። በዚህ ስኬት ላይ በመመስረት፣ ባንኩ አሁን ደግሞ ትኩረቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ላይ አድርጓል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube
በወተትና መሰል ምርቶች ላይ የአስከሬን
ማድረቂያ የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ተገለጸ

የወተትና መሰል ምርቶችን የቆይታ ጊዜና መጠናቸውን ለመጨመር ሲባል የአስክሬን ማድረቂያ ጭምር የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

እነዚህ ምግብ ውስጥ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር በሰዎች ላይ የሚያስከትሉ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

በባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ስራ አስፈፃሚ ሙላት ተስፋዬ፤ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶችን ለገበያ በሚያቀርቡት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰድን ነው ሲሉ ለጣቢያው ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በገበያው ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶች መገኘታቸው ቢቀጥልም፣ ከነበረበት መጠን ግን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ እንደሆነ ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጊቱን ፈፅመው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንና የቅጣት መጠንን ከፍ ማድረግ እንደሚስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ምግብ ነክና የመድሐኒት ምርቶች ላይ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት 14171 የምርመራና ፍተሻ ስራዎችን መስራቱን የባለሥልጣኑ ሪፖርት የሚያሳይ ሲሆን፤በዚህም በአጠቃላይ 3,155ቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ተጠቁሟል፡፡
በወተት ምርቶች ላይ የአስከሬን ማድረቂያ የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ተገለጸ

አንዳንድ የወተትና መሰል ምርት አምራቾች የምርቶቻቸውን የቆይታ ጊዜና መጠን ለመጨመር ሲሉ የአስክሬን ማድረቂያ (ፎርማሊን) ጭምር እንደሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።

በምግብ ውስጥ የሚጨመሩት እነዚህ ባዕድ ነገሮች በሰው ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚያስከትሉ የገለጸው ባለሥልጣኑ፣ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶችን ለገበያ በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም ሥራ አስፈፃሚ ሙላት ተስፋዬ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል።

ሥራ አስፈፃሚው አሁን ላይ በገበያው ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶች መገኘታቸው ቢቀጥልም፣ ከነበረበት መጠን ግን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም፣ ድርጊቱን ፈጽመው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንና የቅጣት መጠንን ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

የባለሥልጣኑ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በምግብ ነክና የመድኃኒት ምርቶች ላይ 14,171 የምርመራና ፍተሻ ሥራዎች ተከናውነዋል። ከእነዚህም ውስጥ በአጠቃላይ 3,155 የሚሆኑት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ተጠቁሟል።
የእነ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ ተመዘገበ!

በጌታቸው ረዳ እና ጓዶቻቸው ይመራል የተባለው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ(ስምረት) የተሰኘ ፓርቲ ዛሬ በይፋ ተመዝግቧል።

ይህ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስምረት የተሰጠው ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሚያገለግለው ለቀጣይ ሶስት ወራት ብቻ ነው ተብሏል።

ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃዱ የፖለቲካ ፓርቲውን በቋሚነት ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ እንደሚያገለግል ቦርዱ አሳውቋል።
አሜሪካ ኤምባሲዎቿ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘች!

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በውጭ አገሮች የሚገኙ ኤምባሲዎቹ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘ።የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የማጣራት ሂደት ለማስፋት በዝግጅት ላይ እንዳለ ያስተዋወቀው አስተዳደሩ፤ ለተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጥ በጊዜያዊነት አግዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ መልዕክት በሰፈረበት ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በተላከ ማስታወሻ ላይ እገዳው "ተጨማሪ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ" ይቆያል ተብሏል።አስተዳደሩ የተማሪዎች አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን የማጣራት ስራ አጠናክሮ የሚሰራ ሲሆን ይህም በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽ/ቤቶች ላይ ትልቅ አንድምታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ትራምፕ የግራውን ርዕዮተዓለም እየተከተሉ ናቸው ካሏቸው ታዋቂ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የተወሰነ ውሳኔ ነው።አንዳንዶቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በግቢያቸው ውስጥ በሚደረገው የፍልስጤም ድጋፎች ለጸረ-ሴማዊነት በር ከፍተዋል ሲል ዋይት ሃውስ ከሷቸዋል።

ዩኒቨርስቲዎች በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ለመጣስ እየሞከረ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ።ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታዋቂው ዩኒቨርስቲ ሐርቫርድ የውጭ አገር ተማሪዎችን እንዲሁም ተመራማሪዎችን እንዳይቀበል በሚል ፈቃዱን ቢሰርዙም ይህ ፖሊሲያቸው በፌደራል ዳኛ ታግዷል።ይህ በሐርቫርድ ላይ የጣሉት ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ሩብ የሚሆኑት ተማሪዎቹ ከውጭ አገር የሆኑት ተቋሙ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

Via BBC
የሀገር ዉስጥ ብድር ክምችት 2.3 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተነገረ

የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ብድር መጠን በተመለከተ የወጡ የተሳሳቱ ዘገባዎችን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው፣ እ.ኤ.አ እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር መጠን የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ጨምሮ 31.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ብድር ክምችት ደግሞ 2.3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የወጣውን ሪፖርት በማጣቀስ፣ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር መድረሱ ተነገረ” በሚል ርዕስ የወጣው ዘገባ ላይ ግድፈቶች እንዳሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል። ዘገባው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ እስከ 2023 ድረስ የነበራትን የውጭ ዕዳ መጠን 28.5 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ሳለ 62.5 ቢሊዮን ዶላር በማለት ማቅረቡ የተሳሳተ መሆኑን ሚኒስቴሩ አብራርቷል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር በአብዛኛው የተጠራቀመ ውርስ ዕዳ (legacy debt) መሆኑን ጠቁሞ፣ መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ይህንን የክፍያ ጫና ለመቀነስ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል። Capital
2025/05/30 18:05:24
Back to Top
HTML Embed Code: