Telegram Web
ደህና ነኝ!

ሰላምታ ሲጠየቅ በተለምዶ ሁሉም ሰው መልሱ ደህና ነኝ ነው! እየከፋው፣ እያዘነ፣ ውስጡ ተጎድቶ፣ ለህይወት ትርጉም አጥቶ፣ ዲፕሬሽን ውስጥ ሆኖ፣ 'ደህና ነህ?' ስንለው ወግ ነውና 'ደህና ነኝ!' ይላል! እያለቀሰ ብታገኘው 'ደህና ነኝ' ይልሀል! ቆዝሞ ብታገኘው 'ደህና ነኝ!' ይልሀል... ስንት የምናቃቸው ወጣቶች ዛሬ ሰላምታ ስንሰጣቸው 'ደህና ነኝ!' ብለውን.. በንጋታው ራሳቸውን አጥፍተዋል! ስንቱ ለቅሶ ላይ ተገኝተን... ትላንትኮ፣ የዛሬ ሳምንትኮ፣ የዛሬ ወር ኮ አጊኝቼው... 'ደህና ነኝ!' ብሎኝ ነበር... ምነው ለዚህ ውሳኔ ያበቃውን ባማከረኝ ብለን አልቅሰናል ስንቱ ጠዋት 'ደህና ነኝ!' ብሎን ከሰዓት ራሱን አጠፋ ተብለናል!

ምክንያቱም እንዴት ነህ? ለሚለው የለመድነው፣ ያደግነው፣ 'ደህና ነኝ!' እያልን ነው! መርምሮ፣ ቀርቦ፣ ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ፣ አጥብቆ ካልጠየቀን 'ደህና ነህ?' ለሚለው መልሱ የቱን ያህል ቢከፋን፣ ብናዝን፣ መልሱ ደህና ነኝ ነው! እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ?! ስንቱ ደህና አለመሆኑን እያወቅን.. 'ደህና ነኝ!' ስላለ ብቻ አልፈነዋል ስንቱ ራሱን ሊያጠፋ በኪሱ መርዝ፣ ገመድ ይዞ 'ደህና ነኝ!' የሚል ቃል እያወጣ ደህና አለመሆኑ ሁኔታው እያሳበቀ አልፈነው የሞቱን ዜና ሰምተናል? ደህና ነኝ! ያለ ሁሉ ደህና ነው? ደህና ነኝ! የሚል ቃልስ ደህንነትን ይገልፃል?

ስለዚህ ምናልባት ደህና ነኝ! ከሚለው ቃል ጀርባ ያለውን ህመም ተረድተን ወይም ገምተን ደህና መሆኑን አጥበቀን ብንጠይቀው..... ደህና አለመሆኑን ነግሮን... ምናልባት ላለበት ችግር መፍትሔ ማስቀመጥ ችለን ካለበት ዲፕሬሽን ወይም ራስ የማጥፋት ስሜት እንታደገው ይሆናል ኮ! እስኪ እንጠይቅ ስንቱ ሀሳቡን፣ ጭንቀቱን፣ የሚያካፍለው አቶ ደህና ነኝ! እያለ አተነዋል? ምናልባት ቤታችን ውስጥ አንድ ጣሪያ ስር እየኖርን ቀርቦ ባለመጠየቁ፣ አይዞህ ያልፋል ባለመባሉ ከባድ ጊዜን ብቻውን እያሳለፈ ነው? ከጊዜ በኋላ ወይ በሽታ ላይ ወይ ሞት ወስዶብናል? ብዙ ባለማውራታችን፣ ባለመወያየታችን፣ ባለመጠየቃችን፣ ባለመረዳታችን በአከባቢያችን ያለን ሰው እያጣን ነው?

አሁን እየተበራከተ የመጣው የወጣቶች ሱሳይድ ቀርቦ የሚጠይቃቸው አተው፣ ችግራቸው የሚያዋዩት አተው 'ደህና ነህ?' 'ደህና ነኝ!' በሚል ቃል እያለፍናቸው በጣም ከተጎዱ በኋላ ያኔ ባወራሁት ብለናል! በተለይ ጉዳታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ስብራታቸውን ለሰው ማዋየት ልምድ እንደሌላቸው የምናውቃቸው ምናልባት የቤተሰባችን አካልም ሊሆን ይችላል እሱ/ሷ እንደዛ ነው! እንደዛ ናት! ማውራት አትወድም፣ አይወድም ብለን አንለፋቸው! የሰው ልጅ በተፈጥሮ መፍትሔ ማግኘት ባይችል እንኳ ችግሩን በአፅኖት የሚያዳምጠው ካገኘ ይቀለዋል ማውራት በራሱ የመፍትሔው 50% ነውና!

Via: Rediet Aseffa

@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
##ለጠዋታችን!!!

💪💯 ተኝተህ ማደርህ እኮ ተዓምር ነው ምክንያቱም ዛሬን ማየት ያልቻሉ ብዙ ናቸው ፤ መተንፈስ እኮ ተዓምር ነው ምክንያቱም ከማሽን ውጪ የማይተነፍሱ ሞልተዋል ። የሚያስጨንቅህ ነገሮች በሞት ፊት ተራ ናቸው!

💪💯 ከጎደለህ ይልቅ የተሰጠህን ተመልከት ፤ ከስንቱ ችግር አልፈሀል ፤ አበቃልኝ ብለህ ተስፋ የቆረጥክባቸው ጊዜያት እንደ ቀልድ አልፈዋል እኮ ፤ ወዳጄ አላስተዋልከውም እንጂ ህይወትህ የተሞላው በተዓምር ነው ።


@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
#ለ_ልበ_ቀናዎች_ብቻ

በኖርንበት የእድሜ ቁጥር ልክ ክረምቶችን አስተናግደናል ሁሉም ክረምቶች የራሳቸውንማስታወሻ ሰተውን አልፈዋል:: በዚህኛው ክረምት ግን እኛ እራሳችን ለክረምቱ የማይረሳውን ማስታወሻ ሰተንው ይለፍ እስኪ ::
አሀዱ ቁምነገር የበጎ አድራጎት ድርጅት መጪውን ክረምት ከወቅቱ መቀየር ጋር ተያይዞ የሚመጣ ወቅቱን የሚመስሉ እልፍ ችግሮችን ችግረኛ ወገኖቻችን በገፍ ያስተናግዳሉ::
ያለንበትን የ 2014 ዓ.ም ክረምት መግቢያ ምክንያት በማድረግ የዝናቡ ጊዜ ከፍቶ ሳይመጣ አረጋውያን እናት አባቶቻችንን ወለታ እንስራላቸው::
ኑ የወገኖቻችንን ቤቶች ከክረምቱ ዶፍ እና ጎርፍ እንታደግ::

በዚህ እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ልበ ቀናዎች መሳተፍ የምትችሉባቸው መንገዶች
* በገንዘብ
* በዓይነት
* በጉልበት
* በእውቀት ...

አድራሻ:- አዲሱ ገበያ ሸገር ግራንድ ሞል ቢሮ ቁጥር EF-49
0948000004
011 8 125111
@Fekrawi
@Ahadukumneger

@Enkopawiyan

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
ስንፍና ባንተ አያምርም!

ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ! ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!

ጥሩ ቀን ተመኘሁ!!!

@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

@betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
መርዝ ምንድነው
አንድ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ ሩሚ የሰጠው መልስ ?
መርዝ ምንድነው?
ሩሚ የሰጠው መልስ ውብ ነበር?
ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉጉት፣ ወይንም ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል።

ፍርሃት ምንድነው?
እርግጠኛ አለመሆንን አለመቀበል ነው። እርግጠኛ አለመሆናችንን ብንቀበል ፣ ፍርሃት ገድል ይሆናል።

ቅናት ምንድነው?
የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል ።

ንዴት ምንድነው?
ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል።

ጥላቻ ምንድነው?
ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል
መልካም ዛሬ

@Enkopawiyan
@Enkopawiyan
ቁም ነገር tube/ subscribe @Ahadukumneger
የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ለመመረቂያ ፅሁፋቸውን ዲፌንስ ዘንጠው ቀርበዋል፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ተማሪ ግን በተራ አለባበስ እና በተበጣጠሰች የነጠላ ጫማ ቀረበ፡፡ ለዲፌንስ የተዘጋጁ መምህራን በልጁ ግድ የለሽ አለባበስ ተበሳጭተው ይሰድቡት ይዘልፉት ጀመር፡፡ ዘለፋና ስድባቸውን ከጨረሱ በኋላ እንባ እየተናነቀው መናገር ጀመረ፡፡
’’እኔ የዲግሪ መመረቂያ ፅሁፌን ለማቅረብ እዚህ ከፊታችሁ የቆምኩት በፈጣሪ ተዓምር ነው፡፡ አቅሜ በፈቀደው ልክ በጥሩ አለባበስ ቀርቤያለሁ፡፡
ቤተሰቦቼ በጣም ባለፀጋ ነበሩ የ9 አመት ልጅ አና የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡ ከሁለት እህቶቼ ጋር ብቻችንን ቀረን የአባቴ ታናሽ ወንድም አጎታችን ለተወሰኑ አመታት ከቤቱ ካስጠለለን በኋላ የቤተሰቦቻችንን ሀብት እና ንብረት በመውረስ ከቤቱ አባረረን፡፡ ሳገኝ እየሰራሁ ሳጣ እየለመንኩ እህቶቼን እና እራሴን መመገብ ጀመርኩ በዚህ ሁኔታ እያለን እኔና እህቶቼ የተሻለ ትምህርት በመማር ህይወታችንን መቀየር እንዳለብን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ግማሽ ቀን ከሰው ማሳ ላይ እያረስኩኝ እህቶቼን እመግባለሁ ግማሽ ቀን የግንባታ ስራ እየሰራሁ አስተምራቸዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን እስካሁን ቃሌን ለመጠበቅ ችያለሁ ፡፡ እኔ በዲግሪ ልመረቅ ነው እህቶቼንም ኮሌጅ አስተምራለሁ፡፡ ዛሬ እንደጓደኞቼ ዘንጬ ለመምጣት አስቤ ነበር፡፡ እህቶቼ የሴሚስተር የትምህርት ክፍያ ተጠይቀው ለሱፍ እና ለጫማ ያዘጋጀሁትን ገንዘብ ለነሱ ትምህር ለመክፈል ተገደድኩ…’’ ከፊቱ ተቀምጠው ሲዘልፉት የነበሩ መምህራን አንገታቸውን ደፉ ከመምህራኑ መካከል አንዷ ’’እባክህ ከዚህ በላይ አትናገር ለመስማት የሚሁን ጥንካሬ የለኝም’’ አለች እንባ እየተናነቃት፡፡
ተማሪው የመመረቂያ ዲፌንሱን በሚገባ ተወጣ፡፡ ሳይረዱት የዘለፉት መምህራኖች ከመቀመጫቸው ተነስተው አጨበጨቡለት፡፡ መፅሀፍን በሽፋኑ ሰውን በአለባበሱ አንዳኘው…

@Enkopawiyan
@Enkopawiyan
@Ahadukumneger
ቁምነገር Tube / subscribe
ልዩነትን ማመን!

ፈጣሪ ህልም ሲሰጥህ ፣ ባለራዕይ ሲያደርግህ ፣ ለትልቅ ስፍራ ሲመርጥህ ፣ ሲያጭህ ህልም ብቻ አይሰጥህም ፣ ራዕይ ብቻ አያስታቅፍህም ፤ እኩል በእኩል የምትቀበለው የልዩነት ህመም ይሰጥሃል ። ህመሙ ድውይ የሚያደርግህ ሳይሆን የሚፈውስህ ነው ፤ ህመሙ ጊዜያዊ እንጂ ጠላቂ አይደለም ፤ ህመሙ የሚሰራህ እንጂ የሚያፈርስህ አይደለም ።

አዎ! ማለም ቀላል ቢሆን ሁሉም ህልመኛና ባለራዕይ በሆነ ነበር ፤ ማለም ልዩነት ባይፈልግ ሁሉም አንድ ላይ ባለ ትልቅ ህልም ባለቤት በሆነ ነበር ።

አዎ! ጀግናዬ..! የህልመኝነትህ ዋናው ሚስጥር ልዩነትህን ማመንህና የህይወት አላማህን /life purpose/ ማወቅህ ነው ። የተለየህ ስለሆንክ ከሌላው በተሻለ ታልማለህ ፤ ታቅዳለህ ፤ ግብህን ታስቀምጣለህ ፣ ለእርሱም ትለፋለህ ፣ ትተጋለህ ትደክማለህ ። የድካምህ ውጤት ይታይሃል ፤ የህልምህ ጫፍ በጥቃቅን እርምጃዎች /baby steps/ ይደረሳል ፤ ግብህም ከዳር ይደርሳል ።

አዎ! ትልቅ ህልም ስላለህ ነገሮች ላይ ያለህ እይታ ልዩ ነው ፤ አቋምህ ግሩም ነው ፤ እያንዳንዱ እንሽስቃሴህ ድንቅ ነው ። ስትራመድ ፊትለፊትህን ትመለከታለህ ፤ ጎንህን ታስተውላለህ ፤ ጀርባህን ታጤናለህ ። መዳረሻህን ማወቅህ ጉዞህን ያቀለዋል ፤ ከውስጥ መኖርህ ህይወትህን ያጣፍጠዋል ፤ ያሳምረዋል ። ላንተ መኖር ፣ መብላት ፣ መጠጣት ፣ መተኛት ብቻ አይደለም ፤ ላንተ ህይውት ማብላት ፣ ማጠጣት ፣ ማስተኛት ፣ መደገፍ ፣ መርዳትም ጭምር ነው ። ህይወትህ ፣ መኖርህ ሰው ለተራበው ፣ ሰው ላጣው ወገንህ ነው ፤ ልባሽ ጨርቅ ለሌለው ፤ ቁራሽ እንጀራ ለተራበው ፤ ጥሪት ውሃ ለተጠማው ገራገር አምሳያህ ነው ። ግድ የሚሰጥህ ያንተ ድሎት ብቻ አይደለም ፤ የምታስቀድመው ሰው መሆንን ፤ ሰው ማትረፍን ነው ።

አዎ! ማለምህን እንዳታቆም ፤ ከግብህ እንዳትመለስ ፤ ራዕይህን እንዳትተወው ። አስታውስ ህልምህ ያንተ ብቻ አይደለም ፤ ከጀርባው ብዙዎች ይጠብቁታል ፤ ብዙዎች ይናፍቁታል ። ለወገንህ መድረስህ ጉልበት ይሁንህ ፤ ችግሩን ማቅለልህ ሃይል ይሁንህ ፤ ያበርታህ ፤ ያጠንክርህ ። ካንተ በላይ የሚጠብቁህ ቤተሰብ ፤ ዘመድ ፤ ወዳጅ ፤ ጓደኛ ፤ ወገን እንዳለህ አስታውስ ። ቢያንስ አንድን ነፍስ ታደግ ፤ የመኖርን ጠዓም አሳያት ፤ ትልቅ ሁን ፤ ትልቅነትህን ስራህ ይመስክር አምላክም በበረከትን ያብስርህ ።

ቸር ያውለን!!!
@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
💪💯 ትርፍህ ሰው ነው!

💪💯 በተተከልክ ማግስት ጥላ አትሆንምና ለጊዜው መተከልህ መልካም ነው ። ምንም ደስተኛ ለጊዜው ደስተኛ ባትሆንም በህይወት መኖርህ ትልቁ በረከትህ ነው ። ሰዎችን ለመርዳት እያሰብክ ባታደርገው እንኳን ለጊዜው ማሰብህም በቂ ነው ። ባንተ ድካም ቤተሰቦችህ እንዲያርፉ ብትፈልግም ለጊዜው ፍላጎትህ ከምንም በላይ ነው ። የመታስባቸው መልካም ተግባራት መነሻቸው ሃሳብ ነው ፤ መሰረታቸው ፅኑ ፍላጎት ነው ፤ ቅንነት ነው ፤ ደግነት ነው ። የመልካም ዕሳቤህ መገኛ አንተ ነህ ። ፍላጎትህ የትልቅነትህ ሚስጥር ነው ፤ ሃሳብህ የሰውነትህ ጥግ ነው ። ፍላጎትህ ያለምክንያት አይመጣም ፤ ሃሳብህም በባዶ አልተወለደም ፤ አንድ ቀን እውን መሆኑ አይቀርም ። ደጋግ ልቦች በቅን ሃሳባቸው ብቻ ያርፋሉ ፤ ሰላምን ያገኛሉ ፤ ይረጋጋሉ ።

💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ልብ ቀና፣ ደግ አሳቢ ሰው በስብዕናው በአመለካካቱ ብቻ ይደሰታል ። ክፋት የሌላት ልብ በምንም አጋጣሚ ከፍታን ከሌላ ሰው አትጠብቅም ። በመልካምነት መኖር ክፍያ የለውም ፤ ወጪ አያስወጣም ። ለሰው መጨነቅ ፣ ለሰው ማሰብ የሚያጎድልብን ነገር የለም ። አንድ የማናውቀውም ሆነ የምናውቀው ሰው በእኛ ምክንያት በህይወቱ የሆነ ነገር ቢያገኝ ፣ ቢሳካለት ፣ ቢለወጥና ቢያድግ የሙላታችን ምክንያት ይሆንልናል ። ኬትም የማይገኝ የልዩ ደስታ ባለቤት ያደርገናል ።

💪💯 አዎ! መልካምነት የድንቅ ሰዎች መገለጫ ነው ። ለወገን ደራሽነት ፣ አጋዥነት ፣ አበርታችነት የንፁ ልቦች ስጦታ ነው ። የሰውነትህ ሙሉነት በጓደኛህ ደስታ ስትደሰት ነው ፤ ለቤተሰብህ እድገት በምታደርገው ጥረት ነው ፤ ለወገንህ በምታበረክተው አበርክቶት ነው ። ለእራስ ብቻ መሮጥ የትም አያደርስም ። ትርፍህ ሰው ነው ። ምንም ብትሰራ የሚጠቀመው ሰው ነው ፤ ያንተም ተጠቃሚነት ከሰው ይነሳል ። ብትደክም ፣ ብትለፋ አገልጋይነትህ ለወገንህ ነው ። ምንም እንኳን ለእራስህ ጥቅም ብትለፋ የምትጠቀመው በሰጠሀው አገልግሎት ልክ ነው ።

💪💯 አዎ! በመልካምነት ተመላለስ ፣ በቅንነት ስራ ፤ ጣፋጩን ስጦታህንም ተቀበል ። በንፉግነትህ ከምታገኘው ገንዘብ በአገልጋይነትህ ፣ በመስጠትህ የምታገኘውን ደስታ እጅጉን የተሻለ ነውና እርሱን ምረጥ ።

ቸር ዋሉልኝ!!!
@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
ሳታልፍ በፊት ኑር!

በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው።

ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ!

ጥሩ ቀን ተመኘንላችሁ🙏🙏🙏

@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

@betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
💪💯 እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል!

💪💯 ሰው በሁኔታዎች ሲለካ አምላክ ግን ከሁኔታዎች በላይ ነው ፤ ሰው ደስታን ሲመኝ ደስታ በእራሱ ፈጣሪ ነው ፤ ሰው አምላኩን ፍለጋ ሲደክም እርሱ ግን በውስጡ አለ ። የነገሮች መደራረብ ፣ የሃዘን ብዛት ፣ የጭንቀቱ ማየለ የአንድ ሰሞን ሁኔታ ነው ። የችግሮች ክብደት ጊዜያዊ ሁኔታ ነው ። ከነዚህ በላይ የሆነ አምላክ ግን ምንጊዜም አብሮን አለ ፤ ውስጣችን ይገኛል ። "አምላክ የት ይገኛል ቢባል ሁሉም ቦታ ይገኛል ?" በተለይ የእጅ ስራው በሆነውና አምሳሉ በሆነው የሰው ልጅ ውስጥ በሙላት ይገኛል ፤ ዘወትር ይመላለሳል ። ስራውን ለመስራት፣ ተአምራትን ለማድረግ ግን የእኛን ፍቃድ ይፈልጋል ።

💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ጫጫታ ውስጥ ሆነህ የአምላክህን ድምፅ አትሰማም ፤ ውስጥህን አታዳምጥም ፤ ከመንፈስህ ጋር አትገኛኝም ፤ ተዓምራዊውን አንተ አታገኘውም ። የእራስህ ጊዜ ያስፈልግሃል ፤ አምላክህን በግልፅ የምታወራበት ፣ መንፈስህን የምታናግርበት ፣ ውስጥህን የምትቃኝበት ፣ ሰላምን የምትሰብክበት የተነጠለ ፣ ከምንም ያልተገናኘ ያንተና የፈጣሪህ ብቻ የሆነ ጥርት ያለ ጊዜ ያስፈልግሃል ። ብቸኝነት አያስፈራም ፤ ከእራስህ ጋር ስታወራ ከአምላክ ጋር እንደምትወያይ አስብ ፤ ቀጣይ እርምጃዎችህን ሲመራህ ትመለከታለህ ፤ ልዩነትህን ያሳይሃል ፤ የሁኔታዎችን አላፊት ያንተን ጥንካሬ ያስገነዝብሃል ።

💪💯 አዎ! እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል ፤ የተሰጠህ አቅም በትናንሽ ክስተቶች የሚደክም አይደለም ፤ ሰውነትህ በጊዜያዊ ክስተቶች የሚከስም አይደለም ። ስራውን የሚሰራው ፣ ያልቻልከውን የሚያስችልህ ፣ የከበደህን የሚያቀልልህ ፣ ዛሬህንም ሆነ ትናንትህን ወደ ታሪክ የሚቀይር ፣ የሰጠህን የሚያስችልህ ፣ የመጣብህን የሚያሳልፍህ የዘወትር ጠባቂህ ፈጣሪህ ነው ። በእርግጥ ከገንዘብህ ፣ ከንብረትህ ፣ ከዝናህ ፣ ከወዳጅህ በላይ በአምላክህ ሃይል የተማመንክበት ጊዜ ካለ አስታውስ ። በቸገረህ ሰዓት መጠለያህ ማነው ? በፈተና ወቅት መደበቂያህ የት ነው ? በጨለብህ ጊዜ ብረሃንህን የት ትፈልጋለህ ? ሁሉን አንድ ላይ የያዘ ፣ የጥያቄዎችህን ምላሽ ከምታገኝበት ከአባትህ እቅፎፍ አትራቅ ፤ በቻልከው ልክ ተጠጋው ፤ ከሁሉም በፊት እርሱን አስቀድም ።


@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

         @betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
💪💯 ፅኑ ፍቅሩ ነው!

💪💯 የመጥፎ ልማድን ክብደት ፣ ለማቆም ወይም ለመቀየር በምንታገልበት ጊዜ እናውቀዋለን ። ምንያህል እንደተቆጣጠረን ፣ ምንያህል እንደተዋሃደን ፣ ምንያህል ነብሳችንን እንደሚያስጨንቃት እንገነዘባለን ። አንወደውም ግን እንደጋግመዋለን ፤ ጠዓሙ መራራ ፣ ስሜቱም ጎምዛዛ ነው ነገር ግን እንደጣፈጠንና እንደተመቸን ለማስመሰል እንሞክራለን ። እየገደለን እንደሆነ እያወቅን እርሱን ተቀብለን በሌላ መንገድ መኖርን እንመርጣለን ። የዚህ ሁሉ ምክንያት መቀየሩን ወይም ማቆሙን ሳንፈልግና ሳንችል ቀርተን ሳይሆን ለማቆም ጠንካራ ምክንያት ስላጣን ነው ።

💪💯 አዎ! እራስን መውደድ ፣ ለእራስ ማዘን ፣ እራስን መቀበል ፣ በእራስ መኩራት ምክንያት ካልሆነን ፣ ብርታት ካልሰጠን ፣ ፍላጎታችንን ካላጠነከረ መጥፎና አስከፊ የተባለውን የለውጥና የእድገት ጠር የሆነን አጉል ልማድ ማቆም እጅግ አስቸጋሪና አዳጋች መሆኑ አይቀርም ። ነገር ግን ከእኛ የሚበልጥ ፣ ሊቆጣጠረን የሚገባ ሌላ ትልቅ ሃይል ፣ ትልቅ ምክንያት አለ ። በእራሳችን እስክንጨክን ያደረገን ክፋት ፣ እራሳችንን እንድንጠላ ያደረገንን መጥፎ ስሜት የምንገታው ፣ እኔ ብቻ ልኑር የምንልበትን የከፋ እራስወዳድነትን የምናስቀርበት ፣ ደግነት የምናደርገው ፣ ሰላምን የምንመርጠው ፣ ለእራሳችን የምናዝነው ፣ ሰዎችን የምንረዳው ፣ የምናስብላቸው ፣ ቅንነት የሚዋሃደን ከፈጣሪ ፍቅር የተነሳ ነው ።

💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ፅኑ ፍቅሩ ነው! አምላክህን ትወደዋለህ ፣ ታፈቅረዋለህ ፣ ዘወትር ትለምነዋለህ ፣ ትማፀነዋለህ ። ለአምላክህ ያለህ ፍቅር ገደብ የለውም ፤ በህይወትህ ሙሉ እንደርሱ የምታምነው ማንም የለም ። እምነትህ ፍቅርህን አጠነከረው ፣ ከወትሮው በተለየ ቁርኝትህን አጎለበተው ። እርሱ ቸር አባትህ የሚጠላውን እንድትጠላ ፣ የሚወደውን እንድትወድ ፣ የሚጠየፈውን እንድትጠየፍ ፣ የሚያቀርበውን እንድታቀርብ የሚያደርግህ አምላክህን መውደድህ ነው ።

💪💯 አዎ! በእራስህም ሆነ በሰዎች ላይ የምታደርገውን ክፋት ፣ ጭካኔ ፣ በደል ፣ ስቃይ ለማንም ብለህ ሳይሆን የምትወደው አምላክህ ስለማይወደው ፣ የመረጠህ የመረጥከው አባትህ ስለማይመርጠው ፣ የዘላለም ገዢህ የዘላለም ንጉስህ እጁን ስለማያስገባበት ፣ ስለሚጠየፈው በእርግጥም አንተም ፣ ትጠየፈዋለህ ፣ ትተወዋለህ ። ፍቅሩን ማሰብህ ፣ መውደዱን በልብህ መያዝህ ከክፋት ፣ ከበደል ፣ ከሀጢያት እንድትርቅ ያደርግሃል ። ትወደዋለህና የሚወደውን አድርግ ፤ መርጠሀዋልና የመረጠውን ፈፅም ፤ በእራስህ ተስፋ ብትቆርጥ ፣ ብታዝን እንኳን ተስፋ ባደረከው ፣ በተማመንከው አምላክህ ፍቅር የተነሳ መልካም ፣ አዛኝና ልባም ሰው ሁን ።

ቸር ዋሉልኝ!!!

@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

            @betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Forwarded from Fekrawi
ሰላም ለናንተ የሀገሬ ልጆች ... በትናንት እና በዛሬ በዛሬ እና በነገ መካከል ለምንኖር ለእኛ ... ካለንበት ከምንኖርበት ያለመጉደል ቀጠና ወጥተን ከመኖር ወደ አለመኖር ከመብላት ወዳለመብላት
ከመልበስ ወደመታረዝ የምንመጣበት ቀን አይታወቅምና እንደ ሰው ነግ በኔን በመፍራት አንድም ፈጣሪያችንን ለማስደሰት እንዲያም ሲል ልባችንን በማድረግ ደስታ ለመሙላት በጎ ምግባርን እንከውን ...

አሀዱ ቁምነገር የበጎ አድራጎት ድርጅት የፊታችንን የዘመን መለወጫ በዓል የ 2015 ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ቁጥራቸው 1000 ለሚያህሉ የጎዳና አዳሪ ወንድም እህቶችችን አስታዋሽ ጠያቂ የሌላቸውን ምስኪን አረጋውያንን የመመገብ የማልበስ እና የመዝናኛ ፕሮግራምን በማሰናዳት ላይ እንገኛለን ::

በመሆኑም "ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለፈጣሪው ያበድራል" ነውና ነገሩ እርሶም እራሶን እና በዙሪያዎ ያሉትን በማስተባበር #የገንዘብ
#የዐይነት
#የአልባሳት እና የመሳሰሉትን ድጋፎች በማድረግ ከምስኪኖች ጎን ይቆሙ ዘንድ በፍፁም ትህትና እንጠይቃለን::

ልበለጠ መረጃ
0948000004
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይሂሳብ ቁጥር
1000312029999

@Ahadukumneger

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
💪💯 ሴት ነሽ!

💪💯 አዎ! ሴት ነሽ ፤ በሴትነትሽ ሃሳብ አለሽ ፤ ህልም አለሽ ፤ ራዕይ አለሽ ፤ ውጥን አለሽ፤ ግብ አለሽ ። በቀድሞ ማንነትሽ መቀጠል አትፈልጊምና ለመቀየር ወስነሻል ፤ የሚያስጠቃሽን ባህሪ ለይተሻልና ለማሻሻል ተነስተሻል ። ማንም እንደፈለገው የሚገምትሽ ፣ የሚጎዳሽ ፣ የሚጫወትብሽ አይደለሽም ። ሴትነትሽ የምትጠቂበት ሳይሆን እራስሽን የምታስከብሪበት ፣ ለሌሎች ከለላ ፣ ድጋፍ የምትሆኚበት ፣ ብቻሽን ብቁ እንደሆንሽ የምታረጋግጪበት ፣ ጠንካራ እንደሆንሽ የምታስመሰክሪበት ፣ ማንም ሳይኖር ጎልተሽ የምትወጪበት ፣ ደምቀሽ የምትወጪበት ብርቱ ሃይልሽ ነው ።

💪💯 አዎ! ጀግኒት..! ሴት ነሽ! ብርቱ ሴት ፣ ጠንካራ ሴት ፣ እራሷን የሆነች ፣ እራሷን ያገኘች ፣ ማንነቷን የተቀበለች ፣ በእራሷ ደስተኛ የሆነች ፣ ጥገኝነትን የጠላች ፣ እራሷን ያገኘች ጀግና ሴት ነሽ ። በሰዎች ተገደሽ ፣ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ወድቀሽ ፣ በወዳጅ በዘመድ ጫና ውስጥ ገብተሽ ፣ የእራስ ምክንያት ሳይኖርሽ ፣ ምርጫ አጥተሽ የምትቀየሪ ፣ ሌላ ሰው የምትሆኚ አይደለሽም ። ሰዎችን ከማጣት በላይ እራስን ላለማጣት ቅድሚያ ትሰጪያለሽ ፣ ከውጪው ጫጫታ ይልቅ የልብ መሻትሽ ሚዛን ይደፋብሻል ፤ ፍላጎትሽ ያይላል ፤ መሆን የምትመኛት ሴት ትበልጥብሻለች ። አዎ! ምርጫሽ የሰነፍ አይደለምና በምርጫሽ ልክ ብርቱ ሁኚ ፣ ውሳኔሽ ቀላል አይደለምና በውሳኔሽ ልክ ጠንክሪ ፣ የሚጠብቅሽ የለውጥ መንገድ ፈተኝ ፋታ የማይሰጥ የሚገዳደርሽ ነውና ይበልጥ እራስሽን አዘጋጂ ፣ ፍላጎትሽ ልዩ ነውና ልዩ መሆንን እወቂበት ። የተለወጠችውን መልካም ብርቱ ሴት ትፈልጊያታለሽና ጉዞሽን አታቋርጪ ፤ ያለምሺያትን ሴት ሳትፈጥሪ አታቁሚ ፤ የዘወትር ምኞትሽን ሳትጨብጪ አትመለሺ ።

ቸር ዋሉልኝ!!!
@enkopawiyan
@enkopawiyan

     @betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
የሕይወት ትልቁ ስህተት ማርፈድ ነው። ሁሉም የሚያምረውና የሚበጀው በጊዜው ሲሆን ነው። እናም ማድረግ ያለብህን ነገር ሳታመነታ አድርገው፤ መተው ያለብህም ነገር ሳታቅማማ  በጊዜ ተወው፤ መወሰን ያለብህ ጉዳይ ካለም ዛሬውኑ ወስን። ህይወት ማለት እንደ አልፎ ሄያጅ ወንዝ ናት፤ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትራመድም። ጊዜና ዕድሜህን በአግባቡ መጠቀም ደግሞ የብስለትህ መለኪያ ይሁን።
ፀፀት_መጀመሪያ_መጥቶ_አያውቅም_መጨረሻ_እንጂ ስለዚህ ነገን እንዳይቆጭህ ዛሬን አታርፍድ።

ዉብ ቀን ይሁንላችሁ!!!

@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

      @betina21
❤️በመንገድህ ሁሉ ለለመነህ የምትሰጠው ነገር አታጣም ፤

💛ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ ። አንዳንዶች
ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው ፤ አንዳንዶች ሰላምታህን ፤ አንዳንዶች ጊዜህን ፤ አንዳንዶች ሃሳብህን ፤
አንዳንዶች ድጋፍህን ፤ አንዳንዶች ጓደኝነትህን ።

💚 ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን (ከምንም በላይ ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች) ፤ ያልተጠቀምንባቸው ሰስተን ሳይሆን አለን ብለን ስላላመንን ይሆናል ።

💙ሌላው ይቅር ፈገግታና ደስታችን ፤ እንኳን የምናውቀውን ሰው ይቅርና የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው ።

💜የሚለኩሳቸው ያጡ ብዙ ሻማዎች አሉ ፤"ለኳሾቹም ሻማዎችም ግን እኛ ነን ፤ ክብሪቱ ደግሞ ፍቅር‼️
         መልካም ቀን🙏
💚💛❤️💚💛❤️💚

@enkopawiyan
@enkopawiyan

    @betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
💪💯 #አብርሃም ሊከን በ21 አመቱ ንግድ ለመስራት ሞክሮ ከሰረ ። ተስፋ አልቆረጠም ። በ22 አመቱ ከህግ ትምህርት ቤት ተባረረ ። ተስፋ አልቆረጠም ። በ24 አመቱ በድጋሚ ንግድ ሊሰራ ሞክሮ ከሰረ ። አሁንም ተስፋ አልቆረጠም ።  በ26 አመቱ ጣም የሚያፈቅራት የልጅነት ፍቅረኛውን በሞት አጣ ። ፈጣሪውን አላማረረም ። በ34 አመቱ ለምክር ቤት ተወዳድሮ ሳይሳካለት ቀረ ። ድጋሜ መሞከርን አላቋረጠም ። በ45 አመቱ ለሴናተርነት ተወዳድሮ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ።

💪💯 #አብርሃም ሊከን አሁንም ተስፋ እንደሰነቀ ነው ። ተስፋ ሳይቆርጥ በ47 አመቱ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳደረ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ። ነገርግን ከመወዳደር ወደኋላ አላለም ። በ49 አመቱ በድጋሚ ለሴናተርነት ተወዳድሮ በድጋሚ ሳይሳካለት ቀረ ።  በመጨረሻ ግን በ52 አመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆን ቻለ ። የሰው ልጅ ተስፋ ካልቆረጠ መሆን የሚችለውን ይሆናል ።

💪💯 ተስፋ የሰው ልጅ ተረጋግቶና በሠላም ይኖር ዘንዶ ከፈጣሪው የተሰጠ ዋነኛው ስጦታ ነው ። ከ22ቱ ፍጥረታት መካከል በተስፋ የሚኖር የሰው ልጅ ብቻ  ነው ። ሰው በተስፋ የማይኖር ከሆነ ባዶ ፣ ተቅበዝባዥና በጭንቀት የሚኖር ብሎም ራሱን ወደ መጥላትና ማጥፋት የሚጓዝ ግደለሽ ይሆናል ።

💪💯 ተስፋ ማለት በየዕለቱ ሊገጥሙን ለሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች መፍትሔ ፣ ለሃዘናችን መጽናኛ ፣ ለደስታችን ፍሬ በጉጉት የምንጠብቅበት ብቻም ሳይሆን  አስቸጋሪ መስለው ለሚታዩን ነገሮች በጎ ነገርን የምናይበት ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው ።

💪💯 ለዚህም ነው ሰዎች በምክራቸው "ተስፋችሁ ሕያው ፣ ጠንካራ ፣ ጽኑና የማይናወጥ መሆን አለበት" የሚሉት ።

ተስፋ ካለን ብዙ ነገሮች አሉን ፤ የምንሄድበት አቅጣጫ ፣ የምንንቀሳቀስበት ኃይል ፣ ብዙ አማራጮች ፣ ሺህ መንገዶችና ሊገመቱ የማይችሉ ህልሞች አሉን ። ተስፋ ካለን መሄድ ወደ ምንፈልግበት ቦታ ግማሽ መንገድ ላይ ደርሰናል ማለት ሲሆን ፣ ተስፋ ከሌለን ወይም ተስፋ ከቆረጥን ግን ለዘለዓለሙ ጠፍተናል ማለት ነው ።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ 💚💛❤️

@enkopawiyan
@enkopawiyan


      @betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
ከድሀ ጋር ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ብላ ፍቅረኛዋን ባለበት ጥላው ሄደች ልቡ ክፉኛ ተሰበረ አበባውን ታቅፎ ብቻውን ፈዞ ቀረ...:: ህይወት ቀጠለ እርሷ ከአመታት በኃላ የአንድ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አግብታ ጥሩ ኑሮን መኖር ጀመረች ....
አንድ ቀን የባሏ መስሪያ ቤት በሄድችበት ወቅት የድሮ ፍቅረኛዋን አገኘችው እንዴት ያለ ሀብታም ባል እንዳገባች ልታሳየው አስባ ለማስተዋወቅ ስትዘጋጅ ባሏ ቀድሟት እንዲህ አለ ....
ውዴ ተዋወቁ እርሱ ማለት የድርጅታችን ባለቤት የኔም አለቃ ነው ይህን ጨምሮ 4 ድርጅቶች አሉት እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰለሽ አላት ...
ድይህን ጊዜ ሚስት የመትናገረው ጠፋት አፏ ተሳሰረ ደርቃ ቀረች....

ብሩክ ዚቲ

ወዳጆቼ ቂቤ ተገፍቼ ነው አናት ላይ የወጣሁት እንዳለችው ሁሉ እናንተም መገፋታችሁን መጠላታችሁን በሙከራዎቻችሁ የሚመጡባችሁን ዘለፋ እና ንቀት አጋዥ እረዳት ማጣታችሁን እንደ መልካም አጋጣሚ ቁጠሩት መጋፋት መናቅ መተው እና ችላ መባላችን ላለምስራት ሳይሆን እንዲያውም በትኩረት በትጋት ለመስራት ምክንያት ይሁነን:: ሰናይ እለት ቸር ይግጠመን::

@Fekrawi
ከጎንህ ያለችው ሚስትህ የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት ደስተኛ ያልሆንክበት ልጅህ መውለድ ለማይችሉት ሁሉ ምኞት ነው ትንሿ ቤትህ ቤት ላጡ ሁሉ ምኞት ናት አድካሚ ስራህ ስራ ላጡት ሁሉ ምኞት ነው ትንሿ ገንዘብህ ምንም ገንዘብ ለሌላቸው ሁሉ ምኞት ናት በገንዘብ የማይተመነው ጤናህ ጤንነት አጥተው ለሚሰቃዩ ሁሉ ምኞት ነው በነፃነት በእግርህ መጏዝህ እስር ቤት ሆነው ለሚሰቃዩ ሁሉ ምኞት ነው ፈጣሪህ የደበቀልህ ነገር ሁሉ ተዋርደው ላፈሩ ሁሉ ምኞት ነው ፈጣሪን ተመስገንእንበለው

ምንጭ Facebook

@Fekrawi
ህይወትህ ያንተ ነው!

ለትውስታ፦ አውቀህ ፈልገህ እራስህን እየፈተንከው ነውን? ሁን ብለህ እራስህን ጫና ውስጥ ከተሃልን? ወደህ ወዳጆችህን ለይተሃልን? ፈቅደህ እራስህን የለውጥ ሂደት፣ የእድገት ጉዞ ውስጥ ከተሃልን? ውሃ ያጠጣሀው ተክል መሬት ይይዛል፣ ያድጋል፣ ፍሬም ያፈራል። የሰራህበት ማንነት፣ ለአዲስ ክስተት ያጋለጥከው፣ የፈተንከውና ለከባድ ሁነት ያጋለጥከው አንተነትህም የተሻለ ሰው ሆኖ ታገኘዋለህ፣ ጠንካራና ብርቱ ሰው ሆኖ ታገኘዋለህ። በህይወትህ እጅግ ወሳኝ የሆነውን ጉዳይ ውሃ አጠጣው፣ አጥብቀህ ስራበት፣ ዋጋ ክፈልበት፣ የሚገባውን ትኩረት ስጠው። ህይወትን እየቀለድክ አታሸንፈውም፤ ህይወትን ችላ እያልክ፣ ትኩረት እየነፈከው አታሻሽለውም። የህይወት ፈተናህ ሲያንስ፣ ጭንቀት ሲርቅህ፣ ከጫናዎች ውጪ ስትሆን በእርግጥ እያደክ እንዳልሆነ አስተውል።

አዎ! ጀግናዬ..! ህይወትህ ያንተ ነው አትቀልድበት፤ የግል ጉዳይ የእራስህ ነው፤ የሚመጣብህ እያንዳንዱ ፈተና ያንተን ጥንካሬ ይጠይቃል፤ ያንተን ብርታት ይፈልጋል። እላይ ታች፣ ወዲህ ወዲያ ማለትን በምትፈልግ አለም ውስጥ እየኖርክ ቁብነገር በሆነው ህይወትህ ብትቀልድ በተራው ህይወት በእራሱ ሲቀልድብህ መመልከትህ አይቀርልህም። አሁን አሁን ብዙዎቻችን ፋታ አጥተናል፣ ማረፍ አቅቶናል፣ ነገሮችን መረዳትና ማስተዋል ከብዶናል፣ ለማን ትኩረት መስጠት እንዳለብን፣ ምንንስ ማስቀደም እንደሚገባን ዘንግተናል። እዚም እዛም ጫወታ ያታልለናል፣ ቀልድ ማየቱ፣ ሌሎች በህይወታችን ሲያፌዙ አብሮ መሳቅን መርጠናል። በዚህ መንገድ ግን እራሳችንን ልናሸንፍ አንችልም። አንዳንዴም ቢሆን ለእራሳችን ብለን ቆምጠጥ ማለት ይኖርብናል። እየቀለድክ የምታድግበት የስራ ዘርፍ የለም፤ እያሾፍክ የሚለውጥህ ተግባርም አይኖርም።

አዎ! ቀልድም ይሁን ቁብነገር ያማረ ፍሬን ሊያፈራ የሚችለው ስራዬ ብለህ ወገብህን ታጥቀህ ስትይዘው ብቻ ነው። አንዳንዱ አንተን አይቶ፣ ሁኔታህን አንብቦ የስራህን ጥራት ያውቀዋል፤ አንዳንዱ ከጅማሬህ ተነስቶ የት እንደምትደርስ ይገነዘባል፣ ሌላው ደግሞ ተግባርህን ብቻ ተመልክቶ ለምን እንዳደረከው ይረዳል። ዘመንህን ሁሉ እየቀለድክ ብትኖር የቀልድህን ክፍያ በአመሻሹ የህይወትህ ክፍል ታገኘዋለህ፤ ዕድሜህን በሙሉ ወሬ በማመላለስና የሰዎችን ስራ በማደማመቅ ብቻ ብታሳልፍ የወጣችልህ ጀምበር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትጠልቅብህ አትጠራጠር። ህይወት በጫወታ ቢቻ የሚመራ፣ በቁብነገር ብቻም የታጠረ ጉዞ አይደለም። ሁለቱንም በማጣጣም ጎን ለጎን ማስኬድ የግድ ነው፤ ከሁሉም ከሁሉም ግን ቁብነገር በሆነው የህይወታችን ክፍል ላይ ማሾፍና መቀለድ የከፋ ዋጋ እንደሚያስከፍለን መረዳት ተገቢ ነው።
═════════❁✿❁ ═════════

ለንጋታችን
@btina21
@enkopaweyan
@enkopaweyan
2024/06/01 21:02:55
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243