Telegram Web
አለምአቀፍ የላብ አደሮች ቀን !

📌የላብ አደሮች ቀን በአለምአቀፍ ደረጃ ግንቦት 1 ወይንም ሚያዚያ 23 ይከበራል።

📌ሜይ ደይ ወይንም ሌበር ደይ የሚሉ ስያሜዎችም አሉት።

📌ጅማሮው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1886 በአሜሪካን የሰራተኞች ማህበራት ንቅናቄ ጋር ተያይዞ መሆኑ ይነሳል።

📌በ 19ኛው ክፍለዘመን በአሜሪካ የኢንደስትሪ መስፉፉትን ተከትሎ በርካታ የስራ እድል ተፈጥሮ ነበር ሆኖም ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት በእነዚህ ተቋማት እስከ 16 ሰአታት መስራትን ይገደዱ ነበር።
በዚህም ለሞት፣ ለከፍተኛ የጤና ጉዳትና፣ ዘላቂ የጤና ቀውስ ውስጥ ይገቡ ነበር።

📌ዝቅተኛ ክፍያ፣ በቀን 16 ሰአታት መስራትና ሌሎችንም የሰራተኞች የመብት ጥያቄዎች ባነገቡ ማህበራትና ንቅናቄዎች የስራ ሰአታት በቀን ወደ 8ሰአት ዝቅ እንዲል ሆኗል።

📌 ለዚህ ቀን እውናዊነት በርካቶች የአካልና የህይወት መስዋትነትን ከፍለውበታል።

📌 በአለምአቀፍ የላብአደሮች ቀን ግንቦት አንድ እንዲከበር የሆነው በአውሮፓውያኑ 1886 ግንቦት 4 በቺካጎ ሄይማርኬት በነበረው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ በፈነዳ ቦንብ የሞቱና የታሰሩ ሰዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው።

📌በአውሮፓውያኑ 2023 በተሰራ ጥናት በአለምአቀፍ ደረጃ 3 .62 ቢሊየን ላብ አደሮች ይገኛሉ።

📌 ዘንድሮም በተለያዩ ሀገራት በድምቀት ይከበራል።

#እንኳን ለአለምአቀፍ የላብ አደሮች ቀን አደረሳችሁ።
እንኳን ለ84ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሰዎ፤ አደረሰን!
ታላቅ የእግርኳስና የሙዚቃ ድግስ

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ማክሰኞ ቀን 05/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የሙዚቃ ድግስና የእግርኳስ ጨዋታ ፕሮግራም በፉትሳል(ትንሿ ሜዳ) ይደረጋል።

በእለቱም የሚኖሩ ፕሮግራሞች:
1. የሙዚቃ እና የውዝዋዜ ፕሮግራም በተለያዩ ተጋባዥ ተወዛዋዦች
2.የእግርኳስ ውድድር በተማሪህብረት + ተማሪ ፖሊስ አመራሮችና በዩንቨርሲቲው መምህራን መካከል
3. የእግርኳስ ውድድር በዩንቨርሲቲው መምህራን እና በሳፋሪኮም ክሩ(ቡድን)
4. የገመድ ጉተታ

የሚገኙ እንግዶች
- የሳፋሪኮም አመራሮችና ማናጀሮች
- የዩንቨርሲቲው አመራሮች
- ተጋባዥ ተወዛዋዦችና ድምፃዊያን

በተጨማሪም ለታዳሚዎች የተዘጋጁ
- የተለያዩ የሞባይል ካርድ ሽልማቶች
-  የሳፋሪኮም የስልክ ቀፎ  ሽልማቶችና ሌሎችም አጓጊ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል።

ስለዚህ እናንተም በእለቱ ይህንን ፕሮግራም ከጓደኛዎ ጋር በመታደም የእነዚህ ሽልማቶች ተካፋይ እንዲሆኑና የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።


https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ነገ ማለትም በቀን 05/09/2017 ዓ.ም የሚካሄደው መርሀግብር በጉጉት ይጠበቃል፡፡ የተለያዩ ዝግጂቶች ተዘጋጂተው እናንተን እየጠበቁ ነው ነገ ጠዋት 2:30 ፕሮግራሙ ይጀምራል ሁላችሁም ተሳታፊወች እንድትሆኑ ተጋብዛችኀል!!

.....የሳፋሪኮም አመራሮችና አስተባባሪዎች ከወዲሁ ዝግጂታቸውን ጀምረዋል፡፡

https://www.tgoop.com/DBUstudent
ቅዳሜ 09/09/2017 ለሚደረገው GC CUP በዛሬው እለት ሁሉም የጂሲ ተወካይ በተገኘበት ድልድል ወጥቷል።

በመጀመሪያ 15 ቡድኖች እንደሚሳተፉበት የተገለፀው ጂሲ ካፕ ነገር ግን የ2013 ባች ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ቀጣይ አመት ጥር ላይ ተመራቂ ቢሆኑም ለአራት ዲፓርትመንት ብቻ ጂሲ ካፕ ስለማይዘጋጅ በአሁኑ አመት እንዲጫወቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ወደ ጨዋታው ተቀላቅለዋል። በዚህም አብዛኛው ተማሪያቸው ኢንተርንሺፕ በመውጣቱ ምክንያት ከሁሉም ዲፓርትመንት ተደርጎ አንድ ቡድን ተዋቅሯል።

ጨዋታዎች በጥሎ ማለፍ የሚካሄዱ ሲሆን ማኔጅመንት በእጣ ስምንቱ ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም የኢንጅነሪንግ ቡድን ወደ ጂሲ ካፕ መግባቱን ተከትሎ ከኢንጅነሪንግ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
ለተፈጠረው ስህተት ማኔጅመት ተማሪዎችን እና ባጠቃላይ ተሳታፊ ቡድኖችን ይቅርታ እንጠይቃለን።

ይህንንም ተከትሎ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለመግባት የሚደረጉ ጨዋታዎች እንደሚከተሉት ይሆናሉ።

1. Mangement vs engineering
2. Computer science vs soft ware
3. Information technology vs sociology
4. Information system vs Biotechnology, Geology and psychology
5. Marketing vs NARM and Agroeconomics
6. Law vs Accounting
7. Economics vs Geography
8. Tuorism and logistics vs Sport, Plant science and Biology

የጨዋታዎቹን ሰዓትና ቀን በቀጣይ የምንገልፅላቹ ይሆናል።

የተማ/ህ ስፖርትና መዝናኛ ዘርፍ


https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
⚠️UPDATE‼️

ዛሬ ከተከናወነው የጂሲ ካፕ የምድብ ድልድል የእጣ ማውጣት በኋላ ዘግይተው የመጡት የኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንደገና ወደ ውድድሩ ገብተው መሳተፋቸው በጂሲ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚዎችና የየክላሱ የጂሲ ተወካዮች ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል።
በዚህም ምክንያት የጂሲ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚና የተማሪ ህብረት በጋራ በተደረገው ስብሰባ መሰረት፦

1. የኢንጀነሪንግ ተማሪዎች ተመራቂ አለመሆናቸው
2. ካለን ጊዜ አንፃር እንደ አዲስ ሌላ ድልድል ማውጣት ስለማንችል
3. ድልድሉን ማውጣት ቢቻል እንኳን በተሳታፊ ቡድኖች ላይ የሚያመጣውን ችግር እና የጨዋታ ስነልቦና ማጣት

እነዚህንና ሌሎች አሳማኝ ምክንያቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ጂሲ ካፑ ገብተው የነበሩት የኢንጀነሪንግ ዲፓርትመንቶች አሁን ከሚደረገው የጂሲ ካፕ ውድድር እንዲቀሩና ጥር 2018 ላይ እነሱ ተመራቂ በሚሆኑበት ወቅት ለነሱ አመቺ በሆነ መልኩ ጂሲ ካፕ በማዘጋጀት እንዲወዳደሩ ተወስኗል።

በዚህም ምክንያት ቀድሞ ወጥቶ የነበረው የጂሲ ካፕ የጥሎ ማለፍ ድልድል በነበረበት የሚቀጥል ይሆናል።

ማኔጅመንትም ቀድሞ በእጣ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተሻግሮ እንደነበረው በዛው የሚቀጥል ይሆናል። ሌሎች ጨዋታዎችም በወጣላቸው ድልድል መሰረት ይከናወናሉ።

ወደሩብ ፍፃሜው ለመግባት የሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች

1. Computer science vs soft ware
2. Information technology vs sociology
3. Information system vs Biotechnology, Geology and psychology
4. Marketing vs NARM and Agroeconomics
5. Law vs Accounting
6. Economics vs Geography
7. Tuorism and logistics vs Sport and Biology

ጨዋታዎቹ ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚከናወኑ ቀደም ሲል መግለፃችን የሚታወስ ነው።


https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ተጠባቂው የጂሲ ካፕ ጨዋታ መርሀግብር ከነገ ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል።
Computer science vs soft ware በሚያደርጉት ጨዋታ ጅማሮውን የሚያደርግ ይሆናል።

ከፌደሬሽን በመጡ ሰዎች የ B ላይሰንስ ኮቺንግ ስልጠና በዋናው ሜዳ ላይ ስለሚሰጥ የጨዋታ መርሃግብሮች ጠዋት የሚከናወኑ ይሆናል።


https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ዛሬ በተደረጉ ሁለት የጂሲ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በ Cs እና በ software መካከል እንዲሁም በ IT እና በ sociology መካከል የተከናወነ ሲሆን CS እና sociology ተጋጣሚዎቻቸውን በመለያምት አሸንፈው አልፈዋል።

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
በመጀመሪያ ለ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ለምርቃታችሁ ቀን አደረሳችሁ እያልን ለሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች በተደረገው የባይንደር ጨረታ ማህሌት ቢያድግልኝ ህትመት ድርጅት በብር 290 ማሸነፉን ለመግለፅ እንወዳለን።

                  የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
ዛሬ የሚደረጉ የመጀመሪያ ዙር የጂሲ ካፕ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች
ዛሬ በተደረጉ ሁለት የጂሲ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በ Law እና በ Accounting መካከል በተደረገው ጨዋታ Law 3-1 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፍ እንዲሁም በ IS እና በ Biotechnology,Geology and Psychology መካከል የተከናወነወ ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ በተሰጠው መለያምት Biotech,Geology and psychology አሸንፎ ወደቀጣዩ ዙር አልፏል።
በተጨዋቾች ላይ እያየን ስላለው መልካም ስነምግባር ከልብ እናመሰግናለን።

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
2025/10/13 00:59:55
Back to Top
HTML Embed Code: