Telegram Web
የክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በግቢያችን በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል።
ለመላው ክርስቲያኖች በድጋሜ መልካም በዓልን DBUDAILY ይመኝላችኋል።
መልካም ፋሲካ!

Photo by:Yibe

@DBU11
@DBU_ENTERTAINMENT
ማስታወቂያ

@DBU11
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፈተናውን 250 ሺህ ተማሪዎች ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና እንዳሉት፥ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመለካት የሚሰጥ ነው፡፡

የሚወጡ ጥያቄዎችም የየትምህርት ክፍሎች ምሩቃን እንዲኖራቸው የሚጠበቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቅሰው፤ፈተናው ተዘጋጅቶ እንዲገመገም ተደርጓል ነው ያሉት።ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ዝርዝር በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተረጋግጦ ነው ወደ ሚኒስቴሩ የሚላከው ብለዋል፡፡

በፈተናው ሞባይል ይዞ የሚመጣና መታወቂያ ሳይዝ የሚመጣ ተማሪ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችል ጠቅሰው፥ ተማሪዎች ይህን አውቀው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@DBU11
የአስራት ወልደየስ የጤና ሳይንስ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት የቴሌግራም ቻናሉ ከቁጥጥሩ ውጪ መሆኑንና ከዚህ በኋላ በቀድሞው ቻናል ሊተላለፍ የሚችለው ይዘት እንደማይወክለው ገልፁአል።

የተማሪዎች ህብረት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ https://www.tgoop.com/Asrat_WHS መሆኑን አውቃችሁ በዩኒቨርሲቲው የምትገኙ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች እና የሚመለከታችሁ አዲሱን ቻናል እንድትቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@DBU11
BEST DISCOUNT

TECNO AND INFINIX ORGIONAL CHARGER AND EARPHONE
BOTH FOR ONLY 5OO ETB

CALL +251940219376

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አመራረጥ አዲስ መመሪያ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሃብት ብክነት እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት፤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በመላክ ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች መጠናቱን ገልፀዋል፡፡

"ዩኒቨርሲቲዎች የብዙ ደሃ ሕዝብ ሃብት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ስለዚህ ተቋማቱ በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨመላለቀ አስተዳደር ሊኖራቸው አይገባም ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት የተማረ የሰው ኃይል ከማምረት ይልቅ፣ ህንጻ ማምረት ላይ የተሰማሩ ተቋማት እንደነበሩ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚታለቡ የጥገት ላሞች ናቸው" የሚለው የአንዳንድ ግለሰቦች አባባል አሁን ላይ አይሠራም ብለዋል፡፡ 

ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የሚያዝ የገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ኃላፊዎቹም በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩንም አክለዋል፡፡ ይህንን አሰራር በመከተል "ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ አመራሮችን በሙሉ እንቀይራለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

@DBU11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
(ቪዲዮው ይታይ👆)

የምርቃት ጊዜ እየደረሰ እንደመሆኑ መጠን ከምንሰራቸው ጊዜ ከሚጠይቁ ስራዎች አንዱ የመፅሄት ህትመት ስራ ሲሆን ይህም ተማሪዎች አብረው ከኖሩት ከጓደኞቻቸው፣ከዲፓርትመንት እና አሶሴሽን፣እንዲሁም ከሚፈልጉት የተለያዩ ማስታወሻዎች ጋር ተሰንዶ የሚያዝ ማስታወሻ ስለሆነ

መፅሔቱን ማሰራት የምትፈልጉ በክፍል ተወካዮቻችሁ በኩል መልሳችሁን እንድታደርሱን መልዕክታችን ነው።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም።" - መንግሥት

ይህ የተገለፀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የስምንት የምርምር እና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በገንዘብ ሚኒስቴር በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተቋማቱ በሚቀጥለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ጠቅሰዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የበጀት ዕቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሠረት አስተካክለው በጥቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡

@dbu11
Forwarded from ᵗˢⁱᵒⁿᵃ
🌸እዮብ ቡቲክ
   /Eyob New Brand Market
🌸

💰 የሴቶች ልብስ በተመጣጣኝ ዋጋ👗👖👚👡
⚜️ቀሚስ           ጃኬት
ኮት               ሸሚዝ
ቶፕ               ቱታ
ሹራብ           ጨርቅ እና ጅንስ ሱሪ
⚜️ የሚፈልጉትን ልብስ ይዘዙን እናስመጣለን።
⚜️ የሚፈልጉትን ልብስ ለመጠየቅ DM @eyoborder1

⚜️አድራሻ፦ ደብረብርሃን ,ማእከል(ምኒልክ አደባባይ) ባለው ቅያስ ገባ ብሎ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
    Join Us On Telegram 
       @eyobmarket12          

        For Orders
        @eyoborder1
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
       
☎️ 0913439338 
🌸ጥራት ላላቸው ልብሶች ትክክለኛው ቦታ🌸
GC CUP

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተመራቂ ተማሪዎች የኳስ ግጥሚያ ከነገ ቅዳሜ 10/09/2016 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ስቴዲየም ይካሄዳል።

ሁላችሁም በኳስ ግጥሚያ እና በመዝናኛ ዝግጅቱ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።

በነገው እለት የሚካሄደው ጨዋታም
Software Vs COTM
LAW VS ELECTRICAL

የእሁድ ጨዋታ
Chemical with Mechanical Vs Industrial with Food
ታላቅ የኪነጥበብ ድግስ

ሆሄ ተስፋ ኪነጥበብ ቡድን በበዓልና በፈተና ምክንያት ሲያሸጋግር የቆየውን የኪነጥበብ ዝግጅቹን ለታዳሚዎች ለማቅረብ ዝግጅቴን ጨርሻለው ይላል።

በዝግጅቱ እንደተለመደው ፦
ግጥም
ሙዚቃ     
መነባነብ

ሙዚቃዊ ግጥሞች እንዲሁም
የመፅሃፍ ጥቆማ ና የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን አዘገጅቶ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርስቲው PR ተገኙልኝ ብሏል።
                           ሆሄ ተስፋ

@dbudaily
@dbu11
@dbu_entertainment
2024/05/19 00:15:47
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243