Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በዩንቨርስቲው የዲሲፕሊን እርምጃ ጣልቃ አልገባምየተማሪዎች ህብረት

ተማሪ ህብረት በይፋዊ ቴሌግራም ገፁ በዩንቨርስቲው የዲሲፕሊን እርምጃዎች ውስጥ ጣልቃ መግባት ተገቢ አለመሆኑን አስታወቀ። ጥፋት ሰርታችሁ ከሆነ በዩንቨርስቲው ደንብ መሰረት ትዳኛላችሁ ደንቦቹ በዩኒቨርሲቲ የተዘጋጁና ለያንዳንዱ ጥፋት ተገቢውን ቅጣት ያስቀመጡ ናቸው። በዩንቨርስቲው የዲስፕሊን እርምጃ ጣልቃ መግባት አልችልም ሲል አስታውቋል።

ህብረቱ ይህን ያለው ወቅቱ የፈተና ወቅቱ መሆኑን ተከትሎ ከኩረጃ ጋር ተያይዞ ወደ ህብረቱ ፅህፈት ቤት ለማመልከት የሚሔዱ ተማሪዎች ቁጥር በመብዛቱ ነው ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ፈተናውን መፈተን የማይቻልበት ሁኔታ ወይም ችግር ካለ ከፈተናው በፊት ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
---------------------------------------------------
ለቻናላችን ማንኛውንም መልዕክት እና መረጃ ማድረስ ሲፈልጉ @gazetegnaw_1 መጠቀም ይችላሉ።

DBU DAILY NEWS
@dbu11
@dbu111
በኢትዮጵያ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ፈቃድ እንጂ እውቅና ያላቸው ተቋማት የሉም መባሉን Ahadu radioን ዊቢ አድርጎ ATC ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ፈቃድ እንጂ እውቅና ያላቸው ተቋማት አለመኖራቸውን የኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች እና 14 ቱንም ክልሎች አጠቃሎ 375 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ሲሆን፤ እነዚህ ተቋማት ፈቃዳቸውን ከኢፌዲሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የሚወስዱ እና የሚያድሱ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ታዲያ እነዚህ ተቋማት የሚሰጡት ከዲግሪ ጀምሮ ያለው የትምህርት ደረጃ፤ በዓለም አቀፍ እውቅና ያለው እና በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ የትኛውም ሀገር ላይ ሄደው ድጋሚ የሄዱበትን ሀገር ትምህርት መማር ሳያስፈልጋቸው መስራት የሚያስችል አይደለም።

"ይህ ለምን ሆነ?፣ ተቋማቱን ዓለም አቀፋዊ እውቅና እንዲኖራቸው እና በእነዚህ ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎችም በዓለማቀፍ ደረጃ ተስተካካይ እንኳን ባይሆን ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችል የትምህርት ደረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ ለምን አልተቻልም?" ሲል አሐዱ መጠየቁን አስነብቧል።

የኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ በሰጡት ምላሽም፤ ይህን እውቅና ለመስጠት በመጀመሪያ ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ሊያገኝ እንደሚገባው ገልጸው፤ እስካሁን ግን እውቅናውን አለማግኘቱን ተናግረዋል።

"በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፈቃድ እንጂ እውቅና ገና ያልተሰጣቸው ናቸው" ብለዋል።

ተቋሙም ከዓለም አቀፍ ደረጃ ሰጭ ተቋም ማለትም (አይሶ) ገና እውቅና እንዳልተሰጠውም ተናግረዋል። እሱን ለማድረግ እና እውቅና ያላቸው የትምህርት ተቋማትን ለማፍራት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ተቋሙ የግልም የመንግሥትም ትምህርት ተቋማትን በአንድ ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ሥራ እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

@dbu11
@dbu111

  
Ethiostudyhub ሁሉንም ትምህርት ክፍሎች ያካተተ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተና(university exit exam), university entrance exam(የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና) ጥያቄዎችን አሰናድቶላችሗል። ትምህርት ጨምሮ exit እና entrance ን የሚመለከቱ ዜናዎችን... ታገኛላችሁ።

በማንኛውም browser ገብታችሁ ይኽን website https://ethiostudyhub.com ብትፅፉ ማግኘት ትችላላችሁ።

ወይም በዚህ https://ethiostudyhub.com/exit-exams webpage Link በቀላሉ መጠቀም ትችላላችሁ።

@dbu11
@dbu111
#Ads
ሀዛርድ ፒክቸር የመስክ ፎቶ ለተመራቂወች ለየት ባለ መልኩ አዘጋጅቶ እየጠበቃቹህ ነው። ልዩ ቅናሽ ከልዩ ጥራት ጋር🧏‍♂️🧏‍♂️ ፎቶን ለሀዛርድ 💃🥰ሀዛርድ ፒክቸር👍👍👍
  🧑‍🔬🧑‍🔬🧑‍🔬0916468302
👉 ገራሚ ገራሚ 🤌 የመስክ ፎቶ ና ቪዲኦ
                         🤌 የግራጆሽን ፎቶ ና ቪዲኦ
                        🤌 የስቱዲኦ ፎቶ ና ቪዲኦ
                        🤌 የሰርግ ፎቶ ና ቪዲኦ
🤌 የልደት ፎቶ ና ቪዲኦ
                       🤌 እና ለተለያዩ ፖሮግራሞች
በጥራት አሰራለን።
🪬 አድራሻ ፦ ደብረ ብርሀን ፦ ገብርኤል መገንጠያ ፊት ለፊት
🏃‍♂️‍➡️🏃‍♀️‍➡️🏃‍➡️🏃‍♀️‍➡️Hazarid Pictures
🤳🤳🤳0914468302
🤳🤳🤳0936535116
May 30 revised-Sene2017-EXIT EXAM Schedule - 1 -(1).xls
235.5 KB
ከአንድ ሳምንት በሗላ የሚሰጠው የ 2017 ሰኔ ወር ብሔራዊ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተና (university national exit exam) መርሐ ግብር(schedule)
ሰኔ 2 management
ሰኔ 3 Accounting
ሰኔ 4 ህግ.........

@dbu11
@dbu111
ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማሳለፍ ያልቻሉ ከ80 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፈቃዳቸው ሥራቸውን ማቆማቸው ተገለጸ 

በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ያስመዘግቡ ተቋማት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የተቀመጠው መምሪያ ተግባራዊ ባይሆንም፤ ከ80 በላይ ተቋማት በፈቃዳቸው ሥራቸውን ማቆማቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

"በተጨማሪም ሕብረተሰቡ አሁን ላይ የመውጫ ፈተናን መሠረት በማድረግ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እያሳለፈ ነው" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፤ "አነስተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት የሚመዝገቡ ተማሪዎች እያጡ በመሆኑ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኗል" ብለዋል።

መንግሥት እስካሁን የቅጣት እርምጃ ባይወስድም አሁን ያለው አካሄድ ግን ሌሎች ተቋማት የመማር ማስተማር ጥራትን በማሻሻል ላይ እንዲያተኩሩ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

"የመውጫ ፈተናው የተጀመረው በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን አቅም ለማሻሻል ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ እርምጃውም በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እንደሚወሰድ አስታውቋል።

የቅድመ-ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ከ2015 ሐምሌ ወር ጀምሮ፤ በሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

VIA አሀዱ ራዲዮ

@dbu11
@dbu111

 
#Ads
ሀዛርድ ፒክቸር የመስክ ፎቶ ለተመራቂወች ለየት ባለ መልኩ አዘጋጅቶ እየጠበቃቹህ ነው። ልዩ ቅናሽ ከልዩ ጥራት ጋር🧏‍♂️🧏‍♂️ ፎቶን ለሀዛርድ 💃🥰ሀዛርድ ፒክቸር👍👍👍
  🧑‍🔬🧑‍🔬🧑‍🔬0916468302
👉 ገራሚ ገራሚ 🤌 የመስክ ፎቶ ና ቪዲኦ
                         🤌 የግራጆሽን ፎቶ ና ቪዲኦ
                        🤌 የስቱዲኦ ፎቶ ና ቪዲኦ
                        🤌 የሰርግ ፎቶ ና ቪዲኦ
                        🤌 የልደት ፎቶ ና ቪዲኦ
                       🤌 እና ለተለያዩ ፖሮግራሞች
በጥራት አሰራለን።
🪬 አድራሻ ፦ ደብረ ብርሀን ፦ ገብርኤል መገንጠያ ፊት ለፊት
🏃‍♂️‍➡️🏃‍♀️‍➡️🏃‍➡️🏃‍♀️‍➡️Hazarid Pictures
🤳🤳🤳0914468302
🤳🤳🤳0936535116
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/14 08:50:40
Back to Top
HTML Embed Code: