Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
”ምርምር ለሁለንተናዊ ሀገራዊ እድገት”

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሳምንት “መጪውን ዘመን እንመግብ:- በኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎች ጋር ማስተሳሰር”
በሚል መሪ ቃል ቢሾፍቱ በሚገኘው የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ዛሬ ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ ም ተጀመረ ፡

የምርመር እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖው የተዘጋጀው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ወቅት መሆኑ ዩኒቨርስቲው ላለፋት 75 ዓመታት በመማር ማስተማር፤ በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ ጉድኝትና አገልግሎት ያበረከተውን አጠቃላይ ጉዞ የሚታወስበትም ነው ሲሉ
ኘ/ር ወራሽ ጌታነህ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ኢኖቬሽን ም/ል ፕሬዝዳንት ገልፀዋል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዓለም የምግብ እና ግብርና ድርጅት (FAO) ተወካይ የሆኑትን ጄምስ ብራዉዲ ፤ በፍጥነት እያደገ ያለውን የአፍሪቃ ህዝብ የምግብ ፍላጎት ለማርካት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ፈጠራዎችን መጠቀም ወሳኝ መሆኑን አመላክተው ዛሪ የተጀመረው ኤክስፖ ይህን ስትራቴጂ ለማሳካት በግምት 70 በመቶ መጨመር ያለበትን የእርሻ ምርት ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የአዲሰ አበባ ዪኒቨርሰቲ የ2017 የምርምር እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ኮሌጆች እንደሚከበር የገለፁት ኩነቱን በንግግር የከፈቱት ሂካ ዋቅቶሌ (ዶ/ር) የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዲን ፣ዩኒቨርሲቲው ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና በምርምር ለታገዘ ግብርና ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል። ‎
የ 2025 ኢራስመስ ከሰሃራ በታች አፍሪካ አገራት ጉባዔ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሪና በመምህራን የአቅም ግንባታ ዙሪያ ከሚሰራው ኢራስመስ (ERASMUS) ጋር በመተባበር "የትምህርት ሚና ወደ ዘላቂ አሬንጓዴ እድገት ሽግግር The Role of Education in Green Transition" በሚል መሪ ሐሳብ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በራስ መኮንን አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ከስሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ እና የአውሮፓ አገራት የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እና የአረንጓዴ አሻራ ሽግግርን ተግባራዊ ለማድረግ ያለሙ ሐሳቦችና መፍትሔዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀረፀው ስትራቴጅክ ዕቅድ መሰረት ዓለም አቀፍ ትብብርን ለመፍጠር አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕ/ት ጀይሉ ኡመር (ዶ/ር) ከኢራስመስ ጋር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ኢራስመስ ከ30 በላይ በሆኑ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እንዲሁም ቱርክየንና ኖርዌይን በመሳሰሉ ሌሎች ሀገራት ድጋፍ እየተደረገለት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የትምህርት ዕድልና የልምድ ልውውጥ በማካሄድ የአቅም ግንባታ ላይ የሚሰራ ሲሆን ጉባዔው ለ3 ቀናት ይቆያል
የ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎች የስራ አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከስራ ቀጣሪ ተቋማት ጋር የተገናኙበት የ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አውደ ርዕይ ዛሬ ግንቦት12 ቀን 2017 ዓ ም ተጠናቋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ ለተሳተፉ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች እና ተማሪዎች በተገኙበት የምስጋና እና ሰርተፍኬት ያበረከቱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀይሉ ኡመር (ዶ/ር) አወደ ርዕዩ በርካታ ተቋማትን በማሳተፍና ተማሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ተማሪዎች በትምህርታቸው ብቁ ; ለመጪው ዘመን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አተኩሮ እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል እንዲህ አይነቱን አውደ ርዕይ ሲያዘጋጅ ይህ 7ኛው ሲሆን እስካሁን ከ 20 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የስራ እድል እንዲያገኙ ማስቻሉ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።
This is the schedule for the online mock exam for Grade 12 students who will be taking the national exam digitally. The exam will be held on May 29 and 30 at Different AAU Campuses. Please see the schedule below for details.
2025/05/30 08:27:40
Back to Top
HTML Embed Code: